አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን የፓለቲካ ምህዳር በውይይት፣ በድርድር እንዲኹም በመነጋገር የወንድማማች እልቂት የቅድሚያ ቅድሚያ እድል እንዲሰጠው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሲኖዶስ ጥሪ አቅርቧል አቅርበዋል።
መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችና ነፍጥ ባነገቡ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ እንዲፈቱና ወደ መግባባት እንዲመጡ ሲኖዶሱ ጥሪ ማቅረቡን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ – ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተለይም በመንግስት ፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞች እና ነፍጥ ያነሱ ወገኖች ሁሉ ወደ መግባባት እንዲመጡ እና እንደ አገር የተወሳሰበውን ችግር እንዲፈታ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ተማፅነዋል።
አቡነ ማትያስ ይህንን ያሉት ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ – ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ነው።
ፓርሪያርኩ፣ በሰጡት መግለጫ የነገው ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው ሰላምና አንድነት መረጋጋት ሲኖር መኾኑን ጠቅሰው ለዚህም መንግስትን ጨምሮ የሚመለከታቸው የፓለቲካ አካላት ስለ ሰላም የበኩላቸውን እንዲወጡ ገልፀው የተጀመረው የሲኖዶስ ጉባዔ
ለዚህ ሁሉ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል መደላድል ሊተልም እንደሚተልም ተናግረዋል።
በመግለጫቸው፣ በሀገራችን ያለው ያለመረጋጋት በሕዝባችን አጠቃላይ ስነ ልቡና እያቃወሰ የሚገኝ መሆኑንና አጠቃላይ የፓለቲካ ኃይሎች ቆም ብለው እንዲያስቡበት ሲኖዶሱ ይመክራል ብለዋል። የሰላም እጦቱ ጉዳይ አገሪቱን አንድነትና ዕድገት ላይ የሚያስከትለውን ጫና በቀላሉ የሚታይ ባለመኾኑ አጠቃላይ የፓለቲካ ኃይሎች ሁሉ ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ እንዲፈቱ ፓትሪያርኩ ተማፅኖ አቅርበዋል ።
በተለይም ለነገን እናስብላታለን የምንላት አገርና ተረካቢ ትውልድ ከተወሳሰበ ችግር የተላቀቀች አገር ማስረከብ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙ ሲኾን የሕዝቡ ሰነ ልቡና ከተጎዳ የነገው ዕድል ጤናማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም ሲሉም አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።
ፓትሪያርኩ አክለውም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እየደጋገማት የሚገኘውን ፈተናዎች እና ችግሮች አስመልክተው ጠንከር ያለ ትችት ያቀረቡ ሲኾን ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመፍትሔ ሐሳቦች የሚቀርብበት መኾኑን ጠቁመዋል።
ለዚህም ቤተክርስቲያን ከተለያዩ ወገኖች እየደረሰባት ያለው ችግር በተመለከተ ደጋግመው ያነሱ ሲኾን ሲኖዶሱ አስፈላጊውን መፍትሔ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ እንዳለና በቅርቡም በቤተ-ክርስቲያን ላይ የደረሰውን የመብት ጥሰት የሚከላከል ሆነ በሕግ የሚጠይቅና የሚያስቆም አካል አለመገኘቱን ወቅሰዋል።
ፓትሪያርኩ፣ በተለይም ስም የማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ እንዳለ ጠቅሰው የቤተ- ክርስቲያኗን እምነት ከመንቀፍና ከማብጠልጠል በላይ አልፎ የቅዱሳንን ቅዱስ ሥዕል በአደባባይ እስከ መቅደድ የተደረሰበት ሁኔታ እንደነበር አንስተዋል።
ሲኖዶሱ ይህ ተግባር ሕገ-መንግስት በቀጥታ የሚፃረር ድርጊት ሆኖ ስላገኘው አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድና የኢትዮጵያ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት ተጠያቂነት እንዲሰፍን አስፈላጊው የሕግ ሒደት መጀመሩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን የሰላም እጦት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በቤተክርስቲያን ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ እንዳለና በተለያዩ አከባቢዎች ባሉ አለመረጋጋቶች በርካታ የቤተክርስትያን ካሀናት ለፍልሰት መዳረጋቸውን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አያይዘው ጠቁመዋል።
አሁን ላይ ያለው የፓለቲካ ምህዳር ያሉ አካላት የችግሩን ውስብስብና የተራዘመ እንዲኾን ያደረጉት ሁሉ ጉዳዮን ቆም ብለው እንዲያጤኑበት ፓትሪያርኩ ጥሪ ያቀረቡ ሲኾን በውይይት፣ በድርድር እንዲኹም በመነጋገር የወንድማማች እልቂት የሚያስቆም እድል ቅድሚያ እንዲሰጠው የሲኖዶስ ጉባኤው ጥረት ያደርጋል ብለዋል።




