በዚሁ ህገ-ወጥ ተግባራቸው በመቀጠላቸው፤ International Medical Corps(IMC) የተባለው ድርጅት ተሸከርካሪ በዳንሻ ከተማ አስተዳደር በሚንቃሳቀስበት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በትራፊክ ደንብ መተላለፍ ሲያዝ ተሸከርካሪው ከጫነው አንድ ትልቅ ታንከር ውስጥ 3 ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ደብቆ እያዘዋዋረ በመገኘቱ እና ይህም ተግባሩ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን የሚያሳፋፋ እና በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ፤ የዞኑ አስተዳደር International Medical Corps (IMC) እና Norwegian Refugee Council(NRC) የተባሉ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ከላይ የተመለከቱትን ህገ-ወጥ ተግባራት በመፈጸማቸው በበቂ ሁናቴ በማረጋገጡ እና ይህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያርሙ የተሰጣቸውን ምክረ ኃሳብ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ዞኑን ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
አዲስ ሪፖርተር – በማንነትና በድንበር ጥያቄ ከፍተኛ ውዝግብና የፍትህ ጥሰት ለሶስት አስርት ዓመታት ያስተናገደው ወልቃይት ጠገዴ አሁን ላይ እያስተዳደረ ያለው አካል ህገወጥ እንደሆኑ በገለጻቸው የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢስዎች ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረው ግጭት በፕሪቶሪያ ስምምነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ስምምነትና ሉዓላዊነትን የማስከበር አስፈላጊነትን አጉልቶ አሳይቷል።
ሰላም እንዲሰፍን ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሆኑ አገር በቀል አካላት የሀገሪቱን ሕጎችና ብሔራዊ ስምምነቶች እንዲያከብሩ የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት የላቀ ነው። ህግም ያስገድዳል።
ተመልሶ “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አካል ሆኗል” በተባለው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር “ወሰድኩት” ያለው እርምጃ የዚህን ታሪካዊ እና የዘመናዊ የሕግ የበላይነት ትግል ፍሬውን ከማስጠበቅ አኳያ አግባብ እንደሆነ የሚገልጹ ያሉትን ያህል የኮነኑና ከተባረሩት ወይም ከታገዱት እርዳታ ሰጪዎች ጎን የቆሙ አሉ።
አስተዳደሩ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ሁለት ዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች፣ ማለትም International Medical Corps (IMC) እና Norwegian Refugee Council (NRC)፣ ላይ “በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተዋል” በሚል ምክንያት እንዲታገዱ እና ዞኑን ለቀው እንዲወጡ ጥብቅ መመሪያና ትእዛዝ አስተላልፏል። ኖርዌጂያን ሬፊውጂ ካውንስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ተጥሎበት የነበረው እገዳ ከሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ተቃውሞ ገጥሞት እነደነበር የሚታወስ ነው። ከትህነግ ዋና አደረጅና የፖለቲካ አጋር ኖርዌጂያዊው ሼትል ትሮድ ቮል ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው በማስረጃ ቀርቦም ነበር።
ይህ እርምጃ የዞኑን ሕጋዊ ባለቤትነት እና በፌዴራል መንግሥት የተፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነትን የማስከበር የጸና አቋም እንደሆነም ግተመልክቷል።

ዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች (NGOs) ሰብዓዊ ድጋፍን በማቅረብ ረገድ ቁልፍ ሚና ቢኖራቸውም፣ በየትኛውም ሉዓላዊ አገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የአገሪቱን ሕጎች እና የአካባቢውን አስተዳደር ማክበር እንዳለባቸው ዞኑ አመልክቷል።
አስተዳደሩ ባወጣው ዝርዝር መግለጫ መሠረት፣ እነዚህ ሁለት ድርጅቶች የተሰጣቸውን የሰብዓዊ ተልዕኮ ዓላማ በመጣስ፣ የኢትዮጵያን ሕጎችና በተለይም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን የሚጥሱ ተከታታይ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።
ዞኑ በዋናነት ያቀረባቸው የታጣሱ ህጎች አሻሚ እንዳልሆኑ አመልክቷል። ድርጅቶቹ ከሰብዓዊ ድጋፍ ተልዕኳቸው በማፈንገጥ ወገንተኛ የፖለቲካ አቋም በመያዝ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥረዋል።
“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ በብዙ መሥዋዕትነት አካባቢው ነጻ የወጣ ቢሆንም፣ እነዚህ ድርጅቶች ይህንን ማኅበረሰብ እንደ “አፈናቃይ” በመቁጠርና አካባቢውንም የትግራይ ክልል አካል በማለት መግለጻቸው እጅግ አሳሳቢ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነው” ሲል ከሷቸዋል።
ከዚህም የባሰ ጥሰት ተብሎ የተጠቀሰው፣ ድርጅቶቹ በቅጥር ሂደት እና በይፋዊ ግንኙነቶች ወቅት አካባቢውን “ምዕራብ ትግራይ” በሚል መጥራታቸው ነው። ይህ አጠራር የፌዴራል መንግሥት የችግሮችን ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የተፈራረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጋፋና አካባቢውን እንደ “አወዛጋቢ ቦታ” (Contested area) የሚቆጥር ግልጽ ጥሰት ተደርጎ ተወስዷል። የፕሪቶሪያ ስምምነት ዋና ዓላማ አንዱ የሰላም ማምጣት ሲሆን፣ ይህ መሰሉ አካባቢውን በሌላ መጠርጠር የብሔራዊ ስምምነትን መሠረት የሚንድ ተግባር ነው።
የIMC ከፖለቲካዊ አቋም በመያዝ ቀጥተኛ ወንጀል መፈጸሙን የሚናገረው መግለጫው፣ በመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዳንሻ ከተማ አስተዳደር ሲንቀሳቀስ የነበረው የIMC ድርጅት ተሽከርካሪ በትራፊክ ደንብ መተላለፍ ሲያዝ፣ ተሽከርካሪው በጫነው ትልቅ ታንከር ውስጥ ሶስት (3) ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ደብቆ ሲያዘዋውር ተገኝቷል።
አስተዳደሩ ይህንን ድርጊት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን የሚያባብስና በወንጀል የሚያስጠይቅ ከባድ ጥፋት መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ገልጿል። ሰብዓዊ ድጋፍ በሚል ሽፋን እንዲህ ያለውን ከባድ ወንጀል መፈጸም የሕግ የበላይነትን የሚንዱ ተግባራት መሆናቸውን አስተዳደሩ አሳስቧል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን መንግሥት እና መላው ሕብረተሰብ ለድርጅቶቹ ከሕገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡና የፕሪቶሪያን ስምምነት እንዲያከብሩ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ሰጥተው እንደነበር መግለጫው ያስረዳል። ይሁን እንጂ፣ ድርጅቶቹ ይህንን ምክረ ሃሳብ ባለመቀበላቸውና ሕገ-ወጥ ተግባራቸውን በመቀጠላቸው፣ የዞኑ አስተዳደር የመጨረሻውን እና የማያዳግም ውሳኔ አስተላልፏል።
International Medical Corps (IMC) እና Norwegian Refugee Council (NRC) የተባሉ ዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ከላይ የተዘረዘሩትን ከባድ ሕገ-ወጥ ተግባራት መፈጸማቸውን በበቂ ሁኔታ ስላረጋገጠ እና ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያርሙ የተሰጣቸውን ምክረ ኃሳብ ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ዞኑን ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው የዞኑን ሰላም፣ ሕግና ሥርዓት እንዲሁም የብሔራዊ ስምምነትን (የፕሪቶሪያን ስምምነትን) ለማስጠበቅ ሲባል መሆኑን አስተዳደሩ ደጋግሞ አጽንኦት ሰጥቷል። ትእዛዙን ተከትሎ የዞኑ የጸጥታ ኃይሎች የድርጅቶቹን ንብረቶች፣ ቢሮዎችና መጋዘኖችን በቁጥጥር ሥር የማዋልና የመፈተሽ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
የዞኑ አስተዳደር የሁለቱ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ማቆም በአካባቢው ለሚሰጠው ሰብዓዊ ድጋፍ ሥራ ላይ ክፍተት እንዳይፈጥር ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። ከፌዴራል የመንግሥት አካላት እና ከሌሎች ህጋዊ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር፣ IMC እና NRC ያቀርቡት የነበረው አገልግሎት (በተለይም በጤና፣ በስደተኞች/ተፈናቃዮች ድጋፍ እና በውሃ ዘርፎች) ሳይቋረጥ እንዲቀጥል አማራጭ አቅራቢዎችን የማፈላለግ ሥራ እየሰራ ይገኛል።
ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሌሎች ዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሁሉ የሀገርን ሕጎች፣ የአካባቢውን አስተዳደርና ማንነት አክብረውና የፕሪቶሪያን ሰላም ስምምነት ተንተርሰው መሥራት እንዳለባቸው እንደ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሆኖ የሚአገለግ፤ል ውሳኔ እንደሆነም ግተመልክቷል። አካባቢውን “ምዕራብ ትግራይ” ብሎ ለመጥራት መሞከር፣ የዞኑን ሕጋዊ ባለቤትነትና ማንነት የሚጻረር በመሆኑ፣ ይህን መሰል ማንኛውም ሙከራ በዞኑ ሕዝብና አስተዳደር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አስተዳደሩ በድጋሚ አረጋግጧል።
በሌላ በኩል፣ ሁለቱ ድርጅቶች አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። የIMC የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ሎውረንስ ሙታህሪያ እና የNRC ካንትሪ ዳይሬክተር አይዛክ ኦዲያምቦ ኦኮም፣ ክሱን እውነተኛነት ለማረጋገጥና ሕጉን ተከትሎ ሁኔታውን ለመረዳት ጊዜ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት በበኩሉ፣ ድርጅቶቹ የፕሪቶሪያን ስምምነትና የሀገርን ሕግ በመጣስ ወገንተኛ የፖለቲካ አቋም መያዛቸውን በተመለከተ የዞኑን አስተዳደር እርምጃ እንደሚደግፍ የሚጠቁሙ ምልክቶች ታይተዋል።
በመጨረሻም፣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር ያሳየው ቁርጠኝነት፣ በታሪክ አውድ የሀገራዊ ሰላም ስምምነትን እና ሉዓላዊነትን የማስከበር ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል። ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ምድር የሚንቀሳቀስ ማንኛውም አካል፣ የተሰጠው ተልዕኮ ሲፈጽም ምንም ይሁን ምን፣ ከሕግ በላይ አለመሆኑንና የሀገርን ማንነትና አንድነት ማክበር ግዴታው መሆኑን በሚገባ አስረድቷል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር በ International Medical Corps (IMC) እና Norwegian Refugee Council (NRC) ላይ የወሰደው የማገድ እና ከዞኑ የማስወጣት እርምጃ የሀገርን ሕግና ብሔራዊ ስምምነቶችን የማስከበር ቁርጠኝነትን ከማሳየቱም በላይ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶች ሊኖራቸው ስለሚገባው ፖለቲካዊ ገለልተኝነት (Neutrality) እና ገለልተኛነት (Impartiality) ዓለም አቀፋዊ ክርክር ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነም ተገልtsual.
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግና የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የአሠራር መርሆዎች ድርጅቶች በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜ ወገንተኛ መሆን እንደሌለባቸው ይደነግጋሉ። እርዳታ የሚሰጡት በሰዎች ፍላጎት መሠረት ብቻ እንጂ በፖለቲካዊ፣ በጎሣዊ ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት መሆን የለበትም።
IMC እና NRC በአካባቢው ላይ የወሰዱት አቋም ግን ይህንን መሠረታዊ መርህ የጣሰ ነው። አካባቢውን “ምዕራብ ትግራይ” በሚል ስያሜ መጥራት እና የዞኑን ሕጋዊ ነዋሪዎች እንደ “አፈናቃይ” መቁጠር፣ ከሰብዓዊ ፍላጎት ይልቅ ለፖለቲካዊ አቋም ቅድሚያ መስጠትን የሚያመለክት ነው። በተለይ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በትህነግ መካከል የተፈረመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአካባቢው ሰላምን ለማምጣት ያለመ ነው። የሰላም ስምምነቱን መርሆዎችና የሀገሪቱን አስተዳደራዊ አወቃቀር የሚፃረር ማንኛውም የውጭ አካል ድርጊት፣ ስምምነቱን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ፣ የዞኑ አስተዳደር እርምጃ መውሰዱ ብሔራዊ ግዴታ እንደሆነም ተመልክቷል።
በተጨማሪም፣ የ IMC ተሽከርካሪ በሰው ዝውውር ወንጀል መያዙ የሰብዓዊ ድርጅቶችን መተማመኛ የሚሸረሽር ድርጊት ነው። ሰብዓዊ ድጋፍ በሚል ሽፋን ለወንጀል ተግባር መደበቂያ መሆን የሕግ የበላይነትን የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ፣ በዞኑ ውስጥ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለሚሠሩ ሌሎች ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጭምር አሉታዊ ጥርጣሬን የሚፈጥር ተግባር ሆኖ ተወስዷል።
አስተዳደሩ ያቀረባቸውን ውንጀላዎችን በተመለከተ ቢቢሲ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የሁለቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንደማይሰጡ ገልጸዋል። የኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮር የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ሎውረንስ ሙታህሪያ “አዲስ አበባ እና መስክ ላይ ያሉ መረጃዎችን ማረጋገጥ፣ መግለጫውን ካወጡት አካላት ጋር ግንኙነት መፍጠር እና [በመግለጫው] የሰፈረውን [ክስ] እውነተኛነት ማረጋጥ” ስለሚያስፈልግ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ማናገራቸውን ቢቢሲ አመልክቷል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






