የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካው ወታደራዊ ዘመቻ እና በቬንዙዌላው ኒኮላስ ማዱሮ ላይ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሜሪካ በቬንዝዌላ ላይ ያላት እውነተኛ ፍላጎት ላይ ክርክር አስነስቷል።
ትራምፕ ታሪካዊ ጥቃት ሲሉ ያሞካሹት ይህ ተልዕኮ አደንዛዥ ዕፅን ከመዋጋት በሚያስደንቅ ሁኔታ የቬንዙዌላ ሰፊ የነዳጅ ዘይት ክምችት ወደ መጠየቅ የተቀየረ ይመስላል።
ለወራት ያህል፣ ኋይት ሀውስ ከ100 በላይ ሰዎችን የገደሉ በጀልባዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ጨምሮ ወታደራዊ እርምጃዎችን “በአደንዛዥ ዕፅ ላይ የሚደረግ ጦርነት” እንደሆነ ተናግሮ ነበር።
ዘገባ ከሆነ ግን ትራምፕ ለአንድ ሰዓት ያህል በፈጀ ንግግራቸው የአደንዛዥ ዕፅን እምብዛም አላነሱም፤ ይልቁንም የነዳጅ ዘይት ጉዳይን ከ12 ጊዜ በላይ ጠቅሰዋል።
የትራምፕ እና ቬንዝዌላ ጉዳይ መባባስ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በቬንዙዌላ በተደጋጋሚ የቀረበውን የአሜሪካ የይገባኛል ጥያቄ ተጠናክሮ በመጨረሻም ማዱሮን ለመጣል እና የሀገሪቱን ሰፊ የተፈጥሮ ክምችት ለመያዝ አስችሏታል።
ትራምፕ በንግግራቸው “የቬንዙዌላ የነዳጅ ኢንዱስትሪን በአሜሪካን ተሰጥኦ፣ ጉልበት እና ችሎታ ገንብተናል፣ እናም የሶሻሊስት አገዛዝ በነዚያ ቀደም ባሉት አስተዳደሮች ተሰረቅን። ይህ በአገራችን ታሪክ የታየው ትልቁ የአሜሪካን ንብረት ዘረፋ ነው” ሲሉ መግለፃቸውም ለዚህ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።
የሩስያ እና የአሜሪካ ስተራቴጂካዊ ዓላማ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርጊቱን “ዘመናዊ የባህር ላይ ወንበዴ” ሲል በመግለፅ የቬንዙዌላ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲከበር እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ እየጠየቀ ማዱሮ እና ባለቤታቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ በጥብቅ ጠይቋል።
ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስከ ዛሬ ጃንዋሪ 6, 2026 እ.ኤ.አ ድረስ በጉዳዩ ላይ ምንም አስተያየት አለመስጠት በአሜሪካ እና ቬንዝዌላ መካከል በተፈጠረው አለመረጋጋት ሩሲያ እንደምታተርፍ ይጠቁማል።
እንደ CNBS ዘገበ፥ የትራምፕ በምዕራባዊው ንፍቀ ክበብ(Western Hemisphere) ላይ ማተኮር በዩክሬን እና በቀድሞ የሶቪየት ግዛቶች ውስጥ የሩሲያን አቋም ለማጠናከር ከፍተኛ አጋጣሚ ይሰጣታል።
ሩስያ በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ያልተገዳደረ የበላይነትን ለአሜሪካ በማረጋገጥ በተዘዋዋሪ የራሷን የተፅዕኖ መስክ በቀድሞ የሶቪየት ግዛቶች ውስጥ ህጋዊ ማድረግ እንዲሁም የምዕራባውያንን ጫና በዩክሬን ላይ በመቀነስ እና ፑቲን ተመሳሳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ሳይፈራ እዚያ የሚገኘውን ጥቅም እንዲያጠናክር ያስችለዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






