“አብሮ ቤተ ክርስቲያን የማይሄድ ህዝብ በህብረት ስለማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ማቀድ ውድቀት ነው”ኢንጂነር ሙሉጌታ፤”እኛ የኮሙኒቲ ሰራተኞች አይደለንም” አቶ ነዓምን

Date:

“ኤሊቶች ስለተሰባሰቡ ህዝብ ዘሎ የሚጨፍር መስለን። እኛ ከተነጋገርን ህዝቡ ታርቋል ብለን ውስነን፣ ራሳችንን ልክ የሕዝብ ውክልና እንዳለን አድርገን አሰብንና ወደቅን / ፌይል አድረግን/ እንደተከፋፈልን ሰላማዊ ስለፍ ማሰባችን ልክ አልነበረም፣ ሰልፍ ማለት ህብረት መፍጠር፣ symbolic action ነው፤ ይህን መንግስት አቅልለን በማየት ሕዝቡ በአግባቡ እንዳይደራጅ አድርገናልእኛ ጋር ትልቅ ስህተትም ውድቀትም አለ፤ በአግባቡ የመራነው ዕቅድና ፕሮግራም አለ ብዬ አላምንም፤ ሌላውን በሌላ መድረክ እንነጋገራለን”

ስለ ግምገማው መግቢያ

አዲስ ሪፖርተር ዜና – ራሱን “የሰላማዊ እምቢተኛነት አደራጅ የጋራ ግብረኃይል” የሚለውና መቀመጫውን አሜሪካና አውሮፓ ያደረግው ቡድን በተለምዶ “የትርምስ አቀናባሪ ቡድን” በሚልም ይጠራል። በጁን 3 ቀን 2026 ባደረገው የዙም ስብሰባ ላለፉት አራት ወራት “በማንኛውም መንገድ ምርጫውን ማደናቀፍና ዕውቅና ማሳጣት” በሚል አጀንዳ ሲንቀሳቀስ የነበረውና አቶ ነዓምን በሻዕቢያ ውክልናቸው ሲመሩት የቆዩት እንቅስቃሴ ግምግሟል።

ከስብስቡ አስራ ሁለት አባላት በተገኙበት የውስጥ ግምገማ በተለይም ኢንጂነር ሙሉ ጌታና አቶ ልደቱ በቅድመ ምርጫ የነበራቸውን እንቅስቃሴ “ውድቀትና በትክክልኛ ስትራቴጂ ያልተመራ፣ እኛ ስለተሰባሰብን ሕዝብ አንድ የሆነ መስሎን በሞቅታ ስህተት ውስጥ የወደቅን” ሲሉ ግምግመዋል።

በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር ያለውን እውነታ በውል አለመረዳታቸውን በማንሳት የተከተሉትን መንገዶች ለማየትና (Self-criticism) ለማካሄድ የሞከረው ግምገማ ሰብሳቢው አቶ ያሬድ ስም እየጠሩ ሲካሄድ የተለየ አስተያየት ከሰጡት መካከል ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴም ይገኙበታል።

በውይይቱ ላይ በዋናነት የተሳተፉትና የተሰራውን ስራ እንደትልቅ በመቁጠር ሞቅታ ውስጥ መግባት እንደማይገባ ያመለክቱት በጎሉበት ግምገማ በአብዛኞቹ የተሰራውን የኮሙኒኬሽን ስራ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረቡትን ቃለ ምልልሶች፣ መግለጫዎች፣ ወዘተ “ታላቅ ስኬት” በማለት የመጀመሪያውን ተናጋሪ ኢንጂነር ግደይን ያቅረቡትን የአድንቆት አሳብ ሲያጎሉ፣ አቶ ልደቱ “ማለባበስ አያስፈልግም” በማለት የዓላማ አንድነት፣ የአንደበት መዘባረቅ፣ የእይታ መለያየት የነበረበት ግብረኃይል እንደሆነ ሶስት ጉዳዮችን በማንሳት ተችተዋል።

አሰደንጋጭና ያልተጠበቀ ግምጋማቸውን አቅርበው መቸረሻ ላይ “ይቅርታ ይህ የግል አቋሜ ነው። ይህን ማለቴ ኝ ከህብረቱ የመለየት አይደለም። ሌላውን በሌላ መድረክ እንነጋገራለን” ያሉት ኢንጂነር ሙሉጌታ ያቀረቡት የግምገማ ነጥብ ይህ ሪፖርት ይዘረራል።

የውድቀቱ እና “ክስረናል” የተባለለት የሰላማዊ ስለፎች ዝግጅት ሰንክሳር

ከቅርብ ጊዜ ውስጥ “ከሴቶች ጉዳይ ውጭ በሁሉም ኮሚቴዎች ስብሳቢ” በሚል ባልደረቦቻቸው የሚተርቧቸው አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ እያቆላመጡ የተገኙትን ካስተዋውቁ በኋላ ሶስት አጀንዳዎችን አቀረቡ። ከምርጫ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያ ስብሰባ መሆኑን ጠቁመው ስለ አራቱ ወራት እንቅስቃሴ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ስለተሰጡ ምላሾችና ስለቀጣይ እንቅስቃሴ መነጋገር በሚል አጀንዳ ሰፈሩ፤ አክለውም ለመግቢያ የሰላማዊ ሰልፎች የከሰሩበትን ምክኛቶች አብራሩ።

ግብረኃይል፣ ቴክኒክ ኮሚቴ፣ ነዑስ ኮሚቴዎች፣ ተቋቁመው ብዙ ከተደከመ በኋላ አብረውን የሚሰሩት ሳይቀር መረጃ ሳይሰጡ የአማራ አደረጃጀቶች ሰልፍ በማዘጋጀታቸው ለሚዲያና የሰላማዊ ሰልፍ ሽሚያ እንዳይመስል ስልታዊ ውሳኔ ተወስኖ የታሰቡት የዋሽንግቶንና የሎንዶን ሰልፎች መቅረታቸውን “የሚደነቅ ውሳኔ” ሲሉ ተናገሩ። የተሰራውን የኮሙኒኬሽን ስራ አድንቀው ዕድል ሰጡ።

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ መስራች ኢንጂነር ግደይ “የጠላቶቻችን ሚዲያ አዲስ ሪፖርተር ዝምቶብናል” ካሉ በኋላ እንዳስተዋወቃቸው በመጠቆም ሁሉም “አንደግመውም” ያሉትን የህዝብ ኝኙነት ስራና በየሚዲያው የተካሄደውን የግልና የቡድን ቃለ ምልልስ እንዲሁም መግለጫዎች አድንቀው በታላቅ ስኬት ገምግመዋል። ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ እንደተቀበለውም ገልጸዋል።

በሁለት አካውንት ስብሰባውን ተቀላቅለው ተራቸው ሲደርስ “ከሁለት ቦታ ነው ያለሁት ማን ነው ሃክ ያደረገኝ” በማለት ሞቅታ የፈጠሩትና በሻዕቢያ ውክልና የግብረኃይሉ መሪ አቶ ነዓምንም በተመሳሳይ የህዝብ ኝኙነት ስራውንና የሚዲያ አተቃላይ ዝመቻውን አድነቀው ምራር ወደሆነው የኢንጂነር ሙሉጌታ አሳብ ተገባ።

የኢንጂነር ሙሉጌታ ጠጣር ግምገማ ማህበራዊ ስብራት እና የስትራቴጂ ስህተቶች

ኢንጂነር ሙሉጌታ በግምገማቸው ወቅት፣ ስብስቡ የነደፋቸው አንዳንድ እቅዶች በህዝቡ ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ስሜትና የቁስሉን ጥልቅነት ያላገናዘቡ ስሜታዊ አካሄዶች እንደነበሩ ተናግረዋል።

  • የሰላማዊ ሰልፍ እቅድ ስህተትነት፦ በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ከፍተኛ መራራቅ ከግምት ሳያስገባ፣ ወጣቶችን በአንድነት አስተባብሮ የጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀድ ትልቅ የስልት ስህተት (Strategic mistake) እንደነበር በግልጽ ሊታመን እንደሚገባ ተናገሩ።
  • የማህበራዊ ግንኙነት መበጠስ ፦ በአሁኑ ወቅት በአማራና በትግሬ ማህበረሰብ መካከል ያለው ጥላቻና ጥርጣሬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና ይህ ሲነከባለል የኖረ ያልታከም ቂም እያለ አብሮ ስለመሰለፍ ማሰብ ስህተት እንደነበር ያወሱት ኢንጊነር ሙሉጌታ፣ ይህ መከፋፈል እስከ እምነት ተቋማት ድረስ ዘልቆ በመግባት አላስቻለም። እሳቸው በሚኖሩበት ከተማ የሚገኙ የሁለቱ ወገን ተወላጆች በአንድ ላይ አብረው ቤተክርስቲያን እንኳ መሄድ የማይችሉበት አስከፊ ሁኔታ እንዳለ አስረዱ። እንዲህ ባለው ስነ-ልቦናዊ ስብራት ውስጥ ወጣቶችን በአንድ አደባባይ ለማሰለፍ ማሰብ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር መጣላት መሆኑን አመልክተው “ ማንን እንኳን ለሰልፍ ይዘን እንደምንወጣ አናውቅም ነበር” በማለት ሲሞጋገሱ ለቆዩት ተናጋሪዎች የማይመች አሳብ እይታቸውን አቀረቡ። ኢንጂነሩ በየስብሰባው ቁልፍ የሆኑ የልዩነትና የመርህ ጉዳይ በማንሳት ከዶክተር ሚካኤል ቀትሎ የሚጠቀሱ ናቸው። የሚያውቋቸው “ካድሬ አይደሉም። ሰው ናቸው” ይሏቸዋል።
  • ስለ ኤሊቶች ስብስብ እና የተሳሳተው እሳቤ ፦ አቶ ነዓም ራሳቸውንና አቶ አባይን፣ አቶ ዘአማንን፣ እንደ ምሳሌ በማቅርብ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ሳይነጋገሩ የኖሩ በቀራረባቸው እንደ ትልቅ ጉዳይ ሊታይ እንደሚችል፣ በዚህ መቀራረብ “አገዛዙ ደንግጧል” በማለት ለተናገሩት “ኤሊቶች ስለተሰባሰቡ ህዝብ ዘሎ የሚጨፍር መስለን” በማለት እያታቸውን ከውድቀት አንጻር አቅርበዋል። “እኛ ከተነጋገርን ህዝቡ ታርቋል ብለን ውስነን፣ ራሳችንን ልክ የሕዝብ ውክልና እንዳለን አድርገን አሰብንና ወደቅን / ፌይል አድረግን/ ያሉት ኤንጂነር ሙሉጌታ “እንደተከፋፈልን ሰላማዊ ስለፍ ማሰባችን ልክ አልነበረም፣ ሰልፍ ማለት ህብረት መፍጠር፣ symbolic action ነው” በማለት የስብሰቡ ዋና ዓላማ መክሸፉን በይፋ ተናግረዋል። “ይህን መንግስት አቅልለን በማየት ሕዝቡ በአግባቡ እንዳይደራጅ አድርገናል” በማለት ግምጋማቸውን ያኖሩት ኢንጂነሩ፣ “እኛ ጋር ትልቅ ስህተትም ውድቀትም አለ፤ በአግባቡ የመራነው ዕቅድና ፕሮግራም አለ ብዬ አላምንም፤ ሌላውን በሌላ መድረክ እንነጋገራለን” በማለት ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

አቶ ነዓምን ለኢንጂነር ሙሉጌታ የውድቀት ግምገማ እንደ ኃላፊና የላካቸው ክፍል ወኪል ምላሽ ሰጥተዋል። ሻዕቢያ በውጭም ሆነ በአገር ቤት ህዝብ አንድነት እንዲፈጥር ፍላጎት እንደሌለው፣ አብዝቶ የሚሰራውም በዚሁ አግባብ መሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ “እኛ ፖለቲከኛ እንጂ የኮሙኒቲ ሰራተኞች አይደለንም ህዝብ እንዲቀራርብ የምንሰራው” በማለት “መስመራቸውን” ጠብቀው ተናገሩ። አክለውም አስፈላጊ ከሆነ ኮሚቴ እንደሚቋቋም አመልከቱ።

መረጃውን ለአዲስ ሪፖርተር የዲሲ ተባባሪ ያቀበሉት ተሰብሳቢ እንዳሉት ኢንጂነር ሙሉጌታና አቶ ነዓምን አንድ መድረክ ላይ መገኘታቸው “የዘመን ያለህ ያሰናል” ሲሉ አቶ ነዓምን በሰጡት ምላሽ ከመገረም የተነሳ “ምነው ዝም ቢሉ” ያሉ በዝተዋል። የፖለቲካ ስራ ከህዝብ ጋር እንደሚሰራ ገና ያልገባቸው አቶ ነዓምን በየስብሰባው በማዕረጋቸው ሳቢያ በዚህ የአስተሳሰብ ደረጃቸው አቅጣጫ ሰጪ፣ መስመር አስተካካይ፣ አስተባባሪና መሪ መሆናቸው የግምገማው የሹክሹክታ መነጋገሪያ እንደነበርና አመልክተዋል።

ከግምገማው በፊት አዲስ ሪፖርተር የዘገባቸው ዘገባዎች በግብረኃይሉ የዋጽ አፕ ገጽ ላይ ተለጥፈው እንደነበር ያወሱት የመረጃው አጋሪዎች፣ አቶ ያሬድም የሰባዊ መብት ተከራካሪ እንደሆኑ በመጥቀስ “አማራ ተሰደደ፣ በማንነቱ ተጠቃ፣” በማለት እንጃዋርን በመቃወም ብዙ እንዳላሉ በግሩፑ ገጽ ላይ ጃዋርን አወድሰው “ስለ አርሲው ግድያ ጥሩ ጻፈ” ብለው ማጋራታቸውን በትዝብት አመልክተዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪ ጃል መሮ አማካሪና ቃል አቀባይ አቶ ጂረኛና ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ከወራት በኋላ “ተበትናችኋል በሚል ለስድብና ትችት ተጋልተናል። ከኦእሮሞ ጋር መስራት አይቻልም በሚል አቶ ነዓምን ተናግረዋል በሚል የአገዛዙ ደጋፊዎች ዘመቻ ከፍተዋል። አለመበተናችንን ለማሳየት በሚል ተለምነው ስብሰባውን መሳተፋቸው ታውቋል። ህዝቅዔል በመኪና እየተጓዙ መሆናቸውን ጠቅሰው በተቆራረጠ ድምጽ ስለምርጫው ለማናገር መረጃ እንደሚያስፈልግ ከማስታውቅ በዘለለ ያሉት ነገር አልነበረም። አቶ ጂሬናም እንደ ሌሎቹ ተመሳሳይ አስተያየት ከመስተት የዘለለ ያሉት ነገር የለም። በግምገማው ስለ አርሲው ጭፍጨፋ ለአማራ ህዝብ ወኪሎች ማብራሪያ እንዲሰጡ የተየቃቸውም ሆነ ጉዳዩን ያነሳ አልነበረም።

የአቶ ልደቱንና የዶክተር ኢሳማኤል ጎርሴን ግምገማ በተከታይ እናቀርባለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ካጃዋር ጋር ገጥመው የነበሩት አቶ ነዓምን ከተረኛ ኦሮሞዎች ጋር መስራት እንደማይቻል አስታወቁ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ምርጫ እንዳይደረግ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግና...

ከግብጽ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው ነእፓ በአማራ ክልል ምርጫው እንዲደገም ጠየቀ

አዲስ ሪፖርተር - ከግብጽ ጋር የሚታማው ነፃነትና እኩልነት...

አውሮፓ ህብረትና፣ ካናዳ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ ምርጫውን “እንቀበለዋለን” አሉ

አዲስ አበባ አዲስ ሪፖርተር — የአውሮፓ ህብረት ልዑክ፣...