በወንጀል በተገኘ ሐብት የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 – በወንጀል የተገኘ የትኛውም የሃብት ፍሬ በሕግ የማገድ ስራ ጥብቅ ክትትል እየተደረጉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲኾን ከዚሁ ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ አምስት ግለሰቦች በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሕገወጥ የሰዎችዝውውር ጋር በተገናኘም ጥብቅ የሕግ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲኾን በዚሁ ረገድ ከዓለማቀፍ የሕግ ማእቀፎች ጋር የሚስማሙ ሕጎችን እየረቀቁ እንደሚገኙ የፍትሕ ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የሩብ አመቱ የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ገልጿል።
 
ይሁንና፣ የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘውን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተገናኙ ያሉ ወንጀሎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚነገር ጉዳይ ሲኾን ይህን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል በመግታት ረገድ የሕግ አካላት በኩል ክፍተቶች  እየተስተዋሉ ናቸው በሚል ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወቀሳ ቀርቦበታል ተብሏል።
 
በቅርቡ እየተበራከተ የመጣውን እና የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘውን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት ጥብቅ የሕግ ክትትል እየተደረገ እንዳልሆነ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ማሳሰብያ እንደቀረበበት ታውቋል።
 
ቋሚ ኮሚቴው፣ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትና አመኔታ ያለው የፍትሕ ስርዓት መገንባት የሚያስችል በተለይም ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ጥብቅ የሕግ ክትትል እንዲደረግ የጠየቀ ሲኾን ይሁንና አሁን ያለው ሕግ አፈፃፀሙን ማሻሻል የሕግ ጥናት ማርቀቅ እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
 
ቋሚ ኮሚቴው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማትን የ2018 የአንደኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በሰማበት ወቅት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚሳተፉ አካላት እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ኤጀንሲዎች ለሕግ በማቅረብ የሕግ ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ክፍተቶች እየተስተዋሉ መኾናቸውን አጥብቆ ወቅሷል።
 
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ኢሳ ቦሩ የስራ አፈፃፀሙን ውጤት መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው በዋነኝነት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በተለያዩ ተቋማት የተሰሩ ምርጥ የተባሉ ተሞክሮዎችን በመቀመር አልያም አቻ ተቋማት ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
 
በተጨማሪም፣ የፍትሕ ተቋማት በቀጣይ ለሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ የሲቪል ማሕበራትን ተሳትፎ ማሳደግ የተመለከተውን ጉዳይ ሲኾን በዚህ ኮሚቴው በሰጠው ቀነ ገደቦች ተሻሽለው እንዲቀርቡ ጠበቅ ያለ ማሳሰብያ መሰጠቱን ተገልጿል።
 
በቀጣይ ለሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ የሲቪል ማሕበራትን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዙ መደላድሎች መፍጠርን ጨምሮ  ሊደረጉ የሚገቡ ዝግጁነት ከወዲሁ እንዲጀመሩ ማሳሰብያ የተሰጠ ሲኾን የፍትህ ሚኒስቴር በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚጠበቅበትን የቤት ስራ እንዲወጣ ተጠይቋል።
 
የፍትሕ ሚኒስቴር በበኩሉ በግምገማ ወቅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ለቋሚ ኮሚቴው ባስረዳበት ሪፖርቱ የሕግ ጥናት ማርቀቅ አፈፃፀሙን ማሻሻልን ጨምሮ የጥብቅና አስተዳደር ጉዳዮችን፣ የአስተዳደር ፍትሕ እና የፌዴራል ሕጎች ተፈፃሚነትን የማሳደግ ስራዎች  ለማሻሻል ጥረት እየተደረጉ ናቸው ብሏል።
 
በተለይም፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ጥብቅ የሕግ ክትትል እየተደረገ መኾኑንና በሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ዙርያ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሶ ሆኖም የትብብር  ማእቀፎቹ የዲፕሎማሲ ግንኝኑነት የሚጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል።
 
በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ዳባ በሰጡት ማብራርያ መሰረት በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩ አካላት ተከታትሎ በህግ እንዲጠየቁ ከማድረግ አኳያ ከተለያዩ የሕግ አስፈፃሚ እና አለማቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰሩ  መሆናቸውን አስታውሰዋል።
 
በተጨማሪ በወንጀል የተገኘ የትኛውም የሃብት ፍሬ በሕግ እንዲታገድ የተደረገባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ እና ከዚሁ ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ አምስት ግለሰቦች በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን ሌሎች ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተመለከቱ ጉዳዮች
የሕግ ክትትል እየተደረጉባቸው መኾኑን ጠቅሰዋል።
 
ሚኒስትሩ ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተገናኘ ከአለማቀፍ የሕግ ማእቀፎች ጋር የሚስማሙ ሕጎችን እየረቀቁና ከአለማቀፍ የፍትህ ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራበት መኾኑን እና የወንጀሉ  መበራከት አሐዝ እየጨመረ መምጣቱን ግን አልሸሸገም ።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...