ከ2009 እስከ 2025 ያልተቀየረው የኤርትራ ኢትዮጵያን የማተራመስ ቀጣናዊ ስትራቴጂ፤ “ሻዕቢያ እያለ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም”

Date:

ሻዕቢያ በከፍተኛ ጭነቀት ውስጥ ነው፤ ሻዕቢያ የቆፈራቸው ኢትዮጵያን የሚያሰምጡ ጉድጓዶች ሁሉ እየተዘጉ ነው፤ አሁን የቀረው በቀሪው ጉዳጓድ ሻዕቢያን መቅበር ነው። ኢትዮጵያን በማጥፋትና በማተራመስ ላይ የተመሰረተውን ዕቅዱን ለማሳካት ሶማሊያን በውክልና እያተራመሰ ሲዳክር ዕድሜውን የጨረሰው ሻዕቢያ ወዳ ሳህል የመመለስ ዕድል እንኳን እንደማይኖረው ስለገባው ጭንቀት ውስጥ ነው፤ በሃይማኖት ለማባላት የጀመረውን የመጨረሻ ካርዱን ባለ ቤሌለ ኃይሉ ለመጠቀም እየተክለፈለፈ ያለውም በዚሁ ጭንቀቱ ሳቢያ ነው። ይህንኑ እንዲያስፈጸሙ የተሾሙት የአብሮነት ቦርድ አባላት ሰሞኑን በመግለጫ የሚደግፉት ይህ የትርምስ አጀንዳ የኖረና ያልተሳካ የሻዕቢያ ሩጫ ወደ 2009 ይመልሰናል። ጉዳዩ ወደ 2005 ሲመጣ የመጨረሻው ስለመድረሱ አመላካች ጉዳዮች በርክተዋል ።

በዝግጅት ክፍሉ ሪፖርተር

አዲስ ሪፖርተር – ኤርትራዊው ጸሐፊና የፖለቲካ ተንታኝ ዮሴፍ ገብረሕይወት ኤርትራ በሶማሊያ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ በአጋጣሚ ወይም በርዕዮተ ዓለም ሳይሆን ስትራቴጂአዊ አካሄድ መሆኑን የሚገልጹ ተከታታይ ጽሑፎችን (እ.ኤ.አ. በ2009 እና 2010) አውጥቶ ነበር። የኤርትራ ተቃዋሚ ተንታኝ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ገብረሕይወት “የኤርትራ ዋና ግብ እስላማዊ ቡድኖችን በሃይማኖታዊ ዙሪያ መደገፍ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳከም ሶማሊያን ያለመረጋጋት ውስጥ ማቆየት ነው” ሲል ተከራክሯል።

በዛን ወቅት ኤርትራ በመሪዎቿ ሴራና በተላለፈቸው ቀይ መስመር እንዲዛጋባት ሆኗል። በማዕቀብ ታስራ፣ ብቻዋን ተዘግቶባት ዛሬ ድረስ “ሰዓት የቆመባት ብቸኛ አገር” የሚል ማዕረግ ለመከናነብ በቅታለች። አገር እንደ ከረሜላ የሚወራወርበት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂና የባንክ ኤቲኤም ካርድ ብርቅ የሆነባት የዓለማችን ቀዳሚዋ ድንዙዝ አገር ሆናለች።

እንደ ዮሴፍ አገላለጽ የኤርትራ ፖለቲካዊ “ምስጢራዊ ኮድ” ቀላልና ወጥ ነው፣ የተረጋጋች ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ለኤርትራ ጎጂ ናት። ሶማሊያ ሰላማዊና የተቀናጀች ብትሆን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷን እንደምታስተካክል፣ በደህንነት ረገድ እንደምትተባበር እና የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዱ የታጠቁ ቡድኖችን መደገፍን እንደምታቆም ጽፏል። ይህ ሲሆን ኢትዮጵያ ትኩረቷን በልማት፣ በቀጣናዊ መሪነት እና በዓለም አቀፍ ተሳትፎ እንድታደርግ ዕድል ይሰጣታል። ይህም የኤርትራ መንግስት ሊከላከለው ወይም ከቶውንም እውን ሆኖ ሊያየው የማይፈልገው ጉዳይ ነው። የረጋች ሶማሊያ አትፈለግም!!

ዛሬስ? ኤርትራ የሶማሊአይን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼኽን በመያዝ፣ ወታደር በማሰልጠን፣ በውክልና በማስታጠቅ ላይ ለመሆናቸው ራሳቸው ቀርጸው ያሰራጩት የቪዲዮ መረጃዎች ቁጥር ስፍር ናቸው። የእስራኤል ሚዲያዎች ኤርትራ ከየመኑ ሃውቲ ጋር ተሻርካ ቀይ ባህርን እያወከችም ነው። ለዚህም መረጃዎች አሉ።

ጸሐፊው ከላይ ያነሳቸውን ነጥቦች ዘርዝሮ ካስረዳ በሁዋላ አፈ ታሪክ እንዳልሆኑ ያስገነዝባል። የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያን ሰላም ለመንሳት በሚልና በሌሎች አጀንዳዎቹ መነሻነት ከአልሸባብ ጋር ሲርመጠመጥ እንደነበር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተወሰዱ እርምጃዎች ተረጋግጧል።
እ.ኤ.አ. በ2009 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ እና ኤርትራ የክትትል ቡድን ሪፖርቶች መሠረት በውሳኔ ቁጥር 1907 በኤርትራ ላይ ማዕቀብ ጣለ። ተመድ እንዳለው ኤርትራ አሜሪካ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የሽብር ቡድን አድርጋ ለፈረጀችው አል-ሸባብን ጨምሮ ለሶማሊያ ታጣቂ ቡድኖች የጦር መሣሪያ፣ ስልጠና እና ፖለቲካዊ ድጋፍ ሰጥታለች። ዛሬስ? ኤርትራ ከትናንቱ ምን አጓደለች? እንደውም ዘልቃ ገብታ ሕዝብን ሰላምና ጤና የሚነሱ ቡድኖችን በማደራጀት እየሰራች ለመሆኑ መስክር መቁጠር የሚያሻ አይመስልም። አሁን አሁን በሚወጡ የደህንነት መረጃዎች የሃይማኖት ልዩነት ለመፍጠር ግድያን ጨምሮ በተለያዩ የአድማ ጥሪዎች ኤርትራ አለችበት።

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የኢሳያስ ተላላኪዎችና የመዋቅር ሰዎች የሽብር ትዕዛዝና ዕቅድ ተቀብለው ቤተክርስቲያን ስር ሲዘምቱና ሲያዘምቱ የነበሩ፣ የሃይማኖት ግብግብ እንዲነሳ ኦርቶዶክስ ውስጥ ገብተው ሸማ መራጭና፣ ሰልፍ አስተባብሪ የነበሩ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የታዋቂ ዳንኪረኛ የትዳር ጓደኞች የሁሉም መረጃ የተስነደ ነው። በጎረቤት አገራትም ያለው መዋቅር ድብቅ ባይሆንም ውሎ አድሮ መጋለጡ አይቀርም። ልክ እንደ ሶማሊያ።

እ.ኤ.አ. በ2010 የሶማሊያ መንግስት ራሱ ተመሳሳይ ክስ አቅርቧል። የሶማሊያ የመረጃ ሚኒስትር ለጋሮዌ ኦንላይን እንደተናገሩት ከፍተኛ የአልቃይዳ አመራሮች ወደ ሶማሊያ የተጓዙት በኤርትራ እና በየመን በኩል ነበር። በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ አልቃይዳ ላይ እየደረሰ ባለው ግፊት ምክንያት ሶማሊያን እንደ አዲስ የጦር ሰፈር ለመጠቀም እየመነጠሩ እንደነበር ተናግረዋል። በወቅቱ የዓለም ዓቀፉ የቀውስ ተንታኝ ቡድን (ICG) ባልደረባ የነበሩት ራሺድ አብዲም ሶማሊያ ደካማና የተከፋፈለች በመሆኗ የአልቃይዳ ፍላጎት በሀገሪቱ ላይ እየጨመረ መሆኑን ገልጸው ነበር።

ሃሰን ሼኽን ደጋግሞ በመጋበዝ ኢትዮጵያ ላይ ቀይ ባህርን አስታከው ሲዶልቱ የከረሙት ኢሳያስ፣ ሚስጢራቸውን እንደቀድሞው እንኳን መጠበቅ አልቻሉም። ዛሬ ደረስ በአሜሪካ የሽብርተኞች ቋት ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን ትህነግን የሽብሩ አካል በማድረግ ኢትዮጵያን ለማተራመስ እስከ አማራ ክልል የተስፈነጠሩት ኢሳያስ፣ የበሶማሊያ የነበረውን ሰላም ወደ ቀውስ ለመለስ፣ ቀደም ሲል ረግተው የነበሩ ቀበሌዎች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር እንዲውል የፈጸሟቸው ተግባሮች በሙሉ አንድ ላይ ቢጨመቁ እንዳለፈው እንዲከርችመባቸው ለማስደረግ ከበቂ በላይ ናቸው።

እ.ኤ.አ. በ2012 የአሜሪካ የግምጃ ቤት መሥሪያ ቤት ለአል-ሸባብ የገንዘብ እና የሎጂስቲክስ ድጋፍ በመስጠት በከሰሳቸው በኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሉ ያታወሳል። እነዚህ እርምጃዎች ዮሴፍ ቀደም ብሎ ያቀረበውን መከራከሪያ አጠናክረውታል “ኤርትራ ሶማሊያን ኢትዮጵያን ለማዘናጋት፣ ለማዳከም እና ለማናጋት እንደ መሣሪያ ትጠቀምባታለች” የታየውም ይህ ነው። እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅዕኤል በሶማሊያ በኩል ከኦብነግና ከአልሸባብ ጋር እንድሰሩ የተሾሙበት ሚስጢርም ይህ ነው። የአገር መከላከያ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “በርካታ ኢትዮጵያዊ ታጣቂዎች ከአልሸባብ ጋር ተደምስሰዋል። የሚገርም ነው ከአልሸባብ ጋር ምን የራሉ” ሲሉ በመድረክ ላይ መናገራቸውን እዞኢህ ላይ ማንሳት ልብ ይሏል።

እስከ 2025 ድረስ ይህ ስትራቴጂ አሁንም የቀጠለ ሆኗል። የአልጀዚራ እና የዓለም አቀፍ የችግር ጥናት ቡድን ሪፖርቶች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት እየተበላሸ መሆኑን ይገልጻሉ። ኤርትራ በታህሳስ 2025 ከኢጋድ (IGAD) መውጣቷ ቀጣናዊ ትብብርን አለመቀበሏን የበለጠ ያሳያል። እነዚህ ሁነቶች በአንድ ላይ ሲታዩ ዮሴፍ ከአሥር ዓመታት በፊት የገለጸው ፖሊሲ በመሠረታዊነት እንዳልተቀየረ ይጠቁማሉ። በተለይም የኢጋድ ዋና ምሶሶ የሆነው ዓላማው የቀጣናውን ሰላም ማረጋጋት ላይ ነውና ከዚህ ሕብረት ማፈንገጥ በራሱ ለኤርትራ የትርምስ ፖሊሲ ዘለአለማዊነት ማሳያ ነው።

ዮሴፍ ገብረሕይወት እ.ኤ.አ. በ2009 እና 2010 መጀመሪያ ላይ ያቀረበው ዋና መከራከሪያ ዛሬም አስፈላጊ ሆኖ ቀጥሏል። የኤርትራ እርምጃዎች ግልጽ አመክንዮ ይከተላሉ ሲል ተከራክሯል። ኢትዮጵያን የሚያዳክም ከሆነ ታጣቂዎችን መደገፍ፣ ኢትዮጵያን የሚያጠናክር ከሆነ ሰላምን መቃወም እና ኢትዮጵያ ትኩረቷ እንዲከፋፈል አለመረጋጋትን ማስቀጠል። በዚህ እይታ ሶማሊያ በግሏ ግብ አልነበረችም ይልቁንም ኤርትራ ኢትዮጵያን በተዘዋዋሪ ለመውጋት የተጠቀመችበት የጦር አውድማ ነበረች።

በ2025 የኤርትራ ቀጣይነት ያለው መገለል፣ ከኢትዮጵያ ጋር እየጨመረ የመጣው ውጥረት እና ከቀጣናዊ ተቋማት መውጣቷ አሁንም ያው አስተሳሰብ ፖሊሲዋን እየመራው መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ መረጋጋትን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን እና ቀጣናዊ ትብብርን ስትፈልግ ኤርትራ ግን ኢትዮጵያ ያለ ግጭት ልትበለጽግ የምትችልበትን ማንኛውንም ቀጣናዊ ሥርዓት መቃወሟን ቀጥላለች።

ኤርትራ እንደ አገር ከቆመችበት የተወናበደ ውሳኔ ማግስት ጀምሮ እምኗን በሙሉ ኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ በማደራጀት ነው የኖረቸው። በቅርቡ ለውጡን ተከትሎ የተጀመረውን አዲስ ግንኙነት ተትሎ ባህር ዳር ቢሮ በመክፈት የትርምስ መዋቅር ተክላለች። በስማሊያና ሱዳን በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ዞራለች። በስውር የአሽከርነት ስራ ስጸራላት ለነበረችው ግብጽ በግልጽ አፈንዳዳ ኢትዮጵያን ለማተራመስ “ጽምዶ” ፈጥራለች። ብዙ ብዙ …..ማለት ይቻላል።

“በፀሐይ የታየን በጧፍ አይፈልጉትም” ነውና የሶማሊያ የረጅም ጊዜ አለመረጋጋት ለብቻው የተከሰተ አይደለም፣ የኢትዮጵያ የደህንነት ተግዳሮቶችም በአጋጣሚ የመጡ አይደሉም። እነዚህ ጉዳዮች የታቀዱ የቀጣናዊ ስትራቴጂ ውጤቶች ናቸው። ዮሴፍ ከዓመታት በፊት እንዳስጠነቀቀው ኤርትራ አለመረጋጋትን እንደ መሣሪያ መጠቀም እስካልተወች በሶማሊያ ሰላም እና በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ሕልም ሆኖ ይኖራል። ኤርትራ የችግሩ ዋነኛ አካል እንጂ መፍትሔ ሆና አታውቅምና አሁን ላይ በቀጠናው ኤርትራ ላይ የወደቀውን የመንግስት ቅርጽና ወግ የሌለውን ድራጎን የማስወገዱ ጉዳይ ከኢትዮጵያ አልፎ ቀጠናዊ፣ ከዛም አልፎ ዓለም ዓቀፋዊ አጀንዳ ሆኗል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...