የብር የመግዛት አቅም ሊያድግ እንደሚችል ተጠቆመ፤ ኢትዮጵያና የዓለም የገንዘብ ድርጅት በጥቅምት ለግምገማ ይቀመጣሉ

Date:

  • አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 13 ቀን 2018 – የወርቅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲተመን በመደረጉ ሁለት ሶስተኛ ዝቅ ያለው የኢትዮጵያ ብር ሊጠናከር እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ አስታወቁ። ኢትዮጵያ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ አራተኛው ዙር የፕሮግራም ግምገማ ያካሂዳሉ።

“ሕዝቡ በሚቀጥሉት ወራት የብር ተወዳዳሪነት መጨመርን መጠበቅ አለበት፤ የብር መዳከምን ብቻ ለሚጠብቁ እቅዳችሁን እንደገና እንድታጤኑ እመክራለሁ” ሲሉ የባንክ ገዢው ከምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። የወርቅ የወጪ ንግድ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡናን በልጦ፤ ባለፈው ሰኔ 30 3.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱ ይታወሳል።

ኢበሌላ ዜና ትዮጵያ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት አራተኛው ዙር የብድር አሰጣጥና አፈፃፀም ዙርያ  የግምገማ ፕሮግራም ለማካሄድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተሰምቷል።

ስምምነቱ ወደ አሜሪካ ያመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ ያደረገው ተሳትፎ በተደረጉት የጎንዮሽ ውይይቶች አማካኝነት መኾኑን በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ቡድን አስታውቋል።

ልዑክ ቡድኑ፣ በየደረጃው ያሉ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተከታታይ የሆኑ ድርድሮችን በማድረግ የብድር አወሳሰድ እና በኢትዮጵያ በኩል የሚጠበቀው የብድር አመላለስ በተመለከቱ ጉዳዮች ዙርያ ለመወያየት ቀጠሮ መያዙን ከዓመታዊ ጉባኤው መጠናቀቅ በኃላ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ልኡክ ቡድኑ በአሜሪካ አገር በተካሄደው የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ሰብሰባ ከሁሉም ወገኖች ጋር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የገለፀ ሲኾን እግረ መንገዱን ከተለያዩ የብድር ተቋማት ጋር የተሻለ መግባባት የተደረሰበት መኾኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ተናግረዋል።

ልኡክ ቡድኑ በአሜሪካ ዋሽንግተን በተካሄደው የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ሰብሰባ ላይ ከነበረው መደበኛ ቆይታ በተጨማሪ በስብሰባው የተገኙት ተቋማት ጋር ጎን ለጎን ውይይት መደረጉንና የተደረጉት ውይይቶችም በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀበት እንደነበር አስታውቋል።

የዓለም ባንክ ጋር በተደረጉ ውይይቶች መካከል በዋነኝነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማዘመን፣ ምርታማነትን በማሳደግ፣ አዳዲስ የዕድገት መንገዶችን በመፍጠር እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማጎልበት የስራ ዕድል ለመፍጠር እና በመላ ሀገሪቱ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል የተወሰዱ እርምጃዎች የተቋሙ ከፍተኛ ሐላፊዎች ያደነቁ መኾናቸውንና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ምክረሐሳብ መስጠታቸውን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

አሕመድ ሸዴ አክለውም የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የረጅም ጊዜ አጋርነት ለሀገሪቱ ዋና ዋና የልማት ዘርፎች ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ  ድጋፍን ማድረጉን ጠቅሰው በተለይም የስራ ዕድል ፈጠራን፣ ዘላቂ መሠረተ ልማቶችን እና የሰው ኃይል ካፒታል ልማትን ለማስቀጠል ከባንኩ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተደረጉ ድርድሮች መካከል የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ለውጥ እና የዕዳ ማስተካከያ ዘላቂ ጥረቶች ለመደገፍ ቁርጠኛ መኾናቸውን ገልፀውልናል ብለዋል።

ከፓሊሲ ለውጡ በኃላ በኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት መመዝገቡን እና የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መሄዱን እንዲሁም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጠናከር መንግሥት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል መምከራቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እንዲጠናከር ዋና ዳይሬክተሯ ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከሰጧቸው ምክረ ሐሳቦች መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

ተቋሙ፣ መንግስት የፊስካል አስተዳደርን ለማጠናከር፣ የአገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብን ለማጎልበት እና ቁልፍ መዋቅራዊ የሪፎርም ሰራዎችን የሚያደርገው ድጋፍ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ገልፀው በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር በሚካሄደው ውይይት እልባት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ሊጀመር በታቀደው አራተኛው ፕሮግራም ግምገማ ወቅት ሁለቱም ወገኖች ትብብርን የበለጠ ለማጠናከር እና ዕድገትን እና የማሻሻያ ዕድሎችን በጋራ ለመገምገም እቅድ መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል ።

በተመሳሳይ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር ኢትዮጵያ በወቅቱ ያልከፈለችውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ልዑክ እና በግል አበዳሪዎች ኮሚቴ መካከል የተደረገው ድርድር በስምምነት መጠናቀቁን በመረጃው ተጠቅሷል ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ የብድሩን አከፋፈል ሁኔታዎች አስመልክቶ ያለ ስምምነት መጠናቀቁን የሚገልፁ ነጥቦች እንደነበሩት የሚታወስ ሲኾን በድርድሩ ወቅት ኢትዮጵያ “ዋይት ኤንድ ኬዝ” እና “ላዛርድ” የተሰኙ የሕግ እንዲሁም የፋይናንስ አማካሪዎችን ይዛ ቀርባ እንደነበር አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የመደራደርያ ነጥብ ሁሉንም አበዳሪዎች በእኩልነት ማስተናገድ የሚለውን አቋሟን በድርድሩ ወቅት እንዳንፀባረቀች ይታወቃል። ሁለቱ አካላት ስምምነት ላይ እንዳይደርሱ ካደረጓቸው ጉዳዮች አንዱ የግል አበዳሪዎች ከሌሎች አበዳሪ አገራት ጋር በእኩል ዐይን መታየት አለባቸው የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት አቋም እንደነበር ለትውስሳ ተነስቷል። 

በዚህ መሰረትም የቦንዱ ገዢዎችን የወከለው የአበዳሪዎች ኮሚቴም በአሁኑ ሰዓት ድርድሩ “ፍሬ አልባ” ደረጃ ላይ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱና በዚህ ሳቢያ “የሕግ እርምጃን ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች እያጤነ” መሆኑ ሲገለፅ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይሁንና አሕመድ ሽዴ እንደገለፁት ከሆነም በዋሽንግተን በተደረገው ተከታታይነት ያለው ድርድር እና ውይይት መሰረትም ከመግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...

በወንጀል በተገኘ ሐብት የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 - በወንጀል የተገኘ...