ድመቶች የባለቤቶቻቸውን ድምፅና ትዕዛዝ ሰምተው እንዳልሰሙ የሚሆኑት ግራ ስለሚገባቸው ወይም የማሰብ ችሎታቸው ዝቅተኛ ስለሆነ እንዳልሆነ አንድ አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።
ይህ ጥናት ለብዙ ዘመናት “ድመቶች ለምን እንደ ውሾች ታዛዥ አይደሉም?” ለሚለው ጥያቄ ሳይንሳዊ ምላሽ ሰጥቷል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ድመቶች የሰዎችን ድምፅ የመለየት፣ ትዕዛዞችን የመረዳት እና የባለቤቶቻቸውን ስሜት የመረዳት ሙሉ ብቃት አላቸው።
ይሁን እንጂ ድመቶች ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ የሚሰጡት እንደ ውሾች በታዛዥነት ሳይሆን፣ ምላሽ ለመስጠት በራሳቸው የሚወስኑት ነፃ እና መራጭ ባህሪ ስላላቸው እንደሆነ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
ይህ ባህሪያቸው ድመቶች ካላቸው ከፍተኛ የማስተዋል ብቃት የሚመነጭ ሲሆን፣ አእምሯቸውን የሰው ልጅን ትዕዛዝ ለመፈጸም ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎት ላይ ብቻ ለመጠቀም እንደሚመርጡ ያሳያል።
ተመራማሪዎቹ ድመቶችን “በገዛ ፈቃዳቸው የሚመሩ እንስሳት” በማለት ገልጸዋቸዋል።
በመሆኑም ድመትዎ ሲጠሯት ዝም ካለችዎት ድምፅዎን ስላልሰማች ወይም ስምዋን ስላላወቀች ሳይሆን፣ በዚያ ሰዓት ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ስለሌላት መሆኑን መረዳት ይገባል።
ይህ ጥናት ድመቶች የሰውን ልጅ እንደ ጌታ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ወይም አብሮ አደግ እንደሚያዩ የሚጠቁም ሲሆን፣ ባለቤቶችም ድመቶቻቸው ምላሽ እስኪሰጡ ድረስ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለባቸው ይመክራል።
ድመትዎ ምላሽ የምትሰጥዎት እሷ ስትፈልግ ብቻ መሆኑን ማወቅ በሁለታችሁ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ አስደሳች ያደርገዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






