አዲስ ሪፖርተር – ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ሕዝብ አመጽ እንዲያቀጣጥል ጥሪ ለማቅረብ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ጃዋር መሐመድ በድጋሚ ቀጠሮውን የሰረዘው በአስቸኳይ ግብጽ የሚያስጄደው ጉዳይ አጋጥሞት እንደሆነ ታወቀ። ይህንኑ ለማጥራት የአዲስ ሪፖርተር የአውሮፓ ተባባሪ በግል የእጅ ስልኩ ላቀረበለት ጥያቄ “አያገባችሁም” ብሏል።
በአብሮነት ሰብሳቢ አቶ ልደቱ አማካይነት በኢትዮጵያ አመጽ ለማቀጣጠል በተቋቋመው ግብርሃይል ውስጥ ካሉት ሰባት አባላት አንዱ ሆኖ የተመረጠው ጃዋር ስብሰባ አይገኝም ነበር። በዚሁ ሳቢያ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገ ስብሰባ “ለምን ከጀርባ ሆኖ ይሰራል” በሚል ቅሬታ ቀርቦበት ነበር።
አዲስ ሪፓርተር ከዲሲ የደረሳት መረጃ አጣቅሳ ከሁለት ሳምንት በፊት ዓርብ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ ወደ ማክሰኞ መተላለፉን አስታውቃ ነበር። ይሁን እንጂ ጃዋር መሐመድ በድጋሚ በማክሰኞው ስብሰባ ያልተገኘው ፊት ለፊት ለመታየት ባለመፈለጉ፣ ይህም የኦሮሞ ማህበረሰብን በመፍራቱ ሳቢያ የተፈጠረ በመሆኑ በግብረኃይሉ አባላት መካከል ክርከር አስነስቶ ነበር። በዚሁ የተነሳ ጃዋር እንዲገኝ እንደሚደረግ ቃል ተገብቶ ስብሰባው ከማክሰኞ ወደ ሃሙስ ተላለፈ።
ከሁለት ሳምንት በፊት ማክሰኞ በተደረገው ስብሰባ “እናንት ከግብጽ ገንዘብ ትወስዳላችሁ። እኛ የለንበትም። ጃዋር ለምን በጓሮ ሆኖ ይሰራል። የግብረኃይሉ አባል እስከሆነ ድረስ በፊት ለፊት መግለጫው ላይ ሊገኝ ይገባዋል” በሚል ተቃውሞ ተነሳበት። አዲስ ሪፖርተር ከተሰብሳቢዎቹ ባገኘቸው መረጃ “እኛን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ በማየት መጠቀም ይቁም” ሲሉ የአነስተኛ ክልል ተወካዮች ባሰሙት ቅሬታ መሰረት ቅሬታ መሰረት ጃዋርን በማነጋገር ሃሙስ ሌላ ስብሰባ ለማድረግ ቀጠሮ ተያዞ ነበር። እዚህ ላይ ዝርዝሩን ያንብቡ፤
በቀጠሮው መሰረት ጃዋር ሃሙስ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ፣ አቶ ልደቱ ያዘጋጀውን መግለጫ “እኔ በንግሊዝኛ አዘጋጀዋለሁ” ካለ በሁዋላ ለማክሰኞ በተያዘው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ ልደቱ የሚያነቡትን የዕለቱን የአመጽ ጥሪ ተንተርሶ ማብራሪያ እንደሚሰጥ አስታውቆ “ጉዞ አለብኝ” በማለት ከስብሰባው ወዲያው መሰናበቱን አመልክተን ነበር። በዚሁ 30 ደቂቃ በፈጀ ስብሰባ ጃዋር አምስት ደቂቃ ብቻ ቆይቶ ጥያቄ ሲቀርበለት መልስ ሳይሰጥ የተሰናበተው ጃዋር በድጋሚ ባለው ቀን ማለትም ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተብለውን የአምጽ ጥሪ ሳያቀርብ ቀረ።
አዲስ ሪፖርተር ባገኘቸው መረጃ ጃዋር “የውጭ ጉዞ አለብኝ” ያለው ወደ ግብጽ እንዲሄድ አስቸኳይ ጥሪ ደርሶት ነው። “ኢትዮጵያ ለምን የደቡብ ሱዳንና፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን ትረዳለች” በማለት ሲከራከር “የግብጽ ኤጀንትነቱን በይፋ አወጀ” የተባለው ጃዋር ወደ ግብጽ ያቀናበትን ልዩ ምክንያት ዜናውን ያጋሩት ወገኖች አላብራሩም። ነገር ግን የተለመደው የፋይናንስ ጉዳይና መመሪያ የመቀበል ጉዳይ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ እንዲበተን ዕቅድ ባወጣው አዲስ የሹመት ድልድል ውስጥ ቁልፍ ቦታ ከተሰጣቸው መካከል አንዱ እንደሆነ መስማታቸውን የገለጹት የመረጃው ምንጮች፣ ኦሮሚያ ክልል ሰላም በመሆኑ ረብሻ እንዲነሳ ኃላፊነት መውሰዱን ጠቁመዋል።
ጃዋር በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወለጋ መሂዳቸውን ተከትሎ “የብሄርና የሃይማኖት ግጭት ሊነሳ ይችላል” በማለት በግል የማህበራዊ ገጹ ላይ ማስታውቁ አይዘነጋም። በዚሁ ጽሁፉ በኢትዮጵያ ያለው የኦሮሞ መንግስት ስለሆነ ኦሮሞ የሆኑ ሁሉ ከዚህ መንግስት ጋር መተባበራቸው ሌላ መንግስት ሲመጣ አደጋ እንደሚሆንባቸው አመልክቶ ነበር። ይህንን አባባሉን በመቃወም “ድርጊቱ የኦሮሞን ሕዝብ ለይቶ ለጅምላ ጭፍጨፋ አሳልፎ የመስጠት ያህል ነው” በማለት ማብራሪያ የጠየቁት ነበሩ።
ጃዋር ይህን ባለ በማግስቱ በአርሲና በሌሎች አካባቢዎች ንብረት ወደመ፣ ህይወት አለፈ በሚል በግል ማህበራዊ ገጹ መንግስት እየወነጀለ መረጃ ሲያሰራጭ እንደነበር ይታወሳል። ጃዋር ሁለት ቀን ስለቆየበት የካይሮ ጉዞው የአዲስ ሪፖርተር የአውሮፓ ተባባሪ በግል ስልኩ ደውሎለት “አያገባችሁም” በማለት ስልኩን ዘገቷል። ድጋሚ ሲደወል አልመለሰም።
የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ከአሜሪካ በላከው መረጃ አሁን ላይ ጃዋርና አቶ ነዓምን ዘለቀ ከወትሮው በተለየ አብረው እየሰሩ መሆኑን አመልክቷል። አቶ ነዓምን የሻዕቢያ ወኪል በመሆን በኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈርስ ሚዲያና ሚዲያዎች ላይ የሚቀርቡ እንግዶችን ከአጀንዳ ጋር በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት የሚያመቻቹ መሆናቸውን ተባባሪያችን በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።
ጃዋር የሚመራው ኦኤምኤን የተሰኘው ሚዲያ ተቅማጭነቱ ግብጽ እንደነበርና የሚሰራጨውም ንብረትነቱ የግብጽ በሆነው ናይል ሳት በነጻ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






