አዲስ ሪፖርተር ዜና – የነዳጅ ነዳጅ መርቶች ላይ ተጨማሪ ግብር እንደሚደረግ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የሰነበተው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታው መኮንን ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቁ።
ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት በነዳጅ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ግብር እንደሚጣል በስፋት ምንጭ የሌለው መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ከዝግጅት ክፍላችን ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
በተለያዩ ሚዲያ አውታሮችና በማህበራዊ ገጾቭ በዘንድሮው በጀት ዓመት በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ ሰላሳ በመቶ ግብር እንደሚጣል ነበር የተመለከተው። ምንጭ ሳይጠቀስ የተሰራጨው መረጃ አስራ አምስት በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ አስራ አምስት በመቶ የኤክሳይዝ ቀረጥን ተጨማሪ እንደሚደረግ ስሌት የተሰራበት ነበር።
ተሰራጭቶ የነበረውን ይህንኑ የጭማሪ መረጃ ተከትሎ የኑሮ ውደነቱ ሊባባስ እንደሚችል በስፋት ተነገኦ ነበር። የነዳጅ ዋጋ መቸመር ከሁሉም አገልግሎቶች ጋር የሚነካካና የሚያያዝ በመሆኑ የመጓጓዣና የተለያዩ አገልግሎቶች ዋጋ ላይ የተጋነነ ጭማሪ ስለሚያስከትል የዘርፉ ባለሙያዎች ከወዲሁ ምክረ ሃሳብ ሲሰጡ ከርመዋል።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታው መኮንን ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት፤ በተለያዩ አግባቦች ሲነገር ከነበረውና ሲሰራጭ ከሰነበተው መረጃ በተቃራኒ “ ምንም የሚጨመር ተጨማሪ ግብር የለም ፤መረጃው ስህተት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት የነዳጅ ምርቶች ላይ የተጣለው ግብር በነበረበት የሚቀጥል ይሆናል።
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393





