ጌዲዮን ጢሞቲዎስ “ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረት መፍትሔው ክልላዊ ምጣኔ ሀብታዊ ውህደት ነው” አሉ፤

Date:

አዲስ ሪፓር አዲስ አበባ፡- “የኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረት መፍትሔው ክልላዊ ምጣኔ ሀብታዊ ውህደት ነው” ሲሉ ያስታወቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ገዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የኤርትራ መንግስት ሉዓላዊ ሆኖ ሲያበቃ “የእኔ የሆነው የእኔ ነው፣ የአንተ የሆነው ደግሞ የእኛ ነው” የሚለው እሳቤው በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው ውጠት አንዱ ምክንያት እንደሆነም አመልክተዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዘ ሆርን ሪቪው በጋራ ባዘጋጁት የውጭ ጉዳይ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ውጥረት የረጅም ጊዜ ታሪክ እንዳለው ያስረዱ ሲሆን የውጥረቱ መሰረታዊ ምክኛቶች ናቸው ያሏቸውን አምስት ነጥቦች ዘርዝረዋል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የኢትዮጵያን የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚሁ ማብራሪያቸው የኢትዮጵያና ኤርትራን ግንኙነት ትኩረት አድርገው አቅርበዋል። ቀጠናው እጅግ ከፍተኛ የልማት አቅም (በሰውና በተፈጥሮ ሀብት) ቢኖረውም፣ ለረጅም ጊዜ በግጭት፣ አለመረጋጋትና ውጥረት ተለይቶ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ሥር የሰደደው የኢትዮኤርትራ ውጥረት

ዶ/ር ገዲዮን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የቅርብ ጊዜ ውጥረት ያልተለመደ ሳይሆን ከ1960ዎቹ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ግጭት የበላይነት የነበረው ግንኙነት ቀጣይ መገለጫ መሆኑን አስረድተዋል። ከ1998-2000 ዓ.ም. በተካሄደው ጦርነት ኤርትራ ወራሪ እንደነበረች የኤርትራ-ኢትዮጵያ የይገባኛል ጥያቄዎች ኮሚሽን (Eritrea-Ethiopia Claims Commission) ማረጋገጡን ጠቅሰዋል። ምንም እንኳን በ2000 ዓ.ም. በአልጀርስ ስምምነት ጦርነቱ ቢቋረጥም፣ እስከ 2018 ድረስ ለ18 ዓመታት “ሰላምም ጦርነትም የለም” በሚል hostile limbo ውስጥ መቆየታቸውን አመላክተዋል። ኢትዮጵያ በ2018 ግንኙነቱን ለማሻሻል በጎ ፈቃድና ጥረት ብታደርግም፣ ይህ ግንኙነት አጭር ጊዜ ብቻ የዘለቀ ሲሆን፣ የኤርትራ መንግሥት ሰላማዊና መደበኛ የጎረቤታሞች ግንኙነትን እንደሚጠላ አሳይቷል ብለዋል።

ሚኒስትሩ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ወደ ባህር ለመውጣት ያላት ምኞት እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ከታሪካዊው ማስረጃ ጋር እንደማይጣጣም አብራርተዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደር የባህር በር ፍላጎትን አጥብቆ ባፈነበት ወቅትም፣ የኤርትራ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ጠላትነት የተሞላበት አቋም እንደነበረው አስረድተዋል።

አምስቱ የውጥረት ስር መሰረቶች

ዶ/ር ገዲዮን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለሚታየው ዘላቂ ግጭት አምስት ዋና ዋና ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። የመጀመሪያው የተዛባ የጥቅም ፍላጎት ሲሆን የኤርትራ መንግሥት ሉዓላዊ እና ነጻ ሀገር ሆኖ፣ ነገር ግን ከኢትዮጵያ የፖለቲካዊ አካልነት ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችንና መብቶችን የማቆየት ፍላጎት አለው። ይህ “የእኔ የሆነው የእኔ ነው፣ የአንተ የሆነው ደግሞ የእኛ ነው” የሚለው የተዛባ መብት ስሜት፣ ከ1998 ግጭት በፊትም ቢሆን ሕገ-ወጥ እና ብዝበዛ ላይ የተመሰረተ የንግድ ልምምዶች እንዲስፋፉ አድርጓል።

ሁለተኛው የውጥረት መሰረት ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች መሣሪያ መሆን ነው። የኤርትራ አመራር ኢትዮጵያን ለማተራመስና እድገቷን ለመግታት ለሚፈልጉ ኃይሎች ሁሉ እንደ መሣሪያ ሆኖ የመቅረብ ዝንባሌ አለው። የኤርትራ መንግሥት ለሶስተኛ ወገኖች የክልላዊ ወኪል ሆኖ ለማገልገል ያለው ጉጉት፣ እንዲሁም የኤርትራ መኖር ዋናው ዓላማ ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ማገድ ነው ብለው የሚያምኑ ኃይሎች መኖራቸው ግንኙነቱን ያወሳስበዋል።

ሶስተኛው የኢሳያስ ዶክትሪን ሲሆን ይህ በግልጽ ያልተቀመረ ቢሆንም በተከታታይ ተግባራዊ ሆኖ የሚታይ ዶክትሪን፣ የኤርትራ የሉዓላዊነት ቀጣይነት የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ አለመረጋጋት፣ መከፋፈል እና ደህንነት ማጣት ላይ ተመስርቶ ነው ብሎ ያምናል።

የኤርትራ መንግሥት ያልተለመደ ባህሪ (Anomalous State) በአራተኛ የግጭነት መነሻ ምክንያት ሆኖ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ የጠቀሱ ሲሆን የኤርትራ መንግሥት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ደህንነት ለማሻሻል ምንም ዓይነት ጥረት አያደርግም። መንግሥት እንደ ግብ እንጂ የዜጎችን ደህንነት ለማሻሻል እንደ መሣሪያ አይቆጠርም። የኤርትራ ዋነኛ ትኩረት ጦርነት ማካሄድ ነው። ይህ መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ጫና ስለሌለበት፣ ሙሉ ኃይሉን በክልላዊ ሴራና ጀብዱ ላይ እንዲያተኩር ያደርገዋል። ይህ ሁኔታ የዜጎችን ግዴታ የለሽ ወታደራዊ አገልግሎት (modern-day slavery) እንዲያስከትል ምክንያት ሆኗል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታገኝ ሆን በሎ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ መታገዱ ሲሆን በፖለቲካዊ ንቃተ ህሊና ባላቸው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የኤርትራ ነጻነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያበላሽ መንገድ ተፈጽሟል የሚል እምነት ተስፋፍቷል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኤርትራን መንግሥትነት ቢቀበልም፣ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር መታገዷን ጥልቅ ኢፍትሃዊነትና ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ አድርጎ ይመለከተዋል። ኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ ወደ ባህር መውጫ መንገድ ማግኘት የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ትዕግስት እና የውህደት ራዕይ

ዶ/ር ገዲዮን የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙ በርካታ የአካባቢ አስተዳደር ክፍሎች ውስጥ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን እና የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያን ለሚያውኩ ቡድኖች ቁሳዊ ድጋፍ በመስጠት በውስጥ ጉዳዮቿ ጣልቃ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሁሉ ኢትዮጵያ የመከላከል መብቷን እንድትጠቀም የሚያስችል በቂ ምክንያት (casus belli) ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ትዕግስት እያሳየች እና ግጭትን ለመከላከል በሙሉ ኃይሏ እየሰራች መሆኑን አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የክልላዊ ፖሊሲ ዓላማ፣ ቀጠናው አንድ የጂኦ-ኢኮኖሚና የባህል ቦታ ነው በሚል እምነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የሆርን አፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ ማህበረሰብ መፍጠር ነው። ይህ ራዕይ እንዲሳካ፣ የሆርን ሀገራት ስልታዊ የራስ ገዝ አስተዳደር (Strategic Autonomy) ሊኖራቸው እና የውጭ ኃይሎችን የበላይነት (hegemony) መቃወም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የረዥም ጊዜ ሰላም ሊመጣ የሚችለው ጥልቅ እና ዘርፈ ብዙ ትብብር ባለው ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ ነው። የኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ የባህር መውጫ ፍላጎት በዚህ የኢኮኖሚ ውህደት እቅድ ውስጥ በጋራ በሚጠቅም መንገድ ይፈታል። ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ፍላጎቷን የሚያሟላና ለኤርትራም ጠቃሚ የሚሆን የአሰብን ወደብ ለመጠቀም አማራጭ ዘዴዎችን ለመዳሰስ ዝግጁ ናት።

ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የቀረበ ጥ

ሚኒስትሩ የኤርትራ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ሰላምን እንደሚያበላሽ (spoiler) እና ቀጠናውን ደካማና ያልተረጋጋ ሆኖ ለማየት ከሚፈልጉ ሀገራት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የኤርትራ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ እና ቀጠናው ያለውን የተሳሳተ ፖሊሲ እንዲያርም፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለችውን ቅስቀሳና ጥሰት አቁማ፣ በጎ-አሳቢነት የተሞላበት ውይይት እንዲጀምር ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ሚንስቴሩ ኢትዮጵያ ለውይይት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነገሰውን የግጭት ታሪክ አሻግሮ ማሰብ እና ለጋራ ብልጽግና አብሮ ለመስራት አዲስ መግባባት (modus vivendi) ለመፍጠር ዝግጁ መሆኗን ገልዋል፡፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...