ትህነግ ለኢትዮፎረም የሚሰጠውን በጀት አቆመ፤ ታደሰ ወረደ አሸነፉ፤ “ጨዋታው አስቀድሞ ይታወቅ ነበር፤”

Date:

አዲስ ሪፖርተር ራ – ሱን ለግማሽ ዘመን በተገንጣይነት ስም የሚጠራው ትህነግ በበጀት ሲያስተዳድረው ለነበረው ኢትዮሚዲያ ፎረም በጀት ማቋረጡን አንድ የአርሚ አዛዥ ለአዲስ ሪፖርተር አረጋገጡ። ሰሞኑን በመቀለ ተደርጎ በነበረው የተለመደ ግርግር ታደሰ ወረድ ማሸነፋቸው ታወቀ። ” ጨዋታው አስቀድሞ ይታወቅ ነበር” ሲሉ እኚሁ ክለፈተኛ የአርሚ አመራር አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ENN በሚል ስያሜ እነ ዶክተር ደብርጽዮን በልዩ በጀት አቋቁመውት በነበረው የቴሌቪዝን ጣቢያ ውስጥ ግንባር የነበረው ያየህሰው ሽመልስ የሚመራውን ኢትዮፎረም የዩቲዩብ የሚዲያ አውድ በበጀት የሚያስተዳድረው ትህነግ እንደነበር ይታወቃል። ኢትዮፎረም ” የብልጽግና ሰነድ እንጃችን ገባ” በሚል ራሱ እያዘጋጀ በሚያቀርበው መረጃ የሚታወቀው ሚዲያ ነው፣ በጀቱ እንዲቆምበት የተደረገበት ምክንያትና ካቋቋመው ትህነግ ጋር የተለያዩበት መነሻ ጉዳይ ለጊዜው በግልጽ አልሆነም። አዲስ ሪፖርተር ኢትዮፎረም እንዴት ራሱ መረጃ ይጠምቅ እንደነበርና ከአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሚስጢር እንዴት ያገኝ እንደነበር በቅርቡ ዘገባ ታቀርባለች።

ኢትዮፎርም በጦርነቱ ወቅትና ከዚያም በፊት ከአቶ ስብሃት ነጋ በቀጥታ የሚሰጠውን የቤት ስራና የትህነግን ዳግም ወደ አዲስ የመመለስ ዕቅድ ከማመቻቸት አንጻር ሰፊ ሚና ሲጫወት እንደነበር ይታወሳል። አዘጋጆቹ ወደ ጀርመን ከመውጣታቸው በፊት በተመሳሳይ በውጭና በአገር ውስጥ በሚሰሩ ሚዲያዎች ለስደት ማመልከቻ የሚረዳ ዘገባ ሰርተውላቸው እንዳሰራጩላቸው አይዘነጋም።

መረጃውን የሰጡን ወገኖች እንዳሉት ትህነግ በጦርነቱ ወቅት እንዳደረገው፣ ውጭ አገር ባሉት ምዕራፎቹ አማካይነት በጀት መድቦ የውጭ ሚዲያዎች ከጎኑ ለማቆም ወስኖ እይሰራ ነው። ችግር የሆነው ግን ቀደም ሲል እንደሆነው በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራዎች መዋጮ እንደተጠበቀው ሊሆን እንደማይችል ስጋቱ ከፍ ማለቱ ነው።

በስብሃት ነጋ ቤተሰቦች በተለይም በሞንጆሪኖና ወንድሟ አቶ ዳዊት አማካይነት የባከነው 18 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ጉዳይ በኦዲት ይፋ አለመሆኑ በትህነግ ውስጥ አንዱ የልዩነቱ ምንጭ መሆኑ፣ ይህንኑ ተከትሎ ልዩነቱ ውጭ አገር ባሉ ደጋፊዎች ዘንድ መለያየትን በመፍጠሩ ዕቅዱ ብዙም ድጋፍ ያገኛል የሚል ዕምነት የለም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከከፈቱ የሚታወቁ ጠላቶች ድጋፍ የሚገኝበት አግባብ ችግሩን ሊቀርፈው ይችላል የሚል ግምገማ መያዙን መኮንኑ ነገረውናል።

በጦርነቱ ወቅት ትህነግ 500 ሚሊዮን ዶላር ከግብጽ ተበርክቶለት እንደነበር ያወሱት እኚሁ መኮንን፣ አሁንም የሚታሰበው ይኸው ድጋፍ እንጂ ሌላው መስመር ብዙም ተስፋ የሚሰጥበት እንዳልህነ አመልክተዋል። አክለውም አሁን ባለው ሁኔታ ትግራይ ውስጥ የሚቀጥል ነገር እንደማይኖር አመልክተዋል። ዝርዝር ግን አልተናገሩም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ በሆኑት የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደን ቢሮ በመያዝ በውል የመፈንቅለ ስልጣን ይዘት ያለው እንቅስቃሴ ያደረጉት ወገኖች መሸነፋቸው ተሰምቷል። ታደሰ ወረደ እንቅስቃሴውን አስቀድመው ያውቁ እንደነበር ያስታወቁት ወገኖች፣ በቅርቡ ተካሂዶ የነበረውን ሰልፍና ተቃውሞ ተከትሎ ታደሰ ወረደ የሾሙት አዲ የፖሊስ ኮሚሽነር፣ “ልዩ ስሪት” ወይም ልዩ ኃይል በሚል አዲስ ያቋቋሙት ኃይል ሁሉንም ጉዳይ በጥምረት ይቆጣጠረው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቀዋል።

የቀድሞ ሰልፍ ተመሳሳይ ይዘት ቢኖረውም በሁሉም የአርሚ ክፍሎች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄው በመቀጣጠሉ ነገሩን ተረባርበው ለራሳቸው ህልውና ሲሉ ለማርገብ እንደተገደዱ ያስታወቁት የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪዎች፣ ሰሞኑን የተሞከረው ተመሳሳይ እንቅስቃሴ የተለያዩ ፍላጎት ባላቸው ሚዲያዎች ከመጦዙ ውጪ እዚህ ግባ የሚባል ኣልነበረም።

አሁን ላይ ታደሰ ወረደ ደስታ ሆቴል የሚገኙ ሲሆን እየተጠቀሙ ያሉት ቢሮ ” አዲ ሃውሲ” በሚባለው ሆቴሎ ግድም በሚገኝ የምክትላቸው ቢሮ ነው። ለአሸናፊው ወገኖች ቅርበት ያላቸው እንዳሉት ታዘው በጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ሰበብ ቢሮ ወረው የነበሩት ሰማኒያ የማይሞሉ ታጣቂዎች ለህግ ይቀርባሉ። ይህንኑ አስመልክቶ አስተዳደሩ ዛሬ፣ ግፋ ቢል ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ አመልክተዋል።

በአክሱም ሊረሳ የማይችል የጅምላ ጭፍጨፋ የፈጸመው ሻዕቢያ የአክሱም ጽዮንን ዓመታዊ ክብረ በዓል ተከትሎ 200 የሚጠጉ ካህናትን በማሳተፍ ጭፍጨፋውን በኃይማኖታዊ ስነ ስርዓት ለመቋጨት በአክሱም ከተማ ከከነ ሞንጆሪኖ ቡድን ጋር ተሰብሰበው የወሰኑትን ውሳኔ ታደሰ ወረደ መሻራቸው ይታወሳል። የትግራይ ቲቪና ድምጸ ወያኔ ጭፍጨፋውን አስመልክተው የዘገቡት ዘገባ ሻዕቢያን ክፉኛ ማበሳቸቱን Gጠቅሰም መዘገባችን አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...