የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ

Date:

በምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን አገር ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያችላቸውን መስፈርት ለማሟላት በሒደት ላይ ናቸው። በመከላከያ ተማርከው ወደ አዲስ አበባ እስከመጡበት ጊዜ ድረስ የቀድሞ የትህነግ አዋጊ የነበሩት እኚሁ ታጋይ፣ በአሜሪካ ጥገኝነት ለማግኘት የሚያበቃቸውን ሰነድ አሟልተው ቃለመጠይቅ እንዲያደርጉ ለቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞላቸው እንደነበር እሳቸውን የሚመለከተው መረጃ ያስረዳል።

ዶክተር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካ ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያስችል ሰነድ እንዲያዘጋጁ መልዕክት እንደተላከላቸውና ቀደም ሲል በጀመሩት ሒደት መሰረት በአሜሪካ የሕክምና ማዕከል ( American Medical Center) ሰነዶች ማስገባታቸው ታውቋል።

ዶክተር አብርሃም ተከስተ በትህነግ ከፍተኛ አመራር መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ፓርቲያቸው ትህነግ በአገር መከላከያ ላይ በክህደት በጀምረው ጥቃትና ወደ አማራና አፋር ክልል ተደርጎ በነበረው ወረራ ተሳታፊ እንደነበሩ በወቅቱ ያሳዩት የነበረው ተሳትፎ ምስክር ነው።

ትግራይ ተጀምሮ ወደ አፋርና አማራ ክልል በተዛመተው ጦርነት ወቅት አመራር የነበሩት ዶክተር አብረሃም፣ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች እልቂት ተጠያቂ አድርገው የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከትህነግ ከትህነግ ባስልጣናት ጋር አንድ ላይ ይከሷቸዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት እሳቸውንና ሌሎች ባልደረቦቻቸውን ከተመሸጉበት ምሽግ በመያስዝ ጥር 3 ቀን 22013 ዓ.ም አዲስ ወህኒ መግባታቸውና ስምምነቱን ተከትሎ በምህረት መለቀቃቸው ይታወሳል።

የአሜሪካ መንግስት በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮች ከአገር እንዳይወጡ ክልከላ ተጥሎባቸው እንደነበር የሚታወቅ ቢሆንም ባገኘነው መረጃ እንሚያመላክተው ዶክተር አብርሃም ተከስተ ጥገኝነት ለማግኘት የሚያስችለው ሒደት አልፈዋል።

አሁን ላይ በተገኘው መረጃ መሰረት ጥገኝነት ለማግኘት የሚያስችል ክትትል (Asylum Follow-to-Join) እያዘጋጀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ጥገኛን ከቤተሰብ የሚያገናኝ ፕሮሰስ ወይም Asylum “follow-to-join” ማለት አሜሪካ ለጥገኝነት የገባው ለራሱ መጀመሪያ ጥገኝነት ጠይቆ ከተፈቀደለት በኋላ ባለቤቱንና ከ21 ዓመት በታች ያሉትንና ያላገቡትን ልጆቹን ወደ አሜሪካ ለማምጣት የሚያደርገው የኢሚግሬሽን ፕሮሰስ ነው። አሜሪካ የገባው ጥገኝነት ጠያቂ አስቀድሞ ለራሱ ፈቃድ ባገኘ በሁለት ዓመት ውስጥ፤ ከላይ በተገለጸው መሠረት መሥፈርቱን ለሚያሟሉት ቤተሰቦቹ Form I-730, Refugee/Asylee Relative Petition የተባለውን ፎርም በመሙላት እነርሱም ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ያመለክታል።

በትግራይ ምስኪኖች የጦርነቱ ሰላባ ሆነው አስተዋሽ በማጣት አካላቸው ጎሎ በየጎዳናው እንደሚታዩ በሃዘኔታ የሚገልጹ የባለስልታናት ልጆችና ዘመድ አዝማዶች ልዩ ዕድል እንደሚመቻችላቸው በመጠቀስ ” ካሁን በሁዋላ ለሌሎች አንሞትም” በማለት ስም እየጠሩ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያሰሙ እንደነበር ይታወሳል። በስለፉ አብዛኞቹ አካላቸው የጎደለ፣ ክራንችና ተሽከርካሪ መቀመጫ የሚጠቀሙ ነበሩ።

ዶክተር አብረሃም የጀመሩትን ሂደት ሲጨሱ ቤተሰቦቻቸው ካሉበት ስፍራ ወደ አሜሪካን በመሄድ ይቀላቀሉዋቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለጸረ ሌብነት ዘመቻው ኢትዮጵያ ያቃታት ሶስተኛው መንገድ – “ድመቷ ጥቁር ትሁን ነጭ ዋናው ጉዳይ አይጥ መያዟ ነው”

በዓለማችን የሙስና መመዘኛ መሠረት በጣም ዝቅተኛ ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው...

እውነት እኛ “ጋዜጠኞች” ነን? የገፈፍነው የሕዝብ ዳኝነት … !!

የ “ጋዜጠኝነት” ስም የሚሰጠው ለሚታወቅ ስራና “ሙያተኛ ” ብቻ...

ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”

ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ...

የትግራይ ሰላማዊ ሰልፎችና የታደሰ ወረደ ዕጣ ፈንታ እያነጋገረ ነው፤ “ሰላም እንሻለን” ታጣቂዎች

በትግራይ ለፓለቲካ ጥቅም ሲባል ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም...
Shares