“ሃይሊ ጉቢ” የተሰኘውን አዲሱን የእሳተ ጎሞራ ፍንዳታ የሚያጠና ቡድን ወደ አፋር ተላከ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና በአፋር ክልል ከ10 ሺሕ ዓመት በላይ ተዳፍኖ የኖረው ሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ባለፈው እሁድ ፈንድቶ ፍንዳታው የለቀቀው አመድ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ላይ በመጓዝ ከባቢ አየር ውስጥ መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።

ይህን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ቀጣይነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያጠና የተመራማሪዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ-ፊዚክስ  ህዋ-ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የፌስሞሎጂ ሳይንስ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።

የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎቹ የየራሳቸው ሥም እንዳላቸው የተናገሩት ተመራማሪው ብዙ ጊዜሆሎሲን ቮልካኖስ እንደሚባሉ ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ባለፉት 10 ሺሕ ዓመታት ውስጥ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያካሄደ ከሆነ አክቲቭ የሚባል ስያሜ እንደሚሰጠው አንስተዋል።

ከሰሞኑን የተከሰተው ሃይሊ ጉቢ ግን እስካሁን ምንም አይነት የተመዘገበ ፍንዳታ ወይም እንቅስቃሴ ያላሳየ ቮልካኖ እንደነበረ አስታውሰዋል። ከአሁን ቀደም ከሚከሰቱ የእሳት ገሞራ ፍንዳታዎች አስቀድሞ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም ንዝረት እንደሚመዘገብ ነግረውናል። ከሃይሊ ጉቢ እሳት ገሞራ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ግን ብዙ የተመዘገበ ነገር እንደሌለ ተመራማሪው ገልጸዋል።

በሳተላይት እና በሌሎች የዘርፉ መሳሪያዎች የተሰበሰቡ መረጃዎ እንደሚያመላክቱት በመሬት ንዝረት ደረጃ ከሁለት ጊዜ በላይ እንዳልተመዘገበ ተናግረዋል። በዚህ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሰልፈርዳይ ኦክሳይድን ጨምሮ በብዙ ኪሎ ቶን የሚገመት የእሳተ ገሞራ አመድ ወደ ሰማይ የተረጨበት እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ተመራማሪዎች ወደ አካባቢው መጓዛቸውን ተናግረዋል። በቀጣይ በተመራማሪዎች የመስክ ምልከታ የሚገኙ ውጤቶች ይፋ እንደሚደረጉ የተናገሩት ተመራማሪው ጉዳዩ ክትትል የሚፈልግ ነው ብለዋል ።

የፍንዳታው ጭስ እና አመድ በንፋስ ቀይ ባህርን በማቋረጥ በየመን አድርጎ ብዙ ርቀት የተጓዘ ቢሆንም ለጤና አዋኪ የሆነው ነገር አብሮ ይጓዛል ማለት አይደለም ብለዋል። ነገር ግን እሳተ ገሞራው እሳት የሚተፋ እንደመሆኑ መጠን በአካባቢው ቅርብ ርቀት ያሉ ማናቸውም ነገሮች ላይ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች እንዳሉ ጠቁመዋል። ተመራማሪው አክለውም አደጋውን መከላከል ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

እንደዚህ አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች ለምን ይፈጠራሉ? እንዴትስ መመዝገብ እና መከታተል ይቻላል? የሚለውን ለማጥናት፤ በሰው ኃይልና በመሳሪዎች የዘርፉን ተቋማት ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል። ከዚህ ባለፈም ይህን መሰሉ ክስተቱ በሚያጋጥምበት ጊዜ ሎጀስቲክስ ጨምሮ እገዛ በማድረግ ትኩረት መስጠት ይገባል ነው ያሉት።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
tiktalk – https://www.tiktok.com/@addisreporter3
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...