ኮንጎና ሩዋንዳ – ለቀናት ያልዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ፊርማ መፍረስ

Date:

አዲስ ሪፕርተር – በሩዋንዳ የሚደገፈው M23 ታጣቂ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እያደረሰ ባለው ጥቃት የኮንጎው ፕሬዚዳት ፌሊክስ ኪሲኬዲ የሩዋንዳ መንግስትን ከሰዋል።

እየተባባሰ በመጣው የሁለቱን ሀገራት ውጥረት አስመልክቶ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት ሩዋንዳ ከሳምንት በፊት በአሜሪካ የተፈፀመውን የዋሽንግተን ስምምነት ጥሳለች በማለት ክስ አቅርቧል።

የኮንጎ መንግስት ክሱን ያቀረበው የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሴምበር 2 ላይ የሩዋንዳ ወታደሮች የቡሩንዲ ግዛትን መምታታቸውንና እና በኮንጎ የሚገኘውን ወታደራዊ ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው።

በዚህም መሰረት የቡሩንዲ ወታደሮች በሩዋንዳ የሚታገዘውን የM23ን ጨምሮ የታጠቁ ቡድኖችን ለመዋጋት በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ተሰማርተዋል።

ከዚህ ቀደም የሩዋንዳ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በዋሽንግተን የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን በስምምነቱም ሩዋንዳ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ፣ የM23 ቡድንን መደገፍ እንድታቆም እና ትጥቅ እንድታስፈታ የሚያዝ ውል ያካትታል።

ሆኖም እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የM23 ታጣቂዎች ስምምነቱን በመጣስ በኮንጎ ሁለት የደቡብ ኪቩ ግዛት ከተማዎችን መቆጣጠረራቸውንና ጦራቸውን ወደ ኡቪራ ከተማ ማዘዋወራቸው ተገልፇል።

የድምበር ከተማ የሆነችው ኡቪራ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮነጎ ስር የቀረች ብቸኛዋ የደቡብ ኪቩ ግዛትም ሆናለች።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...