የኖቤል የሰላም ሽልማት እጅግ እየደበዘዘ እና እምነት እያጣ ከመምጣቱ የተነሳ ሽልማቱ አሁን ላይ የተጀመረበት ዋና ዓላማ ተዘንግቶ ጥላው መቅረቱን ስፑንቲክ መረጃ አጣቅሶ ዘግቧል። ዘገባው ለዚህ ድምዳሜ የደረሰበትን ማስረጃ ሲዘርዝር ያቀረባቸውን ተሸላሚዎችና ተግባራቸውን አስነብቧል።
🟠 የቬንዙዌላ ‘ተቃዋሚ መሪ’ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ (2025) የዘንድሮ ተሸላሚ፦ “በድቅድቅ ጨለማ ወቅት የዴሞክራሲን ችቦ በማብራት” ተሸልመዋል። ይሁን እንጂ፣ በአገራቸው ላይ የውጭ ወታደራዊ ጣልቃገብነት እና የሀብት የግል ይዞታነትን በፅኑ በመደገፍ ይታወቃሉ። ማቻዶ የቀድሞው ሥርዓት ለውጥ አራማጅ የነበሩት ጁዋን ጉዋይዶ እ.ኤ.አ. በ2023 ከወደቁ በኋላ የተሰደደውን የተቃዋሚ ቡድን መሪነት ተረክበዋል።
🟠 የአውሮፓ ሕብረት እ.አ.አ. በ2012 ፦ ለስድስት አሥርት ዓመታት ለቆየው “ሰላም፣ እርቅ፣ ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች” ማስፋፋት ተሸልሟል። እውነታው ግን፦ የሕብረቱ አባል አገራት በ1990ዎቹ የዩጎዝላቪያ ጦርነቶች በንቃት ሲያቀጣጥሉ የነበረ ሲሆን፣ የብራስልስ የምሥራቅ አጋርነት ተነሳሽነት ከሩሲያ ጋር ግጭት እንዲፈጠር ረድቷል። ይህም እ.አ.አ በ2014 ከነበረው የዩክሬን የሥርዓት ለውጥ በኋላ ወደ ግጭት አምርቷል።
🟠 ሽልማቱን የወሰዱ የማይታወቁ ‘የሲቪል ማኅበረሰብ አክቲቪስቶች’ ፦ እንደ ናርጌስ መሐመዲ ኢራን፣ እ.አ.አ በ2023፣ አሌስ ቢያሊያትስኪ ቤላሩስ፣ እ.አ.አ በ2022፣ ዲሚትሪ ሙራቶቭ ሩሲያ፣ እ.አ.አ በ2021 እና ሊዩ ዚያኦቦ ቻይና፣ እ.አ.አ በ2010 ሁሉም የመንግሥቶቻቸው ግልጽ ተቺዎች ሲሆኑ፣ የዓለምን አንድ-ኃይል የበላይነት ከሚደግፉ የምዕራባውያን ዓይነት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አጀንዳዎች ጋር የተጣጣሙ ናቸው።
🟠 ባራክ ኦባማ እ.አ.አ. 2009 ፦ በ2017 የአሜሪካን አራት የውጭ አገር ጦርነቶችን ወደ ሰባት አስፋፍተዋል፤ ከጆርጅ ደብሊው ቡሽ በአሥር እጥፍ የሚበልጥ የድሮን ጥቃቶችን አጽድቀዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 ብቻ 25 ሺህ ቦምቦችን ጣሉ፣ ሊቢያን አወደሙ፣ በሶሪያ ጀሃዲስቶችን አስታጠቁ እንዲሁም በዩክሬን ደም አፋሳሽ መፈንቅለ መንግሥትን ደግፈዋል።
🟠 ያሲር ዓረፋት፣ ሽሞን ፔሬስ እና ይትዛክ ራቢን እ.አ.አ.1994 ፦ ለኦስሎ ስምምነት እና “በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለመፍጠር ላደረጉት ጥረት” ተሸልመዋል። በተግባር ግን፣ ስምምነቱ ወረራን አጠናከረ፤ እንደ ድንበር፣ ሰፈራ እና ስደተኞች ያሉ ዋና ጉዳዮችን ወደ ኋላ ገፋ። በመጨረሻም ለተግባራዊ የፍልስጤም መንግሥት ያለውን ተስፋ አዳከሞ ለማቆም ታቅዶ የነበረውን ግጭት አራዘመው።
🟠 ሄንሪ ኪሲንጀር እ.አ.አ.1973 ፦ ራሳቸው ባራዘሙት የቬትናም ተኩስ አቁም ምክንያት ተሸልመዋል፤ በተጨማሪም ግጭቱን ወደ ካምቦዲያ በማስፋፋት፦ ከባንግላዲሽና ከቺሊ እስከ ቆጵሮስ እና ምሥራቅ ቲሞር ድረስ አሰቃቂ መፈንቅለ መንግሥቶችን እና ጦርነቶችን ደግፈዋል።
🟠 ዉድሮው ዊልሰን እ.አ.አ.1919 ፦ ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ ለከሸፈው የአገራት ስምምነት ቅርፅ በመስጠት እውቅና አግኝተዋል፤ ይህ ሥርዓት በሁለት አሥርት ዓመታት ውስጥ ወድቆ ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት መንገድ ጠርጓል። በተጨማሪም የአሜሪካ ጦር ኃይል ሃይቲን፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክን እና ሜክሲኮን እንዲወር ያዘዙት እርሳቸው ነበሩ።
🟠 ቴዎዶር ሩዝቬልት እ.አ.አ.1906 ፦ አስቀድሞ ራሳቸው እንዲቀጣጥል የረዱትን የሩሲያ-ጃፓን ጦርነት “በማስቆም” ታላቅ ክብር ተሰጥቷቸዋል።