የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ90ኛ ዓመት ምስረታው መጥቆ መሄዱን የሚያሳይ መረጃ ይፋ አደረገ

Date:

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን አጠቃላይ እንቅስቃሴን የሚያሳይ ድረ ገጽ ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በለውጡ ማግስት ዳግም ባይወለድ ኖሮ፣ አዋራው ተራግፎ እንዲጸዳና እንዲያበራ ባይደረግ ኖሮ የወደመበት 34ኛ ዓመቱን እያሰበ ቤትዮጵያዊያን ልብ የሃዘን ቀኑ በሆነ ነበር። ጊዜ ደጉ አየር ኃይል 90ኛ ዓመቱን አንጸባርቆ ያሳልፋል። በሰጠው መረጃ መሰረት ከሆነ ተመንጥቋል።

አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ90ኛ ዓመት ምስረታው መጥቆ መሄዱን የሚያሳይ መረጃ ይፋ አደረገ። በ etaf90years.com ድረ-ገፅ አማካኝነት አጠቃላይ መረጃ ማግኘት እንደሚቻል ተቋሙ አስታወቀ። የምስረታ ቀን በዓሉ ላይ ኅብረተሰቡ እንዲሳተፍም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን በዓሉን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:-

ነሐሴ 12 ቀን 1921 ዓ.ም የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ቢሆንም አየር ኃይላችን እንደ ተቋም አደረጃጀት ይዞ በይፋ የተመሰረተው ሕዳር 20 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያዊው ሻለቃ ሚሽካ ባብቼፍ የአየር ኃይል አዛዥ ሆነው በተመደቡበት ቀን ነው፡፡

ጀግናው የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90 ዓመታትን ባስቆጠረው የምስረታ ታሪኩ በየዘመናቱ ሁሉ የሀገርን ሉዓላዊነት በመጠበቅ አኩሪ ታሪክ ያለው ስመ ገናና ተቋም ነው፡፡ አየር ኃይላችን የኢትዮጵያን የአየር ክልል በጀግንነት ከመጠበቅ ባሻገር በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች በመሰማራት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ አውለብልቧል፡፡

የሠላም አምባሳደርነቱንም በተግባር አሳይቷል፡፡ በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ ታሪክም አኑሯል፡፡ በስልጠናው ዘርፍም ከራሱ አልፎ የሌሎች ሀገራት የአየር ኃይል ሙያተኞችን አሰልጥኗል፡፡

90ኛ ዓመት የአየር ኃይል የምስረታ ቀን በዓል “የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት” በሚል ዋና መሪ ቃል ከጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድርስ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት ይከበራል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር የጀመረ ሲሆን የዚሁ አካል የሆነውና “ለአየር ኃይል እድገት በሙሉ አቅሜ እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል ሕዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በድምቀት ተካሂዷል፡፡

ይህ የሩጫ ውድድር ህብረተሰቡ በከፍተኛ መነቃቃት የተሳተፈበት፣ ተቋሙና ህዝቡ የተሳሰረበት፣ የቱሪስት መዳረሻ የሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ የተዋወቀችበት ከመሆኑም ባሻገር በቀጣይ ለሚካሄዱት ኩነቶች የአየር ኃይል የምስረታ ቀን ዋናው በዓል መሰረት ጥሎ ያለፈ ታሪካዊ ውድድር ነው፡፡

በመቀጠል ከጥር 15 እስከ ጥር 19 ዓ.ም ጀምሮ የሚኖረው የሚከተሉትን ኩነቶች የያዘ ነው የመጀመሪያው በዓይነቱ ለየት ያለ እና ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ አየር ኃይል አዘጋጅነት ‘የአንበሶች ሠማይ! ኢትዮጵያ’ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ኃይል፣ የሩሽያ የአየር ኃይል ትርኢት ቡድን፣ የሞሮኮ የአየር ኃይል እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይል በጋራ የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት 2026 በድምቀት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በመቀጠል በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀው “የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የቻይና፣ የህንድ የአሜሪካ እና የደቡብ አፍሪካ ታላላቅ ኩባንያዎች ብሎም ከ 25 በላይ የሚሆኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የአቪዬሽንና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ስታቲክ ዲስፕለይ እና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኤክስፖ2026 ይካሄዳል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን በዓል ከሚያከናውናቸው ኩነቶች አንዱ ከ38 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦች የሚሳተፉበት እና “የጋራ ስራዎቻችንን አጠናክረን የተረጋጋ ዓለም እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ ለ3ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ አየር ኃይል አዘጋጅነት ፊውቸር አፍሪካ አየር ኃይሎች ፎረም ታላላቅ የአቪዬሽን ባለሙያዎች በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ከአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ጋር ያላትን ቅርብ ትስስር በተግባር የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን በዓል ከሚካሄዱ መርሃ ግብሮች መካከል የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የጦር አዛዦች እንዲሁም የሀገራችን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት “ሀገርን በማገልገል የሚገኝን ክብር መዘከር” በሚል መሪ ቃል ከህብረተሰቡ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሕዝባዊ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን አጠቃላይ የበዓሉን የአከባበርን ሁኔታ የሚገልፅ እና የአየር ኃይልን ታሪክ የበለጠ የሚያሳውቅ፣ የዝግጅቱን ዝርዝር የሚያሳይ እንዲሁም የባለፉት ዓመታትን የተቋሙን የለውጥ ሂደት የሚያስቃኝና etaf90years.com የተሰኘ የኢቨንት ድረ ገፅ ያለው ሲሆን በዚሁ ድህረ ገፅ ሁሉንም የበዓሉ ኩነቶች ማግኘት የመግቢያ ቲኬት መግዛትና በድረ ገፅ ኩነቶቹን መከታተል ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ90 ዓመት ጉዞው ለኢትዮጵያችን መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በጀግንነት ጠብቋል ፡፡ ሀገር አፅንቷል፤ ሀገር አሻግሯል፡፡ በእሳት ተፈትነው ያለፉ ብዙ ጀግኖችንም አፍርቷል፡፡

የከበረ እና የገዘፈ ታሪክ ያለው የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ ቀን በዓሉን ሲያከብርም ያለፈውን ለመዘከር አሁናዊ የተቋሙን ቁመና ለማቀብ፣ የደረሰበትን ሁሉን አቀፍ ዝግጁነት ለማሳየት፣ የሀገራችንን ገጽታ በማጉላት እና የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ተስፋ ለማነሳሳት በሚያስችሉ ዝግጅቶች እንዲሁም ተግባራት የሚከበር መሆኑ ተመላክቷል።

ኅብረተሰቡ በዓሉ ላይ እንዲገኝና በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ያገለገሉትንና እያገለገሉ ያሉ ጀግኖችን እንዲያከብር፣ እንዲዘክር፣ የሀገር መመኪያና ኩራት የሆነው ተቋም እንዲመለከትና በዚህ አስደናቂና ታሪካዊ በዓል ላይ እንዲታደም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...