አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | የሰነዓፌ ንዑስ ዞን ከተማዋንና በዙሪያዋ ያሉትን መቶ የሚጠጉ የገጠር ቀበሌዎች አሏት። ለህወሃት አዲስ መጠለያ እንድትሆን የተመረጠችው እና በደቡባዊ ኤርትራ ከዛላምበሳ ድንበር ማዶ የምትገኘው ይህቺ ከተማ በቁስለኛ መጨናነቋን በስልክ ይፋ ያደረጉ እንደሚሉት ከተማዋ መራወጥ የበዛባት፣ ረፍት ያጣች፣ ስጋት የዋጣት ሆናለች።
የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በጋራ እያካሄዱት ባለው ፈጣን የማጥቃት እና በድሮን የታገዘ ጦርነት፣ አሁን ዛላንበሳን ለመቆጣጠር ጫፍ እንደደረሱ ከየአቅጣጫው መረጃዎች እየወጡ ነው። ዛላንበሳ የመጨረሻዋ የሁለቱ አገራት ድንበር በመሆኗ ቀጥላ ያለችው ሰንዓፌ “ሙሽራዋን እየጠበቀች ነው” እያሉ የሚናገሩም አሉ።
አዲግራትን በቁጥትራቸው ስር ካደረጉ በኋላ በአምስት ኪሎሜትር ላይ የምትገኘውን ፋጺን የከበቡት የአገር መከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ከፋጺ በኋላ ያለው አካባቢ ለረዥም ዓመታት በሻዕቢያ እጅ በመቆየታቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ማጥቃት እንደሚያደርጉ እየተሰማ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ ነው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አገዛዝን የክተት ጥሪ በመሸሸ ወደ በረሃ ያቀኑ የቀድሞ ወታደሮችና የግድጃ ውትድርና ሰልጣኞችን ጠቅሰው ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ ያደረሱ የለውጥ ኃይሎች “የኢሳያስ አገዛዝ ተስፋ እየቆረጠ በመሆኑ ‘ለወንበሬ ታሰጋላቹህ’ በማለት ያሰራቸውን ከፍተኛ መኮንኖች እና የውጊያ ባለሙያዎችን እየፈታ መሆኑን ያስታወቁት።
ከእነዚህ ወገኖች በተጨማሪ አስመራ ለተቀመጡ ዓለም ዓቀፍ ዲፕሎማቶች እና ኤምባሲዎች “ከኢትዮጵያ ድንበር ወጥተናል፣ የያዝነው ቦታ የለም። ኢትዮጵያ ልትወረን ምክንያት ነው የመትፈልገው” በማለት የኢሳያስ አገዛዝ እየወተወተ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። ከተባበሩት መንግስታት ከተጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ ዲፕሎማቶችን እየወተወተ ያለው ሻዕቢያ ጎን ለጎን እስከ ሰባ ዓመት ያላቸውን ወንዶች እና እስከ ሃምሳ ዓመት የሚሆኑ ሴቶችን መሳሪያ እያስታጠቀ ወደ ግንባር በመላክ ላይ ነው።
የአገር መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ሩጫ
የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና ከተማ እንዳስላሰ ሽረ ተቆጣጥረው የነበሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም ሰለኽለኻ የተባለችው ወሳኝና የዞኑን የመጨረሻ ከተማ ተቆጣጥረው ከአክሱም 20 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ውቕሮ ማራይ ተጠግተው ነጻ አውጧት።
መስከረም 30/ 2019 ዓ/ም የዓዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩ በኋላ ታሪካዊቷን እና ከአክሱም በ15 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን የዓድዋ ከተማ በእጃቸው አስገቡ። አክሱም ከተማ ብዙም ሳይቆይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ሰላም ኃይል ቁጥጥር ስር እንደሚወድቁ እየተዘመረ ግስገሳው ቀጠለ።
የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ለግማሽ ምዕተ ዓመት ሲሰበክ የነበረውን የሃሰት ትርክት ሰብሮ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ባንዲራዋን ከፍ አድርጎ በማሳየት አቀባበል ሲያደረጉ ያዩ “ኢትዮጵያ በዳግም ውልደት ላይ” ሲሉ በጽንፈኞችና ሴረኛ ዘረኞች ሞት ላይ አፈር መመለሱን በድፍረት አስታወቁ።
የአገር መከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች አመጣጥ እና በትር የፈጠረው ድንጋጤ እየደረሰባቸው ያሉ ህይወታቸውን ለማትረፍ ከአክሱም እየሸሹ መሆኑ ሲነገር፣ ጎን ለጎን የድሮን ጥቃት በተመረጡ አካባቢዎች ላይ መፈጸሙ በተደጋጋሚ ይሰማ ነበውር። እየቀደመ ጉዳት የሚያደርሠው የድሮን ጥቃት፣ ከተለያዩ አከባቢዎች አክሱም ተሰባስበው የነበሩ የህወሓት አመራሮችን እያከለፈለፈ ወደ ሰነዓፌ ነዳቸው። ነዋሪዎች እንዳረጋገጡት የባለስልጣናቱ ሩጫ አስገራሚ ነበር። ልክ መቀለ እናል ሌሎች ከተሞች እንደሆነው የህወሃት አመራሮች እስር ቤት በርግደው ወነጀለኞችን ፈቱ። ህዝብ ራሱን አደራጅቶ ከተማውን ከዘራፊዎች መጠበቅ ላይ እየጠበቀ “ግባ በለው” በሚል መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎችን ሲጠብቅ አመሸ።
የኤርትራ ወታደሮች በምስራቃዊና ምዕራባዊ የትግራይ ዞኖች ይዘዋቸው ከነበሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች እየለቀቁ ፈረጠጡ። እንደሆነ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዶይቼ እንዳለው የሻዕቢያ ወታደሮች፣ ከዚህ ቀደም ይንቀሳቀሱባቸው ከነበሩት ዛግር፣ ዝባን ገደና፣ ሽመልባ፣ ዓዲሃገራይና ዓዲ አውዓላ ከተባሉ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ አሁንም የኤርትራ ወታደሮች በጓል ባድመ እና ሸራሮ አካባቢ እንደሚገኙ ውር ውር እያሉ መመሪያ እንደሚጠብቁ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የኤርትራ ሰራዊት ከአካባቢው የለቀቁት የፌደራል የመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ሃይል እንዳስላሰ ሽረን ጨምሮ በአካባቢው በቅርብ ርቀት የሚገኙ ቦታዎችን በመቆጣጠራቸውና በተፈጸሙ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃቶች እንደሆነ ነዋሪዎች መስክረዋል። የተፈጸመውን ኦፕሬሽን አስመልክቶ የወጡ የፎቶና የቪዲዮ መረጃዎች የሻዕቢያ ኃይል በሽሽት ላይ እያለ መጠነ ሰፊ የቁስና ሰብአዊ ቀውስ ደርሶበታል።
በዓዲግራት የሚገኙ የአይን እማኝ ደግሞ ከዕዳጋ ሐሙስ የተመለሱ የኤርትራ ወታደሮች ከዓዲግራት ከተማ 5 ኪ/ሜ ርቃ ወደምትገኘው ፋጺ ተሰባስበው የነበረ ቢሆንም ትላንት ማምሻውን ከአካባቢው እንደወጡ ተናግረዋል።
ባለፉት 3 ቀናት ከፋጺ እስከ ዛላምበሳ በተዘረጋው የኤርትራ ወታደሮች የሰፈሩባቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ብርቱ የድሮን ድብደባ እንደነበር ተገልጿል።
በተለይ በዛላምበሳ ከተማ በተፈጸመው ድብደባ መሳሪያ የጫኑ መኪኖች በመመታታቸው ጥይቶቹ ሲቃጠሉ ከባድ ፍንዳታዎች ይሰሙ እንደነበረም እማኞች መስክረዋል። የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎች ይህንኑ የሚያረጋግጡ ሆነዋል።
የተማረኩ ትጥቆች ከነሰነዶቻቸው ለአምባሳደሮች ቀረቡ!
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሠራዊቱ የተማረኩ ዘመናዊ የጦር ትጥቆች፣ የመገናኛ መሣሪያዎችና መሣሪያዎቹ ወደ ታጣቂዎች እጅ የገቡበትን መንገድ የሚያሳዩ የሽያጭና የትራንስፖርት ሰነዶች በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ሰኞ ዕለት በጦር ኃይሎች ዋና መሥሪያ ቤት መቅረባቸውን መሃል ሚዲያ ዘገበ።
በተለይም በመቀሌ ከታጣቂዎች መጋዘን የተገኙ የመገናኛ መሣሪያዎች ከነባርኮዳቸው የቀረቡ ሲሆን፤ መሣሪያዎቹ የተሠሩበትን ሀገር፣ የገዛቸውን አካልና የተጓጓዙበትን መስመር የሚያሳዩ ሰነዶች ለዲፕሎማቶቹ ታይተዋል።
በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና በጄኔራል ገመቹ የተመራው ይህ መርሐ ግብር፣ በቀጣይ በቢሾፍቱና በመቀሌ የሚገኙ ሌሎች መጋዘኖችን በመጎብኘት እንደሚቀጥል ተገልጿል። መድረኩ የተማረከ መሣሪያ ከማሳየት ባለፈ፣ ከታጣቂዎቹ ጀርባ ያሉ አቅርቦት አቅራቢዎችን ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በማስረጃ የማስመርመር ዓላማ እንዳለው ተመልክቷል።
ተስፋ
የትግራይ የለውጥ ኃይሎች ኤርትራ በተስፋ ወጋገን ውስጥ መሆኗን እየተናገሩ ነው። ዝርዝር ባይገልጹም ተስፋ ከፊት እንዳለ አፋቸውን ሞልተው ይናገራሉ። ሻዕቢያ በሚስጢር እስር ቤቶች ያጎራቸውን እየፈታ ወደ ጦርነት በመላክ የሚለውጠው ነገር እንደሌላ ይግልጻሉ።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






