የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኤርትራ መንግስት በአፋር ሕዝብ ላይ የሚያደርስርውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መዘገበ

Date:

አዲ ሪፖርተር – የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(RSADO) ታህሳስ 1 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ACHPR) በሰኔ 4 ቀን 2025 እ.ኤ.አ የቀይ ባህር አባፋ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት RSADO በኤርትራ መንግስት ላይ ያቀረበውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ጥያቄ መያዝ እና መመዝገቡን አስታውቋል። ዜናው የኤርትራ መንግስትን ከማጋለጥ አንጻር የድርጅቱ ትግል መስመር የሚያሳይ መሆኑም ተመልክቷል።

ቅሬታውንም ተከትሎ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ACHPR) በደንካሊያ ክልል በ”ቀይ ባህር አፋር” ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ በደል አስመልክቶ በኤርትራ መንግስት ላይ ያቀረበውን ቅሬታ በኮሚዩኒኬሽን ቁጥር 868/25 መያዝ እና መመዝገቡን አስታውቋል።

ወሳኔውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው RSADO ይህ ውሳኔ በኤርትራ ዳንካሊያ ክልል ለሰፈሩት የ”ቀይ ባህር አፋር” ህዝብ ተወላጆች ለፍትህ፣ ጥበቃ እና እውቅና ለማግኘት በሚደረገው ረጅም ትግል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጿል።

ለበርካታ አስርት ዓመታት መፈናቀል ፣ ስደት እና ግድያ ሲፈፀምባቸው ከነበሩት ስልታዊ ጥቃቶች መካከል እንደነበሩ የጠቀሰው ድርጅቱ በቀይ ባህር ዳርቻ ያለውን የአባቶቻቸውን የትውልድ አገር በህገ-ወጥ መንገድ እንደተወሰደም አሳታውቀዋል።ለዚህም RSADO አሉኝ ያላቸውን ማስረጃዎች በአራት መደብ አዘጋጅቶ ያቀረበ ሲሆን እነርሱም

  • የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ስለ ተወላጅ ማህበረሰቦች ያላቸውን ግንኙነት እና አመለካከት የሚያሳዩ ሰነዶችን
  • የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል እና ልዩ ዘጋቢ ሪፖርቶች፣ በኤርትራ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች አጣሪ ኮሚሽን የተገኙትን ግኝቶችን
  • እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኤርትራ ላይ ያላቸውን የሰብአዊ መብት ይዞታ ዘገባ እና RSADO በሰብአዊነት ላይ በተጠረጠሩ ወንጀሎች ላይ ቀደም ሲል ያቀረባቸው መረጃዎችን እና
  • የቀድሞ የህግደፍ ከፍተኛ ባለስልጣናት መግለጫዎችን ጨምሮ በማያያዝ አቅርበው ነበር።

RSADO ኮሚሽኑ ለወሰደው ፈጣን እርምጃ ያመሰገነ ሲሆን፣ ከዚህ በኃላም ተጨማሪ ሰነዶችን ወይም ማብራሪያዎችን ለማቅረብ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

አዲስ ሪፖርተር ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር...

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

አዲስ ሪፖርተር - በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ...

ዲያቆን ዳንዔል ክብረት ዕምነታቸውን ቀይረው “ጴንጤ ሆነዋል” የሚል የሚዲያ ዘመቻ እንዲከፈትባቸው ዕቅድ መያዙ ተሰማ

አዲስ ሪፖርተር - “ሙዓለ ጥበባት ዲያቆን ዳንዔል ክብረት እምነታቸው...

Official Statement Regarding the Human Rights Watch Report on the WTSH Zone

Prioritizing Sovereign Legal Frameworks and Evidence-Based Assessment Over Unverified...