የአብሮነት እና የግብፅ ድብቅ አጀንዳ – ኢትዮጵያን በሃይማኖትና በብሄር ግጭት የመበጥበጥ ኦፕሬሽን

Date:

ኢትዮጵያን ለማተራመስ ክርስቲያኖች ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲጠናከር አቅጣጫ ተቀምጧል። የፕሮፓጋንዳና ክፍል ክስ አመቻች ኃይል ተመስርቷል

አዲስ ሪፖርተር – በቅርቡ ተካሂዶ በነበረ ግምገማ “በኢትዮጵያ መንግስት ለማፍረስ በትጥቅ የታገዘው ሙከራ ውጤት አላስገኘም። ይህ መንግስት በጦርነት አይወድቅ” ከሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን በመረጃ አስገድፈን መዘገባችን አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ከተጀመረው የጠብ መንጃ ትግል ጎን  “በሰላማዊ ትግል” ሽፋን የሚሰሩ ቡድኖች በህቡዕ ክርስቲያኖች ላይ ያነጣጠረ የትርምስ አቅጣጫ እንደተሰጣቸው ተሰምቷል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ መረጃዎችን አሰብስቦ እንዳለው ከሆነ የተቀመጠውን አቅጣጫ የሚተገብረው “በሰላማዊ ትግል አምናለሁ” በሚለው አብሮነት አማካይነት ነው። አብሮነት ውስጥ የፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ፓርላማ አባልን ጨምሮ የጥይት ትግልን የሚደግፉና በኃላፊነት የሚመሩ በስራ አስፈጻሚነትና በቦርድ አመራር ውስጥ እንዳሉበት ራሱ ድርጅቱ ይፋ ያደረገውን የምርጫ ዝርዝር ጠቅሰን መዘገባችን ይታወቃል። ከአብሮነት የቦርድና የስራ አስፈጻሚዎች መካከል በተደጋጋሚ ቱርክ፣ ግብጽ፣ ኬንያና ሶማሊያ የሜመላለሱ መኖራቸውም የሚታውቅ ነው።

“የሃይማኖት ካርድን በመምዘዝ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የመንግስት ስልታዊ ጥቃት አድርጎ በማቅረብ፣ ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት እንዲያጣና በቁጭት ተነሳስቶ ለትርምስ እንዲጋለጥ ታቅዶ እየተሰራበት ነው” ሲሉ ለተባባሪያችን ያስታወቁት የአብሮነት የቦርድ አባል ናቸው።

ይህን መረጃ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሞሃመድ አብደላቲ በተደጋጋሚ “ኢትዮጵያ በናይል ተፋሰስ ላይ ተጨማሪ ግድብ እንዳትገነባ ባልተለመደ መልኩ (unprecedently) መልዕክት ልከናል” በማለት በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በኮድ ከተናገሩት ጋር በማያያዝ የአብሮነት አባሉ በርካታ ጉዳዮችን እያጤኑ መሆኑን አመልክተዋል።

“የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተናገሩትን ኮድ ለመፍታት ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልገውም” ያሉት የዘወትር የአዲስ ሪፖርተር መረጃ ተባባሪ፣ ሕዝብ ይህን አደገኛ አካሄድ እንዲያጤን አሳስበዋል።

የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትን “ኮድ” ይተባለውን ንግግር አስመልክቶ ያነጋገራቸው አብርሆትን የተለዩ ሌላ አባል፣ “ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን የተከሰቱ ግጭቶችን ኦዲት ማድረግ ወይም መቃኘት በቂ ነው። ሰሞኑን ጋምቤላ እና ወለጋ ውስጥ ከብሄር ጋር የተያያዙ ግጭቶች የተቀሰቀሰው ኢትዮጵያን ከውስጥ የመበጥበጥ ስትራቴጂ አካል መሆናቸውን መረዳት ብዙም አይከብድም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም ግጭቶቹ ለሕዝብ የሚቀርቡበት አግባብና ግጭቶቹን የሚያቀርቡት ሚዲያዎች የሚያሳዩት ስሜት ነገሩ መሪ ያለው፣ የተቀናጀ፣ በቅብብሎሽ የሚከወን መሆኑን እንደሚያሳብቅ አመልክተዋል።

የገዳዮችን ማንነት ወደኋላ በማለት የተገደሉት ንጹሃንን ለፖለቲካ ማገዶነት ሲጠቀሙ የነበሩ ኃይሎች፣ በተለይም የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አቅጣጫ መቀመጡን የአብርሆት ቦርድ አባል ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ ነገረዋል። ይህ ዕቅድ በስፋት እንዲተገበር አቅጣጫ ከተቀመጠም ሳምንታት ተቆጥሯል።

የኦፕሬሽኑን ዋና መሪዎች ስም ዘርዝረው መረጃውን ያጋሩት የአብሮነት የቦርድ አባል እንደሚሉት የተቀመጠው አቅጣጫ ግድያ ሲፈጸም ወዲያውኑ በመናበብ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በሚታወቁ የኤርትራ መንግስት የሚያስተዳድራቸው የዩቲዩብ አውዶች በስፋትና በፍጥነት እንዲሰራጭ ይደረጋል። |ትንተና የሚሰጡ የሚታወቁ የትርምሱ አክተሮች ግድያውን መንግስት እንደፈጸመው በማስመሰል ክስ ለመስረት እየሰሩና መረጃ እያሰባሰቡ እንደሆን እንዲናገሩ ይደረጋል። በዚህም አካሄድ ሕዝብ ቅስቀሳውን ይጋታል” ሲሉም እንዴት በመናበብ እንደሚሰሩ አስታውቅዋል።

መረጃውን የሰጡት የአብሮነት ቦርድ አባል፣ ይህ ኦፕሬሽን ውጤታማ እንዲሆን የዲያስፖራው ማህበረሰብ ዋና “አቀጣጣይ” እና “አስተጋቢ” ሆኖ እንዲያገለግል ይደረጋል። ዲያስፖራው በሀገር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በማህበራዊ ሚዲያ እና በዩቲዩብ በኩል ሰፊ ሽፋን በመስጠት፣ ግድያዎቹ የተፈጸሙበትን ትክክለኛ ሁኔታ በማዛባት እና መንግስትን ወንጀለኛ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ይደረጋል።

በቅርቡ ስብስቡን ጥለው እንደሚወጡ ያስታወቁት እኚሁ መረጃ አቀባይ ለዲሲ ተባባሪያችን “ዕቅዱ በሰላማዊ ትግል ስም የሚፈጸም፣ ሕዝብን ሆድ በማስባስና በማበሳጨት ለማነሳሳት ቁልፍ ስትራቴጂ  ሆኖ በቅንጅት የሚሰራበት ኦፕሬሽን ነው” ብለዋል። የአርሲውን ግድያ አስመልክቶ አዲስ ሪፖርተር በሰራችው ተደጋጋሚ ዘገባ “የንጹሃንን ግድያና ደም የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ማገዶ በማድረግ በመናበብ የሚሰራ ሴራ ነው” በሚል የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማነጋገር መዘገቧ አይዘነጋም።

አቶ ልደቱ የሚመሩትና ቀደም ሲል ስራ አስፈጻሚዎቹ ህቡዕ እንደሚሆኑ የተነገረለት አብሮነት፣ ከውስጥ በተነሳ ተቃውሞ ሳቢያ ስራ አስፈጻሚዎቹን ገሃድ ማድረጉ አይዘነጋም። መረጃ የሰጡት እንዳሉት አሁን ላይ ሲያስቡት ስራ አስፈጻሚዎቹ ህቡዕ እንዲሆኑ የተፈለገበት ምክንያት በሰላማዊ ትግል ስም ይህን መሰል አደገኛ ኦፕሬሽኖች ለማካሄድ ከነበረ ዕቅድ የተነሳ መሆኑ ዘግይቶ እንደገባቸው አመልክተዋል።

ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ “በገፊና ጎታች” ስልት ሲፈጸሙ የነበሩ ግድያዎችና ግድያዎቹን ተከትሎ የሚፈጠሩ ቀውሶች ሆን ተብለው የሚመረቱ፣ በቅንጅትና በመናበብ በሚዲያዎች የሚሰራጩ፣ በሚታወቁና በማይታወቁ የማህበራዊ ገጾች በቅብብል ወዲያው አገር እንዲያዳርሱ የሚደረጉ መሆናቸውን ጉዳዩን ያጠኑ ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል።

ቀደም ሲል ከ360 ጋር አብረው ይሰሩ የነበሩ ይህን አስመልክተው ምስክርነት መስጠታቸውን አብነት አድርገው መረጃውን ያካፈሉት የአብሮነት ቦርድ አባል፣ ሰሞኑን የአሜሪካ ምክር ቤት አንደራሴዎችን በግልና በአካባቢ እንዲጀነጅኑ ወይም ሎቢ እንዲደረጉ ለቦርድ አባላት ደብዳቤ እንደተሰራጨላቸው አመልክተዋል።

እሳቸውን ጨምሮ ለሁሉም የቦርድ አባላት በኤሜል የተበተነው ደብዳቤ እንደራሴዎችን መወሰወስን ጨምሮ ኢትዮጵያ ላይ እንዲጸድቅ የሚፈለገው ህግ የተቀመጠበት ነው። በዚሁ ዕቅድ መሰረት በተለይም አስቀድሞ ከሚደረገው በላይ ግድያ እንዲፈጸምና “ኦርቶዶክሳዊያን ተገደሉ” በሚል ሰፊ ዘመቻ እንዲካሄድ የተደራጀ የሚዲያ የቅብብሎሽ መረብ ተዘጋጅቷል

የዲያስፖራው ሚና እነዚህን አደገኛ እንቅስቃሴዎች “የፍትህ ጥያቄ” ወይም “የሃይማኖት ነፃነት ትግል” በሚሉ ስሞች ሽፋን በመስጠት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከእውነታው በተቃራኒ እንዲረዳ ማድረግ ቢመስልም ዋናው ጉዳይ ሌላ እንደሆነ የቦርድ አባሉ አስረድተዋል። “ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ሰላም በማናጋት እና ህዝብን ከህዝብ፣ ኃይማኖትን ከኃይማኖት ህዝብን ከመንግስት ጋር በማጋጨት፣ በሚፈጠር ትርምስ ሃገሪቱ በናይል ተፋሰስ ላይ ያላትን የልማት ሉዓላዊነት እንዳታስከብር የማዳከም ስራዋን በዲያስፖራው አጋዥነት በስፋት የምታከናውነብት ነው” ብለዋል።

ይህ ዲያስፖራው ተቆጥቶ በገንዘብ እና በፕሮፓጋንዳ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ በማቅረብ፣ በክስና በአቤቱታ ታጅቦ የሚካሄደው አደገኛ ኦፕሬሽን፣ በምስራቅ ኢትዮጵያ አዲስ የጦር ግንባር ለመክፈት ከባዕዳን መንግስታት ጋር ግንኙነት ካላቸው የተፈረከሱ የኦብነግ፣ ኦነግ እና የሶማሌ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እንዲሰሩ አቅጣጫ እንደተቀመጠላቸው ከአብሮነት ቦርድ አባል ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

“በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በከፋ ዕቅድ መታገል አልፈልግም፣ ሌላ ቸግር በማያስከትልና የኃይማኖት ልዩነት በመፍጠር እርስ በርስ በሚያባላ ሴራ ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ መታገል እንደሚገባን ግን አምናለሁ። አብሮነትን የተቀላቀልኩትም ለዚሁ ነበር” የሚሉት ኢኚሁ የቦርድ አባል “አብሮነት ውስጥ በጠብ መንጃ የሚያምኑ፣ በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ተኩስ እንዲጀመር ከኦጋዴንና ኦነግ ኃይሎች ጋር እንዲሰሩ ልዩ ኃላፊነት ከባእዳን አገራት የወሰዱ የኦነግ አባላትና የሶማሌ ፓርላማ አባላት አሉበት። ሌሎችም ትስስሮች አሉ” ሲሉ የሚያውቁትን ሃቅ በግርድፉ ተናግረዋል።

በበሕዝብ ዘንዳ ተአማኝነት ለመገንባትና የዲያስፖራውን ድጋፍ ለማኘት ተለይም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ሎቢስቶችን እና በሃይማኖት ስም የተደራጁ ቡድኖችን በመጠቀም፣ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ በተለይም ኦርቶዶክሶች ላይ ረገጣ እንደሚፈጽም በማስመሰል ጫና እንዲያሳድር ለማግባባት ስራ መጀመሩን እኚሁ መረጃ አቀባይ አመልክተዋል።

“የናይጄሪያን ሁኔታ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ “በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እየጠፉ ነው” የሚል የሀሰት ትርክት ለአሜሪካ ኮንግረስ አባላት  በማቅረብ፣ ሃገሪቱ ማዕቀብ እንዲጣልባትና ከዲፕሎማሲያዊ መድረክ እንድትገለል ለማድረግ ዲያስፖራው እንደ ዋነኛ መሣሪያነት እየተጠቀመበት ያለ ቢመስልም ዋናው አጀንዳ ህዝብን አስቆትቶ አገር ማተራመስ ነው” ያሉት የአብሮነት ቦርድ፣ በዚሁ አግባብ ከፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ጋር መነጋገራቸውንና “አብሮነትን እናፈርሰዋከን፣ ለስልት ነው እዚያ ያለነው” በማለት ሌላ የትህነግ ወኪል የሆነ አባልን ስም ጠርተው እንደነገሯቸው አመልክተዋል።

አሜሪካ በናይጀሪያ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ተከትሎ የያዘችው ዓይነት አቋም በኢትዮጵያም ላይ እንድትይዝ ለማግባባት “መንግስት ክርስቲያኖችን በተለይም ኦርቶዶክሶችን እያጠፋ ነው” የሚል እንቅስቃሴና መጀመሩን አንዳንድ በጀርመን መንግስት ፍላጎትና ጥቅም ላይ ተንተርሶ የተመቋቋመው የአማርኛ ፕሮግራም ዘግቧል።

“ኦርቶዶክሳዊያንን እንታደግ፣ ኦእርቶዶክሳዊያን ላይ የሚደረግ ግድያ እንቃወማለን፣ ፍትህ ለኦርቶዶክሳዊያን” በሚሉ አሳቦች ላይ ያተኮረ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጅት፣ ተደራራቢ መግለጫዎችን ለማሰራጨት፣ በግል በያዙዋቸው የምክር ቤት አባላት አማካይነት የኢትዮጵያ መንግስትን ለማስፈረጅ የፕሮፕጋንዳ፣ የግል ሎቢ፣ እንዲሁም ተናቦ የሚሰራ የሚዲያ ዝግጅት መደረጉን የአብሮነት ቦርድ አባል ለአዲስ ሪፖርተር አመልክተዋል።

“በቅርቡ የሚታይ ሃቅ ነው” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉት የአብሮነት የቦርድ አባል፣ በአርሲ እንደሚደረገው ዓይነት ባለቤቱ የማይታወቅ ግድያ እንዲፈጸም የተያዘው ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ይህን መረጃ መስጠጠታቸው ቢያንስ ክህሊና ወቀሳ እንደሚያድናቸው አመልክተዋል።

አብሮነት ገና ሲጀመር ጀምሮ በተከታታይ በዝግ ስለሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች አዲስ ሪፖርተር በዝርዝር ስትዘግብ መቆየቷ አይዘነጋም። አቶ ልደቱን በተደጋጋሚ አስተያየት እንዲሰጡ በእጅ ስልካቸው ቢሞከርም ስልካቸው አንስተው ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም። እሳቸው በተደጋጋሚ “ሰላማዊ ትግል ብቻ” የሚል አቋም እንዳላቸው የሚናገሩ ፖለቲከኛ መሆናቸው ይታወቃል።

የትህነግን መፍረስና መዳከም በገሃድ ከአንድ አባልና አመራር በላይ የሚቃወሙት አቶ ልደቱ በአደባባይ ይህን ይበሉ እንጂ ከቦርድ አባላቱና ስራ አስፈጻሚዎቹ ስብጥር ጀምሮ አብሮነት በሰላማዊ ትግል የሚያምን እንደማይመስል አባላቱን ጠቅሰን በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም።

በአርሲ በተለያዩ ጊዜያት የተገደሉትን ዜጎች አስመልክቶ አዲስ ሪፖርተር የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን አነጋግራ በዘገበቸው ዘገባ ላይ “ለምን ስለገዳዮቹ ማንነት እንጠየቃለን” ማለታቸውን ጠቅሰን ነበር። ኦፌኮ “ጉዳዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ስለሆነ በራሳቸን መዋቅር እያስጠናነው ነው”  የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌም “ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን የማይፈልጉ ኃይሎች አሉ” በማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኃይማኖትን እንደተቋም ከማውገዝ ገዳዮቹ እንዲታወቁ ጫና ማድረግ ጠቃሚ እንደሆነ ማናገራቸው አይዘነጋም።

ከዝግጅት ክፍሉ – በዚህ ዜና ላይ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተቀመጠውን አዲስ አቅጣጫ እንዲያስፈጽሙ የተመደቡ አካላትን ስም ከመዘርዘር ተቆጥበናል። ዜናው አስደንጋጭ በመሆናቸው የዘለላቸው መረጃዎችም አሉ። በተደጋጋሚ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ፈቃደና ያልሆኑት አቶ ልደቱ ምላሽ ካላቸው በማናቸውም ሰዓት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናችንን ለማስታውቀ እንወዳለን።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...