Monday, December 1, 2025

“ሸኔ ነብሰጡርና ህጻናትን ጨምሮ አርባ የሚደርሱ ሰማዊ ዜጎችን በሌሊት በተኙበት ጨፍጭፏል”  የአካባቢው ነዋሪዎች

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ራሳቸውን በነጻ አውጪነት የሰየሙ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን ዕድሜና ጾታ ሳይለዩ በጅምላ የሚገድሉበትን ምክንያት አያስታውቁም። በቤኒሻንጉል ባለፈው ቅዳሜ የተሰማው ዜና አርባ አንድ ንጹሃን በሸኔ መጨፍጨፋቸው ነው። የቤኒሻንጉሉን ዜና ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ገዳዮቹ በስም መጠቀሳቸው ብቻ ነው።  

የገዳዮቹ ስም በመጠቀሱ ሳቢያ መርዶው እንደ አርሲው ተደጋጋሚ ግድያ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን አለገኘም። አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የቢኒሻንጉል ክልል ባለስልጣን “ገዳዮቹ የተጠቀሱት በግፍ ዕድሜና ጾታ ሳይመርጡ በመሆኑና ማንነታቸው ስለሚታወቅ ነው“ ካሉ በሁዋላ ዝርዝር ምርመራና ማስረጃ ሲጠናቀቅ ይፋ የንደሚሆን አመልክተዋል።  

ሟቾቹ በተኙበት በየቤታቸው ደጃፍ ላይ፣ መንገድ ላይና በድንጋጤ በሚራወጡበት ወቅት በተገኙበት መሆኑን እማኞች አስታውቀዋል።  

የአገር መከላለከያ ሰራዊት በአካባቢው ባለመኖሩ አድፍጠው ምሽት ላይ ድንገት የጥይት እሩምታ የለቀቁትና አርባ አንድ ሰዎችን የገደሉት የሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን ለተለያዩ ሚንዲያዎች የተጎጂ ቤተሰቦችና የሚመለከታቸው አስታውቀዋል። ከግድያው በሁዋላ ከብትና ንብረት ዘርፈው ለመሰወርም ሞክረዋል።  

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በበኩጂ ቀበሌ ከ40 በላይ ሰዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን መገደላቸውን ያስታወቁት ነዋሪዎች፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት አባል እንዲሁም የአካባቢው አስተዳደር አካላትና ፖሊስ ናቸው። 

አንዳንድ መረጃዎች ከሟቾቹ መካከል አስራ አምስት ሴቶች ሲሆኑ ስምንቱ ሕጻናት መሆናቸውን ያስረዳሉ። ከሴቶች መካከል ነብሰጡሮች እንደሚገኙ ተመልክቷል። በጥቅሉ አርባ አንድ ንጹሃን ተጨፍጭፈዋል። እንደ አካባቢው ነዋሪዎች እሁድ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ከአስተዳደሩ ባይገለጽም ሦስቱ የሚሊሻ አባላት ከታጣቂዎቹ ጋር ተኩስ ከፍተው ሞተዋል።  

ይህ መንግሥት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሸኔ ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ብሎ እንደሚጠራ ቢታወቀም አዲስ አበባ ያለው ኦነግ ዩህ እስከተጻፈ ድረስ ግድያውን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም። ነበ ጡርን ጭመሮ ከአንድ ዓመት ሕጻን ጀምሮ እስከ 80 ዓመት የሚደርሱ አዛውንቶችን የጨፈጨፈውን ቡድን በስም ጠርቶ የተቃወም የተቃዋሚ ፓሪ ይህ እስከታተመ ድረስ አልተሰማም።  

ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት ተጎጂዎችና የተጎጆ ቤተሰቦች፣ ነዋሪዎችና የአስተዳደር አካላት በገሃድ ገዳዮችን ስም ጠርተው ይፋ በማድረጋቸው፣ ጉዳዩ ለፖለቲካ ገበያ ስለማይሆንና ግድያው በቅንጅት ሕዝብ ብሶት ውስጥ እንዲገባ የሚፈጸም በመሆኑ እንደሆነ ስማቸውን ያልጠቀሱ የክልሉ ከፍተኛ ባልስልጣን አስታውቀዋል።   

አዲስ ሪፖርተር በአርሲ በተደጋጋሚ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ “ገዳዮችን ለማወቅ ምን እያደረጋችሁ ነው?” በሚል ላቀረበው ጥያቄ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስድብ ሰንዘረው እንደነበር ስም ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።  

ጥቃቱን የፈጸሙት የሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ የሚናገሩ ሚሊሻዎች ከዚህ በፊትም በአጎራባች ጎዶሬ ቀበሌ ጥቃት በከፈቱበት ወቅት ከጭላንቆ እና ከበኩጂ ሚሊሻዎች ተውጣጥተው በመሄድ ተከላክለውና መክተዋቸው እንደነበር ያስረዳሉ። ባለፈው ቀዳሜ ታጣቂዎቹ ነጹሃንን ጨፍጭፈው ከብቶችን ዘርፈው ነነበ። የዘረፉትን ይዘው ግሽባቦ የሚባል አካባቢ ሲደርሱ ሚሊሻዎቹ ተኩስ ከፍተውባቸው የዘረፉትን እንስሳቶቹን ጥለው እንደሄዱም ጠቁመዋል። ሕዝቡ አሁንም ስጋት ስላለበት መከላከያ አካባቢውን እንዳይለይ ጠይቀዋል።

በየጊዜው ቦታና አሳቻ አጋጣሚ በመምረጥ ንጹሃንን የሚጨፈጭፉ ታጣቂዎች ለምን ንጽሃንን እንደሚገድሉ ኡአስታውቁም። ኃላፊነትም አይወስዱም። ግድያ በተሰማ ቁጥር መግለጫ በማውጣት ሲሆ0ን ገዳዮችን በስም ጠርተው፣ አለያም ገዳዮችን ለማወቅና ለማጋለጥ በድርጅታቸው፣ ወይም በስፍራው ባለው መዋቅራቸው ጥረት ሲያደርጉ አይታይም። ይህ አካሄድ በስፋት መነጋገሪያ ከሆነ ቆይቷል። ግዷን ለራስ የፖለቲካ ጀንዳ ማገዶነት መጠቀም የተለመደ መሆኑን አንድ ስመ ጥር አባት ጠሰን መእገባችን አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related