የውድቀት አዋጅ! በበድሉ ዋቅጅራ [የእነ ሰራዊት ፍቅሬ ክሽፈት]

Date:

እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?!


አዲስ ሪፖርተር – በመጀመሪያ ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡

ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡

የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ – ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡

ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ – ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ – ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል?

የትምህርት ስርዓታችን ማጥ ውስጥ ነው! በሙስና ተጨማልቀናል! የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡

በመጨረሻ
ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤ ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡:

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...