የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ /ኦፌኮ በመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ አስር ዕጩዎች አቀረበ፤ ውሳኔው “ስልታዊ ነው” ብሏል

Date:

አዲስ ሪፖርተር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ /ኦፌኮ በመጪው ምርጫ የሚሳተፉ አስር ተወዳዳሪ ዕጩዋችን ማስመዘገቡን አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች። አብዛኛው አባላቱ፣ ውስን ቁጥር ያላቸው አመራሮቹና የመካከለኛ ደረጃ ካድሬዎቹ ወደ ብልጽግና “ኮብልለውበታል” የሚባለው ኦፌኮ የዕጭዎችን ቁጥር ያሳነሰው ወኪል በማጣትም ጭምር ነው ቢባልም የአገሪቱን የጸጥታ ችግር ነው እንደ ምክንያት ያቀረበው።

አስር ተወዳዳሮዎቹን ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት ያስመዘገበው ኦፌኮ ” ማዕከላዊ ኮሚቴው በአገሪቱ ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውስ እንዲሁም የፓርቲውን ህጋዊ ግዴታዎችና ለአባላቱና ለሚወክለዉ ህዝብ ያለበትን ጥልቅ ኃላፊነት ከግምት በማስገባት ሰፊ ግምገማ አድርጓል” ካለ በሚል መግለጫ ቢያወጣም ዕጩ ማስመዝገቡን ይፋ አላደረገም ነበር።

ይህንኑ አስመልክቶ አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የድርጅቱ መካከለኛ አመራር አስር አባላትን በዕጩነት እንዳስመዘገበ ገልጸዋል። ስም ዝርዝር ግን አልዘረዘሩም። ቀደም ባሉት ሪፖርቶች በርካታ የኦፌኮ አባላት በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ ምግባር የተነሳ ተቀይመው ድርጅቱን መልቀቃቸውን እነሱኑ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ፓርቲውን የለቀርቁት እንደሚሉት ጃዋር በፓርቲ ደረጃ ምን አልባት መዋጮ ይከፍል ካልሆነ በቀር አንዳችም ድጋፍ አድርጎ አያውቅም። ከዚህም በላይ በመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተአማኒነቱ ከፍተኛ የነበረውን ፓሪያቸውን “ጽንፈኛ” በማድረግ ከሕዝብ እንዲነጠል ማድረጉንና በሱ ምክንያት ዋጋ የከፈሉ በርካታ አመራሮች መገፋታቸውን እንደምክንያት አቅርበው ነበር።

ከምንም በላይ “የጋላን መንግስት እናጠፋለን ከሚሉ ጽንፈኛ ቡድኖችና አመራሮቻቸው ጋር በመሆን የጀመረውን እንቅስቃሴ ፓርቲው ሊያስቆም ባለመቻሉ ቅር ብሎናል። ይህ አካሄድ ፓርቲውንም ዋጋ አስከፍሏል። ለፖለቲካ ስልጣን መታገል ዓላማችን ቢሆንም እነድ ሕዝብ ኦሮሞን እናተፋለን ከሚሉ ጋር ሕብረት መፍጠሩ ለመላው ኦሮሞ የመከዳት ስሜት ፈጥሯል።” በማለት ከፓርቲው የተለዩበትን ምክኛት አስታውቀው ነበር።

“የጋላን መንግስት እናስወግዳለን፣ የሚኒሊክን ቤተመንግስት ከጋላ እንነጥቃለን” በሚል የተነሱ በአሜሪካ ባነር ለጥፈው ገቢ ሲያሰባስቡ እንደነበር የሚገልጹ፣ እነ ጃዋር ከእነዚህ ቡድብኖች ጋር ያላቸውን ህብረት እንዲያቆሙ በተለያዩ መንገዶች ስለተነገራቸው አሁን ላይ በግልጽ ስብሰባና ህብረት ማድረግ ማቆማቸው ይታወሳል።

የኦፌኮ መሪ ፕሮፌሰር መረራም ሆኑ ጽህፈት ቤቱ ይህን አይቀበለም። ጃዋር በግል የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል። በፓርቲ ደረጃ ይህን አድርግ የተባለው ነገር እንደሌለ ጠቅሰው ይከራከራሉ። በመጪው ምርጫ ለመወዳደር የሰላም ጉዳይ አስቻይ እንዳልሆነ ያገልጻሉ። ሙሉ መግለጫውን ክስር ያንብቡ።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ፤ስለ7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ተሳትፎን በተመለከተ ያሳለፈዉ ውሳኔ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ቅዳሜ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በፊንፊኔ ከተማ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በ7ኛ ዙር የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ላይ መሳተፋችንን በተመለከተ ኃላፊነት በተሞላበትና መርህ ላይ በተመሰረተ የሚካሄድበትን ስልት ወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት፤ ማዕከላዊ ኮሚቴው በአገሪቱ ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውስ እንዲሁም የፓርቲውን ህጋዊ ግዴታዎችና ለአባላቱና ለሚወክለዉ ህዝብ ያለበትን ጥልቅ ኃላፊነት ከግምት በማስገባት ሰፊ ግምገማ አድርጓል፡፡

ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች በመጡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተደረገ ግምገማ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎችም ክልሎች በግልጽ በሚታዩ ወታደራዊ ግጭቶች ምክንያት በስፋት በተከሰተ መፈናቀልና በአሰቃቂ የህይወት መጥፋት የተነሳ፤ በመላ አገሪቱ ነጻ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡

አባሎቻችንን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ መሪዎች በእስር ላይ መቆየታቸው፣ ቢሮዎች መዘጋታቸው፣ እንዲሁም የነጻ ፕሬስና የዜጎች መብቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ በመታፈናቸው የብዝሃ-ፓርቲ ዴሞክራሲን ተስፋ ባዶ የሚያደርግ ሁኔታ በመሆኑ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ የጠበበ ሆኖ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

ኦፌኮ የአባላቱን፣ የዕጩዎቹን፣ የደጋፊዎቹንና የአጠቃላይ ሕዝቡን ደኅንነት እንደ ዋና መርህ ግምት ዉስጥ በማስገባትና ህይወታቸውን አደጋ ላይ በሚጥልና መሰረታዊ ጉድለት ባለበት ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመሳተፍ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደገጠመዉ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ በጽኑ ያምናል፡፡ አስቻይ ሁኔታ በሌለበት የሚካሄድ ምርጫ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚፈልጉትን ሰላምና መረጋጋትም ሆነ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንደማያመጣ ታምኗል፡፡

ነገር ግን፤ ፓርቲያችን ኢ-ዴሞክራሲያዊነትና ኢ-ህገመንግስታዊነት በስፋት በተንፀባረቀበት 6ኛ ዙር አጠቃላይ ምርጫ ላይ ባለመሳተፋችንና እንደ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 99(1)መ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተሻሽሎ (እንደተሸጋሸገ) “የፖለቲካ ፓርቲዉ በሁለት ተከታታይ የምርጫ ወቅቶች በጠቅላላ ወይም የአከባቢ ምርጫ ዉድድር ሳይሳተፍ የቀረ እንደሆነ ከምዝገባ ይሰረዛል” ስለሚል ብቻ፤ ፓርቲያችን በፌዴራሉ ዋና ከተማ ፊንፊኔ ውስጥና በአንዳንድ ጥቂት አከባቢዎች ሊሳተፍ፤ እስከምርጫዉ ጊዜ ድረስ ሁኔታዎች ተስፋ ሰጪና መሠረታዊ በሆነ መንገድ ከተለወጡ ፓርቲያችን ዉሳኔዉን እንደገና እንደሚያጠን ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ወስኗል፡፡

ስለሆነም፤ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ስለ7ኛ ዙር አጠቃላይ ምርጫ ላይ ተሳትፎን በተመለከተ የሚከተለውን ወስኗል፡፡

1/ኦፌኮ በመጪው አጠቃላይ ምርጫ ‘ምሳሌያዊና ስልታዊ ተሳትፎ’ የተሰኘ ስትራቴጂን በመከተል በአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የምርጫ ክልሎች ላይ እና የደህንነቱ ሁኔታ በምርጫ ለመሳተፍ አስቻይ መሆኑን የሥራ አስፈፃሚዉ ገምግሞ በሚያፀድቃቸዉ የምርጫ ክልሎች ብቻ ዕጩዎቹን እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡

2/ከላይ በአንደኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ በሌሎች ሁሉም ክልሎች፣ በተለይም በግጭት በተወጠሩ የኦሮሚያ አካባቢዎችና ከዚያም ውጭ ባሉት የአገሪቱ አከባቢዎች መርህ ላይ የተመሰረተ ያለመሳተፍ ውሳኔያችን፣ መንግስት ለዜጎቹ ሰላምና ደኅንነትን ማረጋገጥ ባለመቻሉ ላይ ያለንን ጽኑ ተቃውሞ የሚገልጽ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ኦፌኮ በሕዝብ ደም ላይ ቆሞ ፖለቲካ አይሰራም፡፡

3/ለነፃና ፍትሓዊ ምርጫ አስቻይ ሁኔታዎች መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ብለን ያቀርብናቸዉ መሰረታዊ ጉዳዮች ያለማቋረጥ ማቅረባችን ይቀጥላል፡፡ እነዚህም፦

●በኦሮሚያ እና ጦርነት ዉስጥ ባሉ ሌሎች ክልሎች አፋጣኝና ሊረጋገጥ የሚችል የግጭት ማቆም ስምምነት እንዲደረግ፤

●ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እና ሁሉም ፓርቲዎች ጽ/ቤቶቻቸውን በነጻነት እንዲከፍቱና እንዲያንቀሳቅሱ እንዲፈቀድ፤

●የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የጸጥታ ተቋማት የፖለቲካ ገለልተኝነታቸውን የሚያረጋግጥ እውነተኛና የሚታይ ተቋማዊ ማሻሻያ እንዲያደርጉ፤

●የቅድመ-ምርጫ ሂደቱን በሙሉ የሚከታተሉና ቅድመ ሁኔታዎቹ መሟላታቸውን የሚያረጋግጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም የረጅም ጊዜ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች በአስቸኳይ እንዲጋበዙ ናቸው፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴዉ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህንን ውሳኔ ተከታትሎ ከመድረክ አባል ፓርቲዎች ጋር በመተባበር እና የመርህ አቋማችንን ለአሮሞ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝቦችና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስረዳትና ለመፈጸም የሚያስችል ጠንካራ የሕዝብ ግንኙነት እቅድ እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

ውሳኔያችን ለኦሮሞ ሕዝብና ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት ያንጸባርቃል፡፡ የመረጥነው መንገድ ቀላል ባይሆንም፤ ኃላፊነት የሚሰማዉና ስልታዊ ፋይዳ ያለው እንደሆነ እየገለፅን፤ ፓርቲያችንን ለቀጣዩ ረጅም ትግል እያቆየን፣ አሁን ያለውን ወቅት ተጠቅመን የፓርቲያችንን ህልውና ለማስቀጠል የምንታገልበት መንገድ መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴዉ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ማዕከላዊ ኮሚቴ

ፊንፊኔ፤ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የዓለም የነዳጅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ ፈተና [ታሪካዊ አርበኝነት ጥሪ] ወቅቱን ለሚመረምሩ ሁሉ

ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ኢትዮጵያ አገሬ ናት፣ ኢትዮጵያ እናቴ ናት፣ ሌላ...

ወሳኙ የአደዋ ድል ሚስጢር – የአፄ ምኒልክ አዋጅ

ይህ ማህበራዊ ውል መላውን ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር አስተሳስሯል።...

“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ – ኢህአፓ አሳማነቷን በሊፒስቲክ ልትደብቅ?

በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ...

ጃዋር መሐመድ የአመጽ ጥሪውን የሰረዘው ለአስቸኳይ ስራ ግብጽ ተልኮ መሆኑ ታወቀ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ሕዝብ አመጽ እንዲያቀጣጥል...