በትግራይ ለፓለቲካ ጥቅም ሲባል ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም የሚጠይቁ ስልፎች ተካሂደዋል።
በትግራይ ክልል ትህነግ ከኤርትራ መንግስትና ፋኖ ጋር በመጣመር ለጦርነት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑ በየአቅጣጫው እየተሰማ ባለበት፣ የትህነግ አመራሮች፣ የትህነግና የሻዕቢያ ልሳን ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ይህንኑ አይቀሬ የሚሉት ጦርነት እንደሚጀመር ምልክት እየሰጡ ባለበት ወቅት የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ያደራጁትና የመሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ እያነጋገረ ነው።
ትናንት የተጀመረውና ዛሬ የቀጠለው የሰላማዊ ሰልፍ፣ ከመኖሪያ መንደራቸው የተፈናቀሉና በመጠላይ ጣቢያዎች በከፋ ችግር እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም፣ እነዚህን ወገኖች ለፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያነት መጠቀም እንዲያበቃ በገሃድ መጠየቁን ሰልፉን የተከታተሉ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪዎች አመልክተዋል። ትህነግ ተፈናቃዬች ተመልሰው ወደ መንደራቸው እንዲገቡ እንደማይፈቅድ በገሃድ መናገሩ አይዘነጋም። መጀመሪያ ትህነግ አካባቢውን ያስተዳድር የሚል አቋም ነው ያለው።
በትናንትናው ዕለት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ውጤት ለህዝብ ሳይገለጽ፣ ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከምስራቅ አቅጣጫ ወደ መቀለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አውራ ጎዳና ከማለዳ ጀምሮ መዘጋቱ ታውቋል። ታጣቂ ኃይሎቹ ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት አቅጣጫዎች መንገዶቹን በመዝጋታቸው የተነሳ የትራፊክ መስተጓጎል መፈጠሩን ከስፍራው የወጡ ምስሎች አረጋግጠዋል። በስፍራው የሚገኙትን በማነጋጋር የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ አረጋግጧል። መንገዶቹ ስለመከፈታቸው ግን ማረጋገጫ አላገኘም።
ሰለፈኞቹ “በትግራይ ክልል ጦርነትና ግጭት መካሄዱን ተከትሎ ከቀዬቸው የተፈናቀሉ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየደረሰባቸው ያለውን በደልና መከራ በቂ ምላሽ እየተሰጠው አይደለም” ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሰልፍ ለማድረግ ያነሳሳቸው ችግራቸውን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት በቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደሆነ አመልክተዋል።
የተቃውሞውን ሰልፍ ያካሄዱት በአመዛኙ የትግራይ ሰራዊት ኃይል በምህፃሩ TDF በሚል ራሳቸውን የሚጠሩና በቀደሙት ዓመታት በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ዋና ተሳታፊ የነበሩ ናቸው። በሰልፉ ላይ እንደታየው ትጥቅ አንግበውም ነበር።
ሰልፈኞቹ፣ ከፕሪቶርያ ስምምነት በኃላ ትጥቃቸውን ፈትተው በተዘጋጀላቸው ማቆያ እንዲሰፍሩ ከተደረገ በኃላ በርካታ ጥያቄዎች ሲያነሱ መቆየታቸውን የሚታወስ ሲኾን ችግሮቻቸውን ለቀድሞ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አቅርበው እንደነበር አይዘነጋም።
ይሁንና ቃል የተገቡላቸው የካሳና ጥቅማጥቅም ጉዳዮች እንዲኹም ተያያዥ ጥያቄዎች እልባት አልተሰጣቸውም በሚል በመቀለ ከተማ አጠር ላሉ ሰዓታት የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል።
በከተማዋ የተሰማውና በሰልፉ ላይ ከቀረቡ አንገብጋቢ ናቸው ካሏቸው ርእሰ ጉዳዮች መካከል ተፈናቃዮች ተገቢውን መልስ እንዳልተሰጣቸው የሚገልፁና ለፓለቲካ ዓላማ ሲባል የሚከፈለውን አላስፈላጊ ዋጋ ከወዲኹ እንዲገታ የሚጠይቁ መሆናቸውን ታውቋል።
የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ትህነግ፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል እየሰፋ የሄደው መካረር ወደ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል። ትግራይ ዳግም የጦርነት ማዕከል እንዳትሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ቆም ብለው እንዲያስቡ ጠይቀዋል።
ትህነግና ሻዕቢያ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሰበብ ወታደራዊ ጥምረት መፍጠራቸው፣ ሰሞኑን በተጠናቀቀው ኮንፍረንስ ላይ ኤርትራ መሳሪያ እንደሰጠቻቸው ራሳቸው የትህነግ መሪዎች መናገራቸው የሚታወስ ነው።
በመቀለ ከተማ የተካሄደው ይኸው ሰልፍ ሙሉ በሙሉ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ፍራቻ መኖሩን ከማስታወቁ በተጨማሪ፣ ትግራይን ወደ ሰላም እንድትመለስ ማሳሰቢያ የተላለፈበት ነው። ይህንኑ ፍላጎታቸውን “ሰላምን እንሻለን” በሚል ድምጽ ሰልፈኛቹ በተደጋጋሚ ሲያጸኑ ተሰምተዋል።
በተጨማሪም፣ በክልሉ በነበረው ጦርነት በትጥቅ ትግል የተሳተፉ እነዚሁ የትግራይ ታጣቂ ኃይል አባላት “የኛን ጥያቄ መመለስ የማይችል አመራር የሌላውን ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ አይችልም” በማለት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ በሚመሩት ጊዜያዊ የክልሉ መስተዳድር ላይ ቅሬታ አሰምተዋል።
በሰልፉ ላይ የትግራይ ኃይል አባላት በመቀለ ከተማ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ሲኾን የተለያዩ የመብት ጥያቄዎች እንዲሁም ለተፈናቃዮች እየተሰጠ ያለውን ትኩረት በቂ አለመኾኑን የሚያወግዙ ሐሳቦች አንፀባርቀዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መፈክሮችን እያሰሙ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ፅህፈት በማምራት የክልሉን ጊዜያዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት ለማነጋገር ፈልገው ነበር። ይሁንና የጊዜያዊ መስተዳድሩ ፕሬዚዳንት ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።
በወቅቱ ጥያቄያቸው ስምቶ መልስ የሚሰጥ የጊዜያዊ መስተዳድሩ ሐላፊዎች በማጣታቸው የተቆጡት ሰልፈኛቹ ከቀኑ 7:00 እስከ 11:00 ባሉ ሰአታት የከተማው አውራ መንገድ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋናው መንገድ በድንጋይ ዘግተውት መዋላቸውን ተገልጿል።
የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ዋናው መንገድ መዝጋታቸውን ከተሰማ በኃላ ከጊዚያዊ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች ሰልፈኞቹን ለማነጋገር ፍቃደኛ በመሆናቸው እንዲሁም ለውይይት መቀመጣቸውን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው መንገድ መከፈቱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ።
ዘግይቶ የተሰማው ዜና እንደሚያመለክተው ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ የትህነግና የሰራዊት አዛዦች ናቸው ከተባሉና በስም ካተዘረዘሩ ጋር ተነጋግረዋል። በውይይቱ ማጠናቀቂያ ምን አቋም እንደተያዘ በይፋ ባይነገርም፣ ለቀረበው የኢኮኖሚና የቁሳቁስ ጥያቄ “ አቅም ስለሌለን ነው፣ ወደፊት እናሟላለን” የሚል ምላሽ መሰትቱን አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች።
ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው መሆኑ በተነገረለት አንድ ቪድዮ እንደተሰማው ከሆነ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የድጎማ፣ የጥቅማጥቅምና የመኖሪያ ቤት የመስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከአቅሙ በላይ ሰፊ የወታደር ኃይል አሰባስቦ የክልሉን በጀት በአብዛኛው ለወታደር ደሞዝ የሚያውለው የትግራይ አስተዳደር አሁን ላይ የተነሳበት የደሞዝ ጭማሪ፣ የመለያ ልብስና ጫማ ጥያቄ ለመመለስ እንደማይችል አስቀድሞ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።
የትህነግ የንግድ ድርጅት የሆነውን ኤፈርትን ቦርዱን በማፍረስ በአዲስ የሰየመው ትህነግ፣ የንግድ ድርጅቱ በሚያስገባው ገቢው የታጣቂዎቹን ደሞዝ እንደሚጨምር ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰላማዊ ሰልፉ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ላይ ማነጣጠሩን የሚጠቁሙ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ነው። በሳቸው ምትክ ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን ጥምረት ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑትን የትህነግ ምክትል ሊቀመንበር ኣማኑኤል አሰፋን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕፕሬዝዳት የማድረግ ዕቅድ እንዳለ ተሰምቷል።
በመቀለ ሃውልቲ አዳራሹ ከሌተናል ጀኔራል ታደሰ ጋር የተሰበሰቡት ሰልፈኞች ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣናቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ይሁን እንጂ ይህ ዜና ከድርጅቱ በይፋ አልተሰማም።
ስምንት መሰረታዊ ጉዳዮችን ለመፈጸም ቃል ገብተው በፌደራል መንግስቱ የተሾሙት ታደስ ወረደ፣ በዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን አንጃ ጋር ቅንጅት በመፍጠራቸው ቢነቀፉም፣ ሻዕቢያ እንዳልወደዳቸው አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እያስታወቁ ነው።
ሰሞኑን ከመንግስት ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን፣ በፕሪቶሪያው የሰላም አማራጭ ስምምነት መሰረት ተቋቁሞ የነበረውን ጊዜያዊ አስተዳደር በሴራና፣ ወታደራዊ ኃይል በመጠቀም ያፈረሱ መሆናቸውን ጠቅሰው ከሰዋቸው ነበር። በትግራይ ለውጥ ለማምጣት የጋራ ካውንስል ያቋቋሙት አራት ፓርቲዎችና ሶስት ተሰሚነት አላቸው የሚባል ወገኖች ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከስላጣን እንዲወርዱ ቀዳሚ ፍላጎታቸው እንደሆነም አክለው ገልጸው ነበር።
- የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱበምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን አገር ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያችላቸውን መስፈርት ለማሟላት በሒደት ላይ ናቸው። በመከላከያ ተማርከው ወደ አዲስ አበባ እስከመጡበት ጊዜ ድረስ የቀድሞ የትህነግ አዋጊ… Read more: የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ
- ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ አቋም አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል። ትህነግ ባዘጋጀው ኮንፍረስን ላይ መንግስትን ለመጣል በቂ ትጥቅና ኃይል እንዲሁም አጋዦች እንዳሉ ባስታወቁ ማግስት ከጠቅላይ… Read more: ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”
- የትግራይ ሰላማዊ ሰልፎችና የታደሰ ወረደ ዕጣ ፈንታ እያነጋገረ ነው፤ “ሰላም እንሻለን” ታጣቂዎችበትግራይ ለፓለቲካ ጥቅም ሲባል ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም የሚጠይቁ ስልፎች ተካሂደዋል። በትግራይ ክልል ትህነግ ከኤርትራ መንግስትና ፋኖ ጋር በመጣመር ለጦርነት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑ በየአቅጣጫው እየተሰማ ባለበት፣ የትህነግ አመራሮች፣… Read more: የትግራይ ሰላማዊ ሰልፎችና የታደሰ ወረደ ዕጣ ፈንታ እያነጋገረ ነው፤ “ሰላም እንሻለን” ታጣቂዎች
- የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና የአገር መከላከያ ሰራዊት አሁናዊ ፈተና – እንደ አሜሪካ ልጓም አሁኑኑ!!Addisreporter – የአሜሪካ ጦር ሰራዊት መስሪያ ቤት (Department of War) ማህበራዊ ሚድያን መሰረት ያደረገ የስጋት ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል እና በወታደራዊ ዲሲፕሊን ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ ጥብቅ የሆነ የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም መመሪያ… Read more: የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና የአገር መከላከያ ሰራዊት አሁናዊ ፈተና – እንደ አሜሪካ ልጓም አሁኑኑ!!
- በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ የኮሪደር ልማት አይከናወንም፤ የቤት ግንባታ፣ መንገድና ውሃ ቅድሚያ ይይዛሉየአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት ዓመቱ አዲስ የምንጀምረው የኮሪዶር ልማት ፕሮጀክት እንደማይኖር አስታወቁ፤ ወደፊት አዲስ ጥናት እንደሚደረግና ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አመልክተዋል። የበጀት ዓመቱ ትልቁ ትኩረት… Read more: በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ የኮሪደር ልማት አይከናወንም፤ የቤት ግንባታ፣ መንገድና ውሃ ቅድሚያ ይይዛሉ