በዲፕሎማሲያዊ ትስስራቸው 75 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙነት ዛሬ አዲስ ምዕራፍን ይዟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን በጉዞውም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ ሞዲን በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም እና በወዳጅነት ፓርክ ውስጥ በይፋዊው የጉዞ መርሃ ግብር ውስጥ ያልተካተቱ ፌርማታዎችን አስጎብኝቷቸዋል።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ረኢ”ታሪካዊ ጉብኝት” ብለው የሰየሙት የህ ታላቅ የዲፕሎማሲያዊ ትስስር ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን ለማጠናከር እና በተለወጠው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ ሚናዋን እንደገና ለመወሰን በምትራመደው እርምጃ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልፇል።
የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የተስተናገደው ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ እድገት፣ በቴክኖሎጂ እና በ”south south” ትብብር ላይ ያተኮረ የልማት አጋርነት ቁርጠኝነትን በማሳየት በ BRICS እና በሰፊው “Global south” ውስጥ እያደረገች ያለውን አቋም እንደሚያጠናክርም ይጠበቃል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በነገው ዕለት በፓርላማ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ እንደገለጹት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መካከል የሚካሄደው የውይይቱ ቁልፍ አጀንዳዎች፡
- ኢንቨስትመንትና ማኑፋክቸሪንግ፡
ሕንድ ለኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዋና ምንጭ በመሆኗ፣ በትብብር የሚተገበሩ የማኑፋክቸሪንግ እና የልማት ዕድሎችን ማሳደግ። - ግብርናና ማዕድን ልማት፡
የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን እና የማዕድን ዘርፍ ልማት በህንድ ተሞክሮዎችና ኢንቨስትመንት መደገፍ። - ዲጂታል መሠረተ ልማት እና ሳይበር ደኅንነት:
በዲጂታል ዘመን ያሉትን የጋራ ስጋቶች ለመከላከል እና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጠናከር በትብብር መሥራትን ያካትታል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝት ባለፉት 10 ዓመታት የሕንድ መሪ ምሥራቅ አፍሪካን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ነው።
Website፡ https://addisreporter.com/
Email፡ info@addisreporter.com
Telegram፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393






