የብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ማሸነፉ በይፋ ታወጀ፤ ተቃዋሚዎችና የግል ተወዳዳሪዎች እስካሁን 49 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አግኝተዋል፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ በ7ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች ወንበሮችን በማሸነፍ በድጋሚ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘቱን አስታውቋል። ተቀናቃኝ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች አርባ ዘጠኝ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አግኝተዋል።

ቦርዱ በመላ ሀገሪቱ የተሰበሰቡትን ድምፆችና ኮንደክተሮችን በጥንቃቄ ሲመረምር ከቆየ በኋላ፣ ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ውጤቱን ይፋ ያደረገው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች 41፣ የግል ዕጩዎች ደግሞ 8 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል።

የብልጽግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተወዳደረባቸው ጠቅላላ ወንበሮች መካከል አብላጫውን 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ያሸነፈው ብልፅግና ይሁንታ ለሰጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋና አቅርቧል። በበላይነት በማሸነፍ ቀጣዩን የፌዴራል መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን ሕጋዊ ማግኘቱ ይበልጥ አደራ መሸከም መሆኑንም አመልክቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ፣ በአብዛኞቹ የሀገሪቱ ክልላዊ ምክር ቤቶች ውስጥ ሰፊ የአብላጫ ድምፅ ማግኘቱ ተረጋግጧል።

በዘንድሮው ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር እና ድምፅ የሰጡ ዜጎች መቶኛ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም በገጠርና በከተማ አካባቢዎች የነበረው ሰላማዊ የሕዝብ ተሳትፎ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማድረጉ፣ በምርጫው ሂደት ይህ ነው የሚባል ጥሰት ወይም ችግር አለመፈጠሩን ታዛቢዎች አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት ብልጽግና ፓርቲ የአሁኑን ምርጫ ሲያሸንፍ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። “ሕዝባችን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ሂደትን ማጽናት የሚቻለው በምርጫ ብቻ መሆኑን አሳይቷል!” silu ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በስነ ስርአቱ ላይ ተናግረዋል።

ፓርቲው ባወጣው የደስታ መግለጫ ለተሰጥው ድምጽና ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉ ምስጋና አቅርቦ ” ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር፣ ምርጫ የሥልጣን መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዟችንን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት አጠናክረን ለመቀጠል ለተከበረው ሕዝባችን ዳግም ቃላችንን እናድሳለን” ብሏል።

በከፍተኛ ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥና በሌብነት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ሲያስታውቅ የነበረው ብልጽግና አዲስ መንግስት ሲመሰርት እነማንን ወደፊት እንደሚያመጣ ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

ከትግራይ ክልል ውጪ አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ፓርላማ)

1. አዲስ አበባ ከተማ (23 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 20 መቀመጫዎች

– ኢዜማ 2 መቀመጫዎች

– የግል ዕጩ 1 መቀመጫ

2. አፋር ክልል (8 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 7 መቀመጫዎች

– የአፋር ህዝብ ፓርቲ 1 መቀመጫ

3. አማራ ክልል (ምርጫ የተካሄደባቸው 130 የፓርላማ መቀመጫዎች )

– ብልጽግና 117 መቀመጫዎች

– አብን 6 መቀመጫዎች

– አዲህን 3 መቀመጫዎች

– አርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ 1 መቀመጫ

– ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1 መቀመጫ

– ኢዜማ 1 መቀመጫ

– ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ

4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (9 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 8 መቀመጫዎች

– ጉሙዝ ብሔራዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ

5. ድሬዳዋ (2 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች

6. ጋምቤላ ክልል (3 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 3 መቀመጫዎች

7. ኦሮሚያ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 173 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና 167 መቀመጫዎች

– 5 የግል ዕጩዎች 5 መቀመጫዎች

– አዲስ ትውልድ ፓርቲ 1 መቀመጫ

8. ሐረሪ ክልል (2 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች

9. ሲዳማ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 16 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 13 መቀመጫዎች አሸንፏል

– መድረክ 3 መቀመጫዎች

10. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (20 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 17 መቀመጫዎች

– ኢዜማ 1 መቀመጫ

– ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ 1 መቀመጫ

– ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 1መቀመጫ

11. ደቡብ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 45 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 35 መቀመጫዎች

– ኢዜማ 7 መቀመጫዎች

– የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 1 መቀመጫ

– የወላይታ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ

– የግል እጩ 1 መቀመጫ

12. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 33 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልጽግና ፓርቲ 28 መቀመጫዎች

– ኢዜማ 2 መቀመጫዎች

– የግል ዕጩ 1 መቀመጫ

– ትብብር ለኢትዮጵያ 1 መቀመጫ

– ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ

13. ሶማሌ ክልል (22 የፓርላማ መቀመጫዎች)

– ብልፅግና ፓርቲ 19 መቀመጫዎች

– የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር 1 መቀመጫ

– ሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ 1 መቀመጫ

– ህብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ፓርቲ 1 መቀመጫ

ማስታወሻ ፦በትግራይ ክልል በ38 የፓርላማ መቀመጫዎች ምርጫ አለመከናወኑ ይታወቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related