በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የመሬት ባለቤትነት፣ የግብር ቅናሽ እና የህዝብ ቆጠራ ጥብቅ መነጋገሪያ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገለጸ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በምክክር ጉባዔው ከመሬት ይዞታ እስከ ደመወዝ ግብር ያሉ አጀንዳዎች ላይ ምክረ ሀሳቦች መቅረባቸው ታውቋል። በ1999ኙ የህዝብ ቆጠራ ሳቢያ ያጣነውን በጀት ይካካስ የሚል ጥያቄ በምክክር ጉባዔው መነሳቱ ተነግሯል። በሀገራዊ ምክክሩ የደመወዝ ግብር እንዲቀነስ እና የታችኛው ወለል ተከፋዮች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ መጠየቁ ተብራርቷል። የመሬት ባለቤትነት በሦስት አማራጭ እንዲደራጅ የሚሉ ሀሳቦች በምክክር ጉባዔው መቅረባቸው ተገልጿል

በይፋ ከተከፈተ 26 ቀናት ባስቆጠረው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ እና አርብቶ አደር ጉዳዮች በሚለው አጀንዳ ስር የመሬት ባለቤትነት፣ የግብር ቅናሽ እና የህዝብ ቆጠራ ውዝግብ ዋና ዋና መነጋገሪያ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገለጸ።

በጉባዔው ተሳታፊዎች በኩል ከመሬት ይዞታ እስከ ደመወዝ ግብር ያሉ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሀሳቦች መቅረባቸው ተመላክቷል።

በተለይም የመሬት አጠቃቀምን በተመለከተ የአርሶ አደሮች የግል መሬት፣ የአርብቶ አደሮች የወል መሬት፣ የሃይማኖት ስፍራዎች እንዲሁም የደን፣ የወንዝ እና የማዕድናት ቦታዎችን አጠቃቀም የሚደነግግ የሕግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መጠየቁ ተገልጻል።

የመሬት ባለቤትነትን በተመለከተም መሬት የግል፣ የወል እና የመንግስት እንዲሆን በሦስት አማራጭ ሀሳቦች መቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ መሬት የመንግስት ወይም የግል ብቻ መሆኑ የሚያስከትላቸውን ስጋቶች ለማስወገድ የሚያስችል አሰራር እንዲዘረጋ በ250 የውይይት ቡድኖች መጠየቁ ታውቋል።

በሌላ በኩል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ በሀገራዊ ምክክሩ የደመወዝ ግብር እንዲቀነስ እና የታችኛው ወለል ተከፋዮች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ መጠየቁ ተገልጻል።

አነስተኛ ደመወዝ በሚከፈላቸው ሰራተኞች ላይ የሚጣለው ከፍተኛ ግብር ሊቃለል እንደሚገባና ፍትሃዊ የሀብት እና የመሰረተ ልማት ክፍፍል በሁሉም ክልሎች እንዲኖር ተመካካሪዎች አሳስበዋል።

በ1999 ዓ.ም በተካሄደው የሕዝብ ቆጠራ ወቅት ሕዝባችን በትክክል አልተቆጠረም በሚል ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልል ተሳታፊዎች ቅሬታ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በቆጠራው ሳቢያ ያጣነውን በጀት ይካሰስ የሚል ጥያቄ በምክክር ጉባዔው መነሳቱ ተመላክቷል።

በቀጣይም የሕዝብ ቆጠራው በገለልተኛ አካል እንዲከናወን የሚል ሀሳብ በስልታዊ የውይይት ቡድኖች መቅረቡ ተገልጻል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አገራዊ ምክክሩን ለማሰናከል ስምሪት ተሰጠ፤ ኮሚሽኑ በአንድም አጀንዳ የመወሰን ስልጣን እንደሌለው አስታወቀ

አዲስ ሪፖርተር - አገራዊ ምክክሩ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በአገሪቱ...

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ መሪነት ወደ አፍሪካ ኃያልነት እየተሸጋገረች ነው፤ ፈርስት ፖስት

አዲስ ሪፖርተር - ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)...

“ኤርትራ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ አረጋግጣለች” ኢንጂነር ግደይ የትህነግ መስራች

አዲስ ሪፖርተር - ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ...