ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

Date:

አዲስ ረፖርተር ዜና – አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው ያሰባቸውን ሰልፎች ያቋረጠው የአመጽ አደራጅ ግብረኃይል ሊሰጠው ያሰበው ጋዜጣዊ መግለጫ ለረቡዕ ተላለፈ። መግለጫው የተላለፈው አቶ ነዓምንና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በኤርትራ ኤምባሲ በሚከበረው የነጻነት በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ነው። መግለጫው የሚሰጠው የእስልምና ተከታዮች የኢድ በዓል በሚያከብሩበት ዕለት ነው።

በበአሉ ላይ የሚገኙት እነዚሁ ክፍሎችና ሌሎች ተጋባዦች “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ ናት፣ ኢትዮጵያዊያን የኤርትራን ህዝብ ጨቁነዋል” የሚል ምስክርነት እንደሚሰጡ ያስታወቁት ባልደረቦቻቸው “መንግስትን ብንቃወምም፣ በፊት ቀርቶ ‘ነጻነት’ ካሉ በኋላ እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለአንዳች ሃሳብና ልዩነት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኤርትራውያን ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ እያየን አገራችን በመካድ መቆም ከሞራል አንጻር ትክክል አይደለም” በሚል ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ለሻዕቢያ ድግስ ሲባል የራስን ስራ መተው ከጀርባ ጉዳዩን ማን እንደሚመራው ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል።

መግለጫውን እንዲሰጡ የተመደቡት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ ዶክተር እስማኤል ጎርሴ፣ መምህር ደምሰው እና አቶ አባይ ነበሩ። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ የግብረኃይሉን አባል ጠቅሶ እንዳለው ከተመደቡት አምስቱ መግለጫ ሰጪዎች መካከል ፈቃዳቸውን ያልተጠየቁ፣ መመደባቸውን የማያውቁ፣ ይገኙበታል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ “ከማን ጋር እንደምንዋጋ የገባን አይመስለኝም። ሁልጊዜ እያጣጣልን የምናየው ጉዳይ እየጎዳን ነው። ተላልፎ መሰጠትም ሊኖር ይቻላል” በማለት በመጨረሻው ስብሰባ ላይ የተናገሩት ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን መግለጫ ከሚሰጡት አምስት ሰዎች ምካከል ተመድበው “አልችልም” በማለታቸው የህወሃት ባልደረባቸው አቶ አባይ እንዲተኳቸው ተደርጓል።

ምርጫ እንዳይካሄድ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ በሻዕቢያ አደራጅነት በግብጽ ሙሉ ደጋፍ የተቋቋመው ግብረኃይል በሳምንት ሁለትና ሶስቴ ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ ማቋረጡን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። በፖርት ሱዳን ግብጽ በምትመራው ኢትዮጵያን የማፍረስ ዕቅድ ስብሰባ ላይ በፖርት ሱዳን የተደረገውን ስብሰባ ተከትሎ የሃሳብ መከፋፈል የገጠመው የአቶ ነዓምን ቡድን በግልጽ የሻዕቢያ እቅድ አስፈጻሚ መሆኑን ማረጋገጣቸውን የገለጹ “ተሸውደን ነበር” ማለታቸው አይዘነጋም።

ከሱዳን፣ግብጽ፣ኤርትራ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለመውጋት የተመሰረተውን “ጽምዶ” የተባለ ህብረት የተቀላቀሉት ፊትለፊት የሚታዩትና በውክልና የሚንቀሳቀሱትን በመቃወሙ የአቶ ነዓምን ቡድን ያሰበውን መስራት የማይችልበት ደረጃ በመድረሱ የድህረ ምርጫ ዕቅድ መያዙን አዲስ ሪፖርተር ዘግባ ነበር።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በሻዕቢያ የሚመራው የእነ ነዓምን ዘለቀ ግብረ ኃይል ተበተነ፤ ስብሰባ፣ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ ስለፍ በይፋ ቆመ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ ተደራጅቶ...

[ሞዐ ተዋህዶ] አዲስ የድህረ ምርጫ ህዝባዊ አመጽ ዕቅድ በኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ቀረበ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት በተቀመጠው አግባብ...

አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ምን እያሰቡ ነው? “አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር ፍላጎት ማሳካት ህልውናዋ ነው”

ኢትዮጵያ የቀጥታ የባህር ዳርቻ ባይኖራትም፣ በወታደራዊ አቅሟ እና የባህር...