በኢትዮጵያ የወተት ምርት ጥራት አሳሳቢ በመሆኑ ባለስልጣኑ ቁጥጥሩን ሊያጠብቅ ነው

Date:

አዲስ ሪፖረተር – በኢትዮጵያ ለማኅበረሰቡ የሚቀርብ ብዙ መጠን ያለው የወተት ምርት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርብ አምስት በመቶ ብቻ የሚሆነው የወተት አቅርቦት ጥራቱ የጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለሥልጣን ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤት የእንሰሳት ተዋፅዖና አልሚ ምግቦች ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለአዲስ ሪፖርተር እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ አጠቃላይ የወተት ምርት አቅርቦት ላይ የጥራት ችግር መኖሩን ተናግረዋል።

ማንኛውም ሰው እንደፈለገ ወተት እያዞረ መሸጥ እንደማይችል፣ ይህን የመረዳትና የማክበር የግንዛቤ ጉድለት በማሕበረሰቡ ዘንድ መኖሩን የገለጹት ኃላፊው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የወተት ምርትና ሽያጭ ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ጥንቃቄ አንፃር በጀሪካንና በሌሎችም ባልተፈቀዱ ዕቃዎች ማጓጓዝ ጥራቱን ከማጓደል ባሻገር ለበሽታ አምጪ ተዋህስያን የሚያጋልጥ መሆኑን አስረድተዋል። አክለውም፤ “ዘርፉ ያላደገ በመሆኑ የሚስተዋሉ የጥራት ችግሮችን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ አልተቻለም” ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በወተት ምርቶች በተለይም በባህላዊ መንገድ ለሕብረተሰቡ የሚቀርቡ ምርቶች ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚሹ በመሆናቸው፤ ወተት አቅራቢዎች በቂ ስልጠናዎችን በመውሰድ ዘመናዊ አሰራሮችን  ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዚህም በዋናነት ከሚስተዋሉ ችግሮች አንጻር የመኖ በበቂ ሁኔታ አለመቅረብ እና የእንሰሳት አያያዝ ተጠቃሽ መሆኑን አስረድተዋል። ይህ ማለት ሙሉ ለሙሉ ጥራት የጎደላቸዉ የወተት ምርቶች ገበያ ላይ አሉ ማለት እንዳልሆነ እና ጥራት ያላቸው የወተት ምርቶች ስለመኖራቸው አንስተዋል።

በባለሥልጣኑ በኩል የተጀመሩ የቁጥጥር ሥራዎችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎችም ተጠናክረው እንደሚሰሩም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል። የዴስክ ኃላፊው አክለውም ባለሥልጣኑ የወተት ጥራትን ለማስጠበቅ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ሕጋዊ ሂደቱን በተመለከተ ለማሕበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...