[ከአያያዝ ይቀደዳል…] የፋኖ ታጠቂዎች ተሃድሶና መልሶ መቋቋም ጥንቃቄ ያሻዋል፤ የካቢላ ተሞክሮ

Date:

የኢኮኖሚ ሙሕሩ ፓል ኮሊን “The Botton Billion” በተሰኘው ድንቅ መፅሃፉ ታዳጊ ሃገሮች ለምን “በግጭት ወጥመድ” ውስጥ እንደሚቆዩ በምክንያትነት ያቀረበው የነፃነት ታጋዮች በትግል ውስጥ የሚያገኙት ጥቅም በሰላም ውስጥ ከሚያገኙት ስለሚበልጥ እንደሆነ ይገልጻል። የዲሞክራቲክ ኮንጎ Lord resistance Army መሪ የነበረው ሎሬታ ካቢላ በእርቅ ወደ ሲቪል ሰላማዊ ትግል እንዲገባ ተደርጎ ስልጣን በመጋራት የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ተሰጠው። አጅሬ ፕሬዝዳንት ኦፊስ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሂሳብ ሰራ። ጫካ ውስጥ እያለ ዳይመንድ እየሸጠ በሚሊየን ዶላር ያፍስ ነበር። አሁን ግን ወር ጠብቆ ከሚያገኘው ደሞዝና ጥቅማጥቅም ውጭ ሌላ ወፍ የለም። ምኑ ሞኝ ነው፣ ምክንያት ፈጥሮ እንደገና ጫካ ገባ ይለናል ፓል ኮሊን።

አዲስ ሪፖርተር – የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅ (አፋሕድ) የውጭ ጉዳይ ሃላፊና ስራ አስፈፃሚ አባል የነበረው ማስረሻ ሰጤ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ከፈፀሙ በኋላ በተለይም በጎንደርና አካባቢው የነበሩ የፋኖ አመራሮችና ታጣቂዎች በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰላማዊ ትግል በመለስ ለመንግስት የፀጥታ ሃይሎች እጅ እየሰጡ ይገኛል። ይህ የክልሉን ሰላምና ደህንነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከማስቻሉም በላይ በክልሉ የአባይ ተፋሰስ ወንዞች ላይ ለሚገነቡ የመስኖ ልማት ፕሮክቶች ያለምንም ፀጥታ ችግር ለመገንባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት የማተራመስ ሴራቸው እንዲከሽፍ ያደርጋል።

ሆኖም ግን መንግስት ወደ ሰላም የሚገቡትን የፋኖ ታጣቂዎችን የመሳሪያ ማስፈታት፣ መበተን እና ወደ ሲቪል ሕይወት መመልስ (Disarmament, Demobilisation and Rehabilitation) መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በታቀደ፣ በተደራጀ እና ገለልተኛ ታዛቢዎች ባሉበት ሁኔታ ተቀብሎ እየፈጸመ እንዳልሆነ ከመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች መረዳት ይችላል። በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ ይህን መርሃ ግብር በአግባቡ አለመፈፀም የሚያስከትለውን የሰላምና ፀጥታ ችግር ከሌሎች ሃገሮች ልማድ እና እንደሁም የፋኖ አመራሮች ወደ ሰለም መመለሳቸው የመንግስት የፀረ-ሽምቅ ወጊያ እንዴት እንደሚያግዘው እናያለን።
የነፃነት ትግል የሚያገረሽ ስለመሆኑ
የነፃነት ትግል የሚያገረሽ በሽታ ነው። በዋናነት ከሰው ልጅ ጥቅምና ኪሳራ ከማስላት ተፈጥሮው ይመነጫል። ጫካ ውስጥ እያለ የሚያገኘው ጥቅም አሁን እርቅ አውርዶ ሲቪል ሲሆን ከሚያገኘው ጥቅም ሊበልጥ ይችላል። መሳሪያ ማንገብ በራሱ የተለየ ውሳኔ ሰጭነት ሃይል ወይም ስልጣን ያጎናፅፋል። “ስልጣን ከአፈሙዝ ይመነጫል” ተራ አባባል አይደለም። አፈሙዝ የአመፃ ሃይል የመጠቀም መብትን (Monopoly of violence) ከመንግስት ጋር እንድትጋራ ያደርግሃል፡፡ ተቆጣጥረህ በያዝካቸው አካባቢዎች ገዥ ያደርግሃል፡፡ ገዥነት በውዴታና በግዴታ ታክስና ቀረጥ እንድትሰበስብ ያደርግሃል፡፡ ከውጭ ሃይል ገንዘብ፣ ትጥቅና ስንቅ እንድትሰበስብ ያስችላል፡፡ ትጥቅ ስትፈታ ‘የገዥነት’ እና የትዕዛዝ ሰጪነት ስልጣን ታጣለህ። ስልጣን ማጣትም ስሌት ውስጥ ይገባል። ‘
እንዲሁም ታጋዮች ደማቸውን በማፍሰስ ያገኙትን “የትግል ክብር” እና “ትልቅ ግምት” ሲያጡ፣ የተገለሉ እንደሆኑ ከተሰማቸው ወይም የሲቪል ሕይወታቸው ከነበሩበት የትግል ሕይወት የከፋ ከሆነ፣ ‘የለመድኩት ለምን ይቀርብኛል’ በሚል ስሌት ወደ ጫካ የመመለስ እድሉ ሰፊ ይሆናል። ለዚህም ነው፣ “የነፃነት ትግል የሚያገረሽ በሽታ” የሚባለው ነው።
ስለዚህ በስሌቱ መሰረት ገንዘባዊ ጥቅም፣ ውስኔ ሰጭነቱ እና የታጋይነት ክብሩ ከተጓደለብህ ተመልሰህ ወደጫካ የመግባት እድልህ ሰፊ ነው። የለመድከው ጥቅም ለምን ይቀርብሃል።
የቀድሞው የዓለም ባንክ የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር የነበረው ታዋቂው የኢኮኖሚ ሙሕሩ ፓል ኮሊን “The Botton Billion” በተሰኘው ድንቅ መፅሃፉ ታዳጊ ሃገሮች ለምን “በግጭት ወጥመድ” ውስጥ እንደሚቆዩ በምክንያትነት ያቀረበው የነፃነት ታጋዮች በትግል ውስጥ የሚያገኙት ጥቅም በሰላም ውስጥ ከሚያገኙት ስለሚበልጥ እንደሆነ ይገልጻል። የዲሞክራቲክ ኮንጎ Lord resistance Army መሪ የነበረው ሎሬታ ካቢላ በእርቅ ወደ ሲቪል ሰላማዊ ትግል እንዲገባ ተደርጎ ስልጣን በመጋራት የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ተሰጠው። አጅሬ ፕሬዝዳንት ኦፊስ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሂሳብ ሰራ። ጫካ ውስጥ እያለ ዳይመንድ እየሸጠ በሚሊየን ዶላር ያፍስ ነበር። አሁን ግን ወር ጠብቆ ከሚያገኘው ደሞዝና ጥቅማጥቅም ውጭ ሌላ ወፍ የለም። ምኑ ሞኝ ነው፣ ምክንያት ፈጥሮ እንደገና ጫካ ገባ ይለናል ፓል ኮሊን።
ከዚህም በተጨማሪ መሳሪያ አውርደው፣ ተሃድሶ ወስደው ወደ ሲቪል ሕይወት ገብተው ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀሉ ታጣቂዎቹም ስሌት ሰርተው መሳሪያ በመያዛቸው ብቻ ያገኙትን እየዘረፉ ሲበሉ ሲጠጡ የነበረውን የድሎት ኑሮ በሲቪሉ ሕይወት መልሰው ሊያገኙት ስላልቻሉ ተመልሰው አንጃ ሆነው ጫካ እንደገቡ ይገልፃል። የቀሩት በአልኮልና አደንዛዥ እፅ ተጠቂ ሆኑ። አዙሪት።

ይህ ልምድ ሊሆነን ይችላል

የኢትዮጵያ መንግስት በእርቅ ወደ ሰላማዊ ትግል ወይም ኑሮ የተመለሱ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅ (አፋሕድ) የውጭ ጉዳይ ሃላፊና ስራ አስፈፃሚ አባል የነበረው ማስረሻ ሰጤ እና ሌሎች በጎንደር አካባቢው የነበሩ የፋኖ አመራሮችና ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ትግል በበመለስ ለመንግስት የፀጥታ ሃይሎች እጅ እየሰጡ ይገኛል። በመሆኑም የነበሩበትን ባህልና ሰውኛ ባህሪ በአግባቡ መረዳት ይገባል። እንዲሁም በታቀደና በተደራጀ መልኩ መሳሪያ የማስፈታት፣ የተሃድሶ የሲቭል ሕይወት ልምድና የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል አለባቸው። ከተቻለ ስልጣን ማጋራት ወይም ተመጣጣኝ ኑሮ የሚመሩበት ገንዘብ ሊደጉማቸው ይገባል። ባዕድ ሆነው መታየት የለባቸውም። አካባቢያቸውን መምሰል ይገባቸዋል። ስለዚህ ለብለብ ሳይሆን ትክክለኛ DDR መርሃ ግብር ተቀርፆ ሊተገበር ይገባል።
የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እና የሌሎች ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች ወደ ሰላም መመለስ እና የታቀደና ዝቅተኛ መስፈርቶችን ያሟላ ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተንና መልሶ ማቋቋም (DDR) መርሃ ግብር ለመንግስት የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ስትራቴጂ የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ በሚከተሉት ሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ተደግፎ ቀርቧል። እነዚህ ዘርፎች የሽምቅ ተዋጊዎቹን የሞራልና የሕጋዊነት መናድ እንዲሁም ስልታዊ የመረጃ ብልጫ በማስገኘት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

የሞራል እና ሕጋዊነት ማዳከም

የከፍተኛ አመራሮች እና አባላት እጅ መስጠት የሽምቅ ተዋጊው ድርጅት በውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖረውን ተዓማኒነት በእጅጉ ያዳክማል። በፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጽንሰ ሐሳብ፣ ሕዝባዊ ድጋፍ የሽምቅ ውጊያ የጀርባ አጥንት ነው፤ ይህ ድጋፍ ሲጠፋ ድርጅቱ ይፈርሳል።

የትግሉን ሕጋዊነት (Legitimacy) ማጥፋት: ማስረሻ ሰጤ የትግሉን መሰረታዊ ችግሮች፣ በተለይም ከግል ጥቅም ባሻገር የዲሲፕሊን እጦት፣ የአላማ መዛባት እና በሲቪሎች ላይ የደረሱ አስከፊ ጥቃቶችን (እንደ ዝርፊያ፣ መደፈር እና ታግቶ ገንዘብ መቀበል) በይፋ ማጋለጣቸው የፋኖን የትግል ሞራል እና በሕዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት በእጅጉ ይጎዳል። ይህ ምስክርነት መንግስት ሽምቅ ተዋጊዎቹን “የጥቅም ፈላጊ ወንጀለኞች” በማለት ለመፈረጅ የሚያደርገውን የመረጃ ጦርነት (Information Warfare) ያጠናክራል። ሽምቅ ተዋጊው ድርጅት ሕጋዊነትን ሲያጣ፣ ለትግሉ ተጨማሪ አባላትን መመልመል እና ከሕዝብ እርዳታ ማግኘት ይቸገራል።

የሞራል ውድቀት (Morale Collapse): አንድ ከፍተኛ አመራር የነበረ ግለሰብ ትግሉን ጥሎ መውጣት፣ በሌሎች የታችኛው ደረጃ ታጣቂዎች ዘንድ የትግሉን አዋጭነት እና አመራሩን መጠራጠርን ይፈጥራል። ይህ የጅምላ ተስፋ መቁረጥ እንዲሰፍን ያደርጋል፣ ይህም ተከትሎ ሌሎች አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ ወይም የትግሉን ቦታ ለቀው እንዲሰደዱ ያበረታታል።
የአመራር ክፍተት: የቁልፍ አመራሮች መውጣት ድርጅቱ በስትራቴጂ፣ በሎጂስቲክስ እና በፋይናንስ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲዳከም ያደርጋል። የተበታተነ እና የሚተማመኑበት አመራር የሌለው የሽምቅ ውጊያ ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ውጊያ ማድረግ አይችልም።

ስልታዊ የመረጃ ብልጫ ማስገኘት እና የተሃድሶ ሚና

የከፍተኛ አመራሮች መመለስ ለፀረ-ሽምቅ ውጊያው ወታደራዊ እና ስልታዊ ብልጫ ለመውሰድ የሚያስችሉ ቁልፍ የመረጃ እና የንብረት ግብዓቶችን ያቀርባል።

ወሳኝ መረጃ ማግኘት (Actionable Intelligence): እጅ የሰጡ አመራሮች ስለ ሽምቅ ተዋጊዎቹ የውስጥ መዋቅር፣ የቁልፍ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራዎች፣ የገንዘብ ምንጮች፣ የሽፋን ቦታዎች (safe houses) እና የሎጂስቲክስ መስመሮች ወሳኝ እና ጥልቅ መረጃዎችን ያቀብላሉ። ይህ መረጃ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ (Asymmetrically) በሽምቅ ተዋጊዎቹ ላይ ትክክለኛ (Surgical) እና ፈጣን ወታደራዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።

የሰላም ማስፈን ስትራቴጂ ማጠናከር: መንግስት የDDR መርሃ ግብርን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሞከሩ ልምዶች መሰረት በአግባቡ መፈፀሙ፣ ለቀሩት ታጣቂዎች ሁሉ “የሰላም መንገድ አለ” እና “መንግስትም ተቀባይነት ያለው ምላሽ ይሰጣል” የሚል መልዕክት ያስተላልፋል። ስኬታማ የሆነ የዲዲአር ፕሮግራም የሽምቅ ውጊያውን ወደ ፖለቲካዊ መፍትሔ (Political Solution) እንዲሸጋገር በማበረታታት፣ የረጅም ጊዜ ወታደራዊ ወጪን ይቀንሳል።

የመንግስትን ተዓማኒነት ከፍ ማድረግ: መንግስት የቀድሞ ታጣቂዎችን በአክብሮት ተቀብሎ ሥነ-ልቦናዊ፣ ክህሎት ነክ እና የኢኮኖሚ ድጋፍ (DDR) ማድረጉ፣ በሕዝብ ዘንድ የመንግስትን አስተዳደራዊ እና ሰላም አስከባሪ አቅም ያጠናክራል። ይህ ደግሞ ሕዝቡ ከሽምቅ ተዋጊዎች ይልቅ ከመንግስት ጋር እንዲተባበር ያበረታታል።

በአጠቃላይ የማስረሻ ሰጤ እና የሌሎች ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች ወደ ሰላም መመለስ እና ተገቢው የተሃድሶና ማቋቋም (DDR) መርሃ ግብር መፈጸሙ ለመንግስት የፀረ-ሽምቅ ውጊያ (COIN) ስትራቴጂ ስልታዊና ሥነ-ልቦናዊ ድል ያስገኛል። ይህ ክስተት በዋነኛነት የፋኖን ሕጋዊነትና ሞራል ከውስጥ ያፈርሳል፤ ይህም የሚሆነው አመራሮቹ የትግሉን ሥነ-ምግባራዊ ጉድለቶች (እንደ ግላዊ ጥቅም እና በሲቪሎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን) በይፋ በማጋለጣቸው ነው። ይህ ምስክርነት የፋኖን ተዓማኒነት በሕዝብም ሆነ በራሳቸው ታጣቂዎች ዘንድ በእጅጉ ያዳክማል፣ ይህም ለሌሎች አባላት የሞራል ውድቀት በመፍጠር እጃቸውን እንዲሰጡ ያበረታታል። በተጨማሪም፣ እጅ የሰጡ አመራሮች ስለ ሽምቅ ተዋጊዎቹ የውስጥ መዋቅር እና የሎጂስቲክስ መስመሮች የሚያቀብሏቸው ጥልቅ መረጃዎች መንግስት ትክክለኛ (Surgical) ወታደራዊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያስችለዋል። ከዚህም በላይ፣ መንግስት የDDR መርሃ ግብርን (መሳሪያ ማስፈታት፣ ታሃድሶ ማስገባትና ወደ ሲቪል ሕይወት መመለስ) በታቀደ መልኩ መተግበሩ ለቀሩት ታጣቂዎች ሁሉ ‘የሰላም መንገድ አለ’ የሚል መልዕክት በማስተላለፍ የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ወጪን በመቀነስ፣ ግጭቱን ወደ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያመራ ይረዳል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...