የፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች የሰላም ስምምነት ለመፈጸም መስማማታቸው ተሰማ፤ የበታች ታጣቂዎች እጅ እየሰጡ ነው፤ የሚሾሙ አሉ

Date:

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት /አፋህግ/ አመራር ማስረሻ ሰጤ መካከል የተፈረመውን የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተከትሎ ከጎንደር፣ ጎጃምና ወሎ የተለያዩ አደረጃጀቶች በተመሳሳይ ወደ ሰላም መንገድ እያቀኑ መሆኑ ተሰምቷል። ታጣቆዎች በከፍተኛ ቁጥር እጃቸውን እየሰጡ መሆኑ ታውቋል።

የታችኛው ታጣቂ በማይረዳውና ግልጽ ሳይደረገለት የፋኖ አመራሮች ከሻዕቢያና ትህነግ ጋር በጋራ መስራት መጀመራቸው በተወሰኑት አመራሮች ደረጃ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር በተለያዩ አገባቦች ሲገለጽ ቆይቷል። አሁን ላይ የሰላም ስምምነት የፈረመው ማስረሻ ሰጤ ይህንኑ አስመልክቶ ” ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር አያስፈልግም” በማለት ድርጊቱን ከባንዳነት ጋር በማያያዝ ከስምምነቱ በሁዋላ ታናግሯል።

አዲስ ሪፖርተር ከሁለት ሳምንት በፌት በኮሎኔል ሙሃባ የሚመራው የፋኖ ኃይል ወደ ሰላማዊ መንገድ ለማምራት ወስኖ አንዳንድ ጉዳዮችን እየጠበቀ እንደነበር ጠቅሰን ጽፈን ነበር። ይህን ኃይል ጨምሮ በጎጃም ዘመነ ካሴ የሚመራውን ጨምሮ በጎንደር የእነ ሃብቴ፣ በወሎ ምሬ ወዳጆች የሚመራው ፋኖ የማስረሻ ሰጤን ዱካ እየተከተሉ መሆኑን አዲስ ሪፖርተር አረጋግጣለች።

የወሎው ኃይል እየገባ መሆኑ አዲስ ሪፖርተር ስታረጋግጥ ቀሪዎቹም በቅርቡ የሰላም አማራጩን በመቀበል እንደሚገቡ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አመልክተዋል። ከሚገቡት መካከል የተወሰኑ ኃላፊነት እንደሚሰጣቸው እነዚህ ወገኖች ጠቁመዋል።

በውጭ አገር ሆነው ከተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር እንደሚሰሩ የሚናገሩ፣ በከፈቱት ሚዲያዎች ጦርነትና የአማራ ክልልን አለመረጋጋት ሲዘገቡ የነበውሩና እይዘገቡ ያሉ አሁን ላዩ የተጀመረው የሰላም ስምምነትን አስመልክተው የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን “ባንዶች” በማለት እየፈረጁ ይገኛሉ። አንዳንዶቹም መግለጫ እያሰራጩ የሰላም ሂደቱ እንዲቋረጥ እየቀሰቀሱ ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አንቀጽ 39 «እስከ መገንጠል» እና «ያለገደብ» የሚሉ ድንጋጌዎች እንዲሰረዙ ስምምነት ተደረሰ -ሪፖርት

"እስከመገንጠል" የሚለው እና ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና ከጅምሩ የተቃወመው...

የጋራ መድረክ በሻዕቢያ እንደሚመራ ሰብሳቢው አረጋገጡ፤ “ኢሳያስ እየረዱን ለምን ተቃውሞ ይሰነዘራል”

አዲስ ሪፖርተር - ራሱን "የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የጋራ የትግል...

በችኮላ የሚወጡ ሕጎች የሕግ አወጣጥ ሥርዓቱን እያዳከሙ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋት ላይ የተካሄደ ጥናት፣ በችኮላና...