“ኦነግና ኦፌኮ በግል ለሽመልስ አብዲሳ ላቀረቡት ማመልከቻ በፓርቲና በመንግስት ደረጃ መልስ አይሰጥም” ብልጽግና

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ /ኦፌኮ እና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር/ ኦነግ በጋራ ላቀረቡት ደብዳቤ ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ አስታወቁ። ደብዳቤው ለፓርቲ፣ የውይይት ጥያቀውን አድንቀው ለመንግስት ወይም ለተቋም የቀረበ ባለመሆኑ ምላሽ ለመስጠት እንደማይችሉ አንድ የብልጽግና ከፍተኛ ባለስልጣን ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።

ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር ለመወያየት ጥያቄ ማቅረባቸውን በየግል የማህበራዊ አውዶቻቸው ይፋ አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር ያናገራቸው ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ደብድዳቤ ለመጻፍ የተገደዱት በክልሉ ያለው ችግር እየገዘፈ በመምጣቱ እንደሆነ አመልክተዋል።

ፓርቲዎቹ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በቀጥታ “ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት” በጋራ የላኩት ደብዳቤ የጋራ ውይይት እንዲደረግ የሚጠይቅ ነው።

በአጠቃላ ስለኦሮሚያ ፣ የኦሮሞ ህዝብና ስለ ክልሉ የጸጥታ ሁኔታ አቶ ሽመልስ ቀጠሮ እንዲይዙላቸው ያስገቡት ማመልከቻ መጪውን ምርጫ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እንደሆነ ፕሮፌሰር መረራ ተናግረዋል።

አሁን ባለው ችግር ዙሪያ ውይይትከመጠየቅ ይልቅ ዝም ብሎ መመልከት አግባብ ባለመሆኑ ጥያቀውን ማቀረባቸውን ያወጉት የኦፌኮ ሊቀመንበር፣ ቀደም ሲል በተለያዩ አካላት አነሳሽነት ስለተጀመሩ ውይይቶች ውጤት ተጠይቀው የተፈታ ችግር እንደሌለ ተናግረዋል።

አሁን ስለጠየቁት የእንነጋገር ጥያቄና ስለሚጠብቁት ውጤት ሲያስረዱ “ ገና ደብዳቤው ከገባ ሁለተኛ ቀኑ ነው። ምላሽ የጣል ብለን እናምናለን” ብለዋል። አክለውም “የምርጫ ቲያትር” ያሉት ምርጫ በርካታ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ፣ እነሱም አስር ፓርቲዎች በጋራ ያወጡዋቸው ሰባት ነጥቦች እንደሆኑ አመልክተዋል።

ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በሕግ የሚመለሱ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ስለሚገለጽ፣ ይህ ካልሆነ ፓርቲያቸው ራሱን ከምርጫ እንደሚያገል ተጠይቀው “ ከወዲሁ ምላሽ መስጠት አይቻልም። ምርጫ ቦርስ ሁለት ሳምንት የመመዘገቢያ ጊዜ ሰጥቷል። ውይይቱ ብዙ ጥቅም አለው ብለን እናስባለን” በማለት መልሰዋል። ምርጫው ነጻ፣ ተአማኒና ገለልተኛ ሊሆን እንደሚገባ አስምረውበታል።

ሁለቱ ፓርቲዎች ስላቀረቡት የውይይት ጥያቄ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ብልጽግና ከፍተኛ ባለስልጣን “ እንዴት መልስ ልስጥ” ሲሉ ነው ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት።

ከፌደራል ጀምሮ፣ ክልል፣ ዞን፣ እስከወረዳ የተዘረጋ የፓርቲዎች የጋራ መድረክ መኖሩን ያመለከቱት እኚሁ ባለስልጣን፣ በተዋረድ በዘዘሯቸው መዋቅሮች ጥያቄው አልቀረበም።

በፓሪ ደረጃ ለአገር አቀፍ ብልጽግና፣ ለኦእሮሚያ ብልጽግና፣ ወይም ለመንግስት በስም ተጠቅሶ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ ባከስልጣኑ ደብዳቤውን ጠቅሰው አስታወቀዋል። ደብዳቤው በቀጥታ ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተላከ በመሆኑ ምላሹን የሚሰጡት አቶ ሺመልስ በግላቸው እንደሆነም ገልጸዋል።

ፓርቲያቸው ብልጽግናም ሆነ መንግስት ውይይትን እንደሚያበረታታና ለዚሁ አመቺ ይሆን ዘንዳ አጀንዳ የማይገደብበት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያእጋራ የምክክር ምክርቤት በየደረጃው እስከ ወረዳ ድረስ መኖሩን ያወሱት ባለስልጣኑ፣ “ እንዲህ ባለው ተቋማዊ አሰራር ላልቀረበ ጥያቄ መልስ መስጠት አይቻልም” ብለዋል።

የውይይት ጥያቄ የሚበረታታ፣ የሚደገፍ፣ በፓርቲም ሆነ በመንግስት ደረጃ ምክክርና ውይይት በፖሊሲ ደረጃ የተያዘ ጉዳይ እንደሆነ ባለስልጣኑ ተናግረዋል። በዚህ ምክንያት በግል ለቀረበ ጥያቄ በፓርቲ ወይም በመንግስት ስም ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።

በተለይ ከኦሮሚያ ፐሬዚዳንት አቶ ሽመልስ ቢሮና ከራሳቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረገነው ጥረት አልተሳካም።

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...