“ፋኖ ሲጀምር የነበረውን ብቸኛ ኃይሉን ከስሯል፤ ሕዝብ አንቅሮ ተፍቶታል፤ ለመታረቅ መንግስትን ይፈራል ” የአብን ከፍተኛ አመራርና የፓርላማ ተወካይ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ፋኖ ሲጀምር የነበረውን ብቸኛ ኃይሉን መክሰሩን የአብን የፓርላማ ተወካይ አስታወቁ። የፋኖ ሃብት የነበረው ሕዝብ አሁን ላይ ፋኖን “አንቅሮ ተፍቶታል” ያሉት እኝሁ ተወካይ የእርቅ አሳብና ፍላጎት ያላቸው ቢኖርም መንግስትን እንደሚፈሩ አስታውቀዋል። ፍርሃቻውም አደረጃጀታቸና ፖለቲካዊ አቅማቸው የፈጠረው እንደሆነ ተናግረዋል።

ከሁለት ዓመት በፊት በአማራ ክልል የተጀመረው ጦርነት እያስመዘገበ ያለው ችግር ሊሸፈን ከማይችልበት ደረጃ መድረሱን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። በተለይም በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ “ ምን እየተደረገ ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? መዳረሻውስ?” የሚያሰኝ ነው።

ለአዲስ ሪፖርተር በግርድፉ የሚደርሱ መረጃዎች በክልሉ የሚደርሱና እየደረሱ ያሉ አስከፊ ወንጀሎች ዝርዝር ጥናትና ምርመራ የሚያስፈልጋቸው በመሆናቸው ለጊዜው ማተም አልተቻለም። ይሁን እንጂ ነብሰ ጡሮች ህክምና ማግኘት አልቻሉም፣ የጤና ክትትል ማግኘት ዘበት የሆነባቸው አካባቢዎች አሉ። አሰገድዶ መደፈር አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል። በይፋ እንደሚታወቀው ሕጻናት መማር እንዳይችሉ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ይከለከላሉ። እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ፤ መመህራን የደረሰባቸው መከራና ግድያ በርካታ ነው ወዘተ። ይህ ሁሉ እየሆነ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላም የማይመጡበትን ምክንያት ይፋ አያደርጉም።

ጥናት የሚያሻቸውን ጉዳዮች ለጊዜው በማስቀመጥ ሕዝብ ከተማረረባቸው ሌሎች ጉዳዮች መካከል የገንዘብ ክፍያ፣ የመንገድ መዘጋት፣ የነጻ እንቅስቃሴ መስተጓጎል፣ እንግልት፣ አፈና፣ እገታ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

በአማራ ክል በበርካታ አካባቢዎች ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ትራንስፖርት፣ ስልክ እና ኢንተርኔትን የመሳሰሉ አገልግሎቶች በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን የሚናገሩ ይህ እስከመቼ ይቀጥላል ባይ ናቸው።  ዋና ዋና ከተሞችን ከተለያዩ መንደሮችና አነስተኛ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶችም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል። በክልሉ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ተዘንግቷል።  ነዋሪዎች ለአዲስ ሪፖርተር እንዳስረዱት ከሆነ ምሬታቸውን ከሚገለጸው በላይ ሆኗል።

“የአማራ ሕዝብ ላይ በደል በርክቷል” በሚል ቃታ የሰባው ፋኖ የጠብ መንጃ ትግሉን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁልት ዓመታት የሆነውን የሚገመግሙ፣ ድርጅቱ “ተነሳሁለት” ከሚለው አጀንዳው በተቃራኒ እየሰራ መሆኑን በማንሳት ይከሳሉ።

ይፋኖ ትግል ከሚወራና “ተነሳሁበት” ካለው ጉዳይ ጋር ሲመዛዘን ከእውነታው የራቀ እንደሆነ በታጣቂው ኃይል በደል የደረሰባቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። “የቡድኑ ዓላማ ሳይሰሩ መብላት መጠጣት ፣ሴቶችን መድፈር ፣መዝረፍ ነው” የሚሉ ነዋሪዎች የጥውቆሙት ጉዳይ በጥልቅ ምርመራ ቢያሻውም የሚስተባበል አይደለም። ፋኖን ለይተው የሚከሱት ወገኖች እይደረሰ ያለው ሁሉ አብዛኛው ታጣቂ ኃይል ፊደል ካለመቁጠሩ ጋር እንደሚያያዝ ይናገራሉ። የመማሪያ ጠረጴዛ ፈልጦ ማንደድና በሱ አብስሎ መብላትን ለምሳሌ ያነሳሉ።

በርካታ ጥፋቶችን ነቅሰው በማውጣት እውነታው በሂደት የገባው የአማራ ክልል ነዋሪ ፋኖን አንቅሮ እንደተፋ የአብን ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለአዲስ ሪፖርተር ገልጸዋል። ምክንያቱን ሲያስረዱ ደግሞ የቡድኑ የክፋት ተልዕኮ በግልፅ በመገለጡ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለዚህም ጊዜውን ጠብቆ የሚወጣ በርካታ መረጃ እንዳለ አመልክተዋል።

ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም ስለ ፋኖ ፍላጎት የተናገሩት የአብን አመራር እና  የቡድኑ መሪዎች የአማራን ሕዝብ በደል ማስቆም እና ጥቅሞቹን ማስከበር እንጂ የሥልጣን ፍላጎት እንደሌለው ነበር፤ አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአብን አመራር ዛሬ ያ የቀደመው አመለካከት ስህተት መሆኑን ይናገራሉ፤ “የፋኖዎቹ የመጨረሻ ግባቸው ስርዓቱን በጠብ መንጃ  በመለወጥ  የአንድን ብሔር ፣ኃይማንት የበላይነትን ማስጠበቅ ነው” ብለዋል። ይህ ደግሞ ሌሎች የሚገዙት አካሄድ በመሆኑ ምስኪኑን የአማራ ሕዝብ የሚጎዳ እንጂ አንዳችም የሚፈይድለት ነገር የለም።

መንግስት ለመሆን በማሰብ  ብቻ ወታደራዊ አቅሙን አጋኖ የማየት ችግር ውስጥ የገባው ፋኖ “የሚደርስበትን ግብ ግልጽ በሆነ መንገድ የለየ ጠንካራ የፖለቲካ ኃይል ባለመሆኑ እንቅስቃሴው ሩቅ አይጓዝም” ሲሉ አሁን የታየውን መፈረካከስ በመጥቀስ ይተቻሉ።

መንግሥት እና ፋኖ በወታደራዊ አቅም ደረጃቸው በእጅጉ የተለያየ መሆኑን  የሚጠቅሱት የአብን  የተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ፣ መንግሥት በድሮን፣ በታንክ እና በትላልቅ መሳሪያዎች የተደራጀ ሠራዊት እንዳለው በመግለጽ ፋኖ ከዚህ ግዙፍ ኃይል ጋር ለንፅፅር እንደማይቀርብ ያመልከታሉ።

የፋኖ ብቸኛ አቅሙ የነበረው ሕዝብ እንደነበር የሚገልጹት የአብን አመራር፣ ሕዝብ ጋር ያለን አቅም ለመያዝ እና ለማነሳሳት የፖለቲካ አቅምና የሕዝብ ግንኙነት ስራ ወሳኝ ቢሆኑም ፋኖ በዚህ ረገድ እንዳልቻለበት ይገልጻሉ። ፋኖ በፖለቲካ አቅሙ የበሰለ ስብሰብ ባለመሆኑ  ብቸኛ ኃይሉን “ሕዝብ” አማሮ ብቻውን እየቀረ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ፋኖ አገራዊ የፖለቲካ ፍላጎት፣ መሬት የረገጠ የፖለቲካ ስትራቴጂና ይህ ነው የሚባል የሚታወቅ ፍኖታ ካርታ የያዘ ድርጅት ባለመሆኑ በሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች እምነት እንዲጣልበት አያደርግም” ያሉት የአብን አባል፣ ራሳቸውን በወጉ መመራት ካላቻሉ አንዳንድ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከቅዠት ጋር አመሳስለውታል። “ፋኖ ያግዙኛል ብሎ የሚያስባቸው ኃይሎች እንኳን ፋኖን ሊያግዙ ለራሳቸው በሁለት እግር ለመቆም የተቸገሩ ናቸው” ሲሉ ስም ሳይተቅሱ ተናግረዋል።

አሁን አሁን ሀቁ የገባቸው የፋኖ ኃይሎች ከመንግሥት ጋር ለመታረቅ ፍላጎት እንዳላቸው እንደሚያውቁ ያመለከቱት እኚሁ የፓርላማ ተወካይ፣ ይህንኑ የዕርቅ ፋልጎት ለአስታራቂ ኮሚቴ ማቅረባቸውን እንደሚያውቁ አመልክተዋል። የዕርቅ አሳብና ፋልጎት ቢኖርም ፍርሃት እንዳለም አስታወቀዋል።

የፍርሀታቸው መነሻ ምንጮች ብዙ ቢሆንም፣ በዋናነት ግን “መንግሥት ከሰፈረ ወጠጤ ጎረምሳ ጋር ቁጭ ብሎ እንደማይደራደር ጠንቅቀው ማወቃቸው የፈጠረባቸው ፍርሃት ብዙ እርምጃ እንዳይሄዱ ያደርጋቸዋል” ሲሉ የአብን ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለአዲስ ሪፖርተር ነግረዋል።

የክልሉ መንግስት በተደጋጋሚ ለውይይት ክፍት መሆኑን ማስታውቁን ተከትሎ የውይይት ጥሪው ከማይሳካባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋናው የፋኖ አደረጃጀቶች በሰፈርና በአካባቢ ላይ የተመሰረተ፣ የበሰለ ፖለቲካ ማራመድና ወቅታዊ ሁኔታዎችን ማንበብ የሚችሉ አመራሮች የሌሉበት መሆኑ፣ ከምንም በላይ ድርጅታዊ ቅርጽና በተዋረድ መዋቅሩን ጠብቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል አለመሆን እንደሆነ ተጠቅሶ ቀደም ሲል አስተያየት ሲሰጥ እንደነበር ይታወሳል።

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...