ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ አዲስ የጦር ህብረት “ጽምዶ”መሰረቱ፤ “መከላከያ ይበተናል” የእነ ነዓምን ዘለቀ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ከሸፈ፤

Date:

ራሳቸውን ከትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ፣ እስክንድር ከሚመራው የፋኖ የውጭ ጉድዳይ ኃላፊነት እና ከፋይናንስ አሰባሳቢነት ማግለላቸውን አስታውቀው የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ አዲስ የጦር ሕብረት ወይም “ጽምዶ” መሰረቱ። የእነ አቶ ነዓምን ዘለቀ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ እንደከሸፈ እና አቶ ልደቱ በትነውት የነበረውን አብሮነትን ዳግም ማንቀሳቀሳቸው ተሰማ።

አዲስ የታጣቂዎች ጽምዶ የመሰረቱት የ84 ዓመቱ አቶ ሻለቃ ዳዊት የተጠቀሰውን የታጣቂዎች ህብረ መመስረታቸውን ያስታወቁት እንዲካተቱ የፈለጓቸውን ቡድኖች ሲያነጋገሩ በሰጡት ማብራሪያ ነው። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ ሪፖርተር እንዳለው ሻለቃ ዳዊት በጽምዶ እንዲካተት ላሰቡት የአፋር ተወላጅ ከሰጡት የማግባቢያ ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል፣ የአማራ፣ የኤርትራ፣ የሱዳን፣ የኦሮሞ ታጣቂ ኃይሎች የስምምነት ውል አስረዋል።

“አሁን የቀሩት የደቡብ፣ የአፋርና የሶማሌ ታጣቂዎችን ማካተት ነው” በማለት ለአፋር ተወላጅ የውስወሳ ማብራሪያ እንደሰጡ ለተባባሪያችን ያስታወቁት ግብዣው የቀረበላቸው የዲሲ አፋር ተወላጅ ናቸው። ሻለቃ ዳዊት የበጀትና የሎጂስቲክ ችግር እንደማይኖር፣ በቅርቡም የትግራይ ኃይሎች እንደሚካተቱበት እንደነገሯቸው መረጃውን የሰጡት አመልክተዋል።

በደርግ ወታደራዊ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ መኮንን የነበሩት ሻለቃ ዳዊት፣ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን (RRC) ኮሚሽን በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ በ1977 ዓ.ም የተከሰተውን አስከፊ ረሃብ ለመታደግ የተሰበሰበ የእርዳታ ገንዘብ ይዘው የኮበለሉና በ”ክህደት” የተመደቡ ናቸው። ከረሃብተኞች ጉሮሮ ነጥቀው ከመኮብለላቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሻለቃ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት በመሰረቱት ግንኙነት ኢትዮጵያ ላይ ክህደት እንደፈጸሙ በተደጋጋሚ በመረጃና ማስረጃ ይከሰሳሉ።

አሁን እንደ አዲስ የሚመሰረተው እና እሳቸውና የሻዕቢያ ኃይሎች የሚመሩት አዲስ የታጣቂዎች ሕብረት ይፋ ሲሆን ዲያስፖራው ገንዘብ እንዲያዋጣ በይፋ ዘመቻ እንደሚጀመር የጋምቤላ ተወካይ ሆነ ህብረቱን የተቀላቀሉትን የሚቀርቡ እሳቸውን ጠቅሰው ለአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ተናግረዋል።

አርበኛ እስክንድር ነጋ በይፋ በሰጣቸው የውጭ ግንኙነት ኃላፊነታቸው “በፋኖ ስም የዲያስፖራውን ዶላር በመሰብሰብ ለግል ጥቅምና ሀገር የማፍረስ ዓላማ ለሚንቀሳቀሱ የውጭ ኃይሎች (በተለይም ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለሚደረግ ግንኙነት) ድልድይ በመሆን እየሰሩ ነው” የሚል አብረዋቸው በሚሰሩ የፋኖ ባልደረቦቻቸውና ለዚሁ ስራ በተቋቋሙ ሚዲያዎች ተቃውሞ ተነስቶባቸው የነበረው ሻለቃ ዳዊት ራሳቸውን ከገንዘብ ማሰባሰብም ሆነ ከማንኛውም የፋኖ ትግል ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀው ነበር።

በዲያስፖራ ውስጥ ካሉት የሻዕቢያ ተባባሪና ወኪሎች መካከል ክርሻለቃ ዳዊት ቀጥሎ ዋና ወኪል የሚባሉትና ራሳቸውም በተለያዩ ቡድኖች ስብሰባ ላይ ይህንኑ በይፋ የሚናገሩት አቶ ነዓምን ምርጫውን ለማስተጓጎል የተለያዩ ግብረኃይሎች አቋቁመውና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር አጣምረው ሲመሩት የነበረው አመጽ መክሸፉን ተከትሎ ሻለቃ ዳዊት አዲስ ጥምረት እንዲመሰርቱ መደረጉን መረጃውን ያካፈሉት አመልክተዋል።

ሻለቃ ዳዊት የአፋሩን ተወላጅ ሲያገባቡ ጥምረቱ ከተጠናቀቀና ይፋ ከሆነ በኋላ ግፋ ቢል በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ብልጽግና የሚመራው መንግስት እንደሚወገድና የሚተማመንበት መከላከያ እንደሚበተን ገልጸዋል። ሻለቃ ዳዊት የኢትዮጵያ መከላከያ እንዲበተን ሆነ ብለው እንዲከሽፍ ተደርጎ የተዘጋጀ መፈንቅለ መንግስት አደራጅተው የኢትዮጵያ ምርጥ ጄኔራሎች እንዲረሸኑ ትልቁን ስራ የሰሩ መሆናቸው አይዘነጋም። ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሱዳን ሆነው መፈንቅለ መንግስቱን ይመሩ እንደነበር መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ዓላማው የኢትዮጵያን መከላከያ ለሁለተኛ ጊዜ መበተንና መንግስት ማፍረስ እንደሆነ ገለጸው የአፋሩን ወኪል ያግባቡት ሻለቃ ዳዊት፣ የሶማሌና የደቡብ ክልል ታጣቂዎችን ከተካተቱ በኋላ የጽምዶው ስም እና የህብረቱ አባላት በይፋ ለሐዝብ ይፋ ሆኖ ኦፕሬሽኑ እንደሚጀመር አመልክተዋል። የእነ አቶ ነዓምን መንገድ የማያዋጣና የከሸፈ በመሆኑ ወደ እሳቸው ስብሰብ መግባት ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኢትዮጵያ የምርጫ ዋዜማ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዛቢዎችና ሚዲያዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች አቀኑ፤

አዲስ አበባ አዲስ ሪፖርተር ዜና - ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ...

“የብልጽግናን ሚስጢራዊ መረጃ ማግኘት አለመቻላችን እየፈረካከሰን ነው” የግብረኃይሉ አባላት፤

የኢሳያስ ዝምታ በጽምዶ አባላት ውስጥ ቅሬታና ልዩነት አስነሳ አዲስ...

ስቴት ዲፓርተመንት የህወሃትን የውጭ ግንኙነት ኃላፊዎች “የአደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በስምምነት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ...