“ዓብይ አህመድን ገዳይ አድርጎ ገዳይንና ሟቸን እኩል ማጀገን በሚል ሤራ ተማምነን አዲስ ትርክት ፈጠርን” ሲል የሰጠውን ምስክርነቱን የሚያረጋግጠው የዶክተር ዳኛቸው ገለጻ፣ ሤራውን የሚያሳጣ ከበረዶ የነጣ መረጃ ቢሆንም ሃብትሽ ባላየ አልፎታል። እንደ “ሚዲያ ሰው” ቢያስብ ኖሮ እሳቸውንም ሆነ የቀድሞ ባልደረባውን በዝርዝር በሞገተ ነበር። እንደ ሰማሁት ከሆነ ይህ ሤራ ሲጎነጎን ሃብትሽ የተነፈሳት ሁሉ በድምጽ ተይዛለች። እናም ከዚህ በላይ እላፊ አይሄድም።
አዲስ ሪፖርተር – ቀደም ሲል ለወራት ዝግጅት ተደርጎበት የተፈጸመው የአማራ ክልል ባለስልጣናት እና የጄኔራል ሰዓረ ግድያ በአገር ደረጃ መጥፎ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለወደፊትም ትውልድ ዋጋ እንዲከፍልበት ተደርጎ መቅረቡ አግባብ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ከተለያዩ ወገኖች አስተያየት ሲቀርበበት ነበር። ዛሬም ድረስ የክልሉ ፍትህ ቢሮ የጀመረውን ምርመራ እንዳያተናቅቅ ማን እንደከለከለው ይፋ አለመጠየቁን የሚናገሩ ልክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲተየቁ ያሳስባሉ። በወቅቱ ክልሉን ሲመሩ የነበሩና ሃላፊዎችና የድርጅቱ መሪ አቶ ደመቀ መኮንን በገሃድ መረጃ እንዲሰጡ መገደድ እንዳለባቸው የተለያዩ ወገኖች አሁንም ይጠይቃሉ።
ይህንኑ ግድያ ከኢትዮጵያ ሳይሆን ከአሜሪካ ቨርጂንያ ዛሬ በሌብነት ተካሰው የተበታተኑት የዩቲዩብ ባለቤቶች ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብለው “አዲስ ትርክት እንፍጠር” በማለት ተስማምተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የወንጀሉ ባለቤት ለማድረግ እንደጽማሙ አዲስ ሪፖርተር ከሚዲያው ሰዎች ውስጥ ሁለት ምስክሮችን ጠቅሳ ከአሜሪካ መዘገቧ አይዘነጋም።
“የ ሦስትን ወደ አራት የፈጠራ ትርክት ውልደት በቨርጂኒያው ዳማ ሆቴል በ 360 ስቱዲዮ እስከ አራት ኪሎ” በሚል ርዕስ አዲስ ሪፖርተር ባዘጋጀችው ዘገባ ባለስልጣናቱ ሰኔ 15 ቀን የተገደሉበትን አግባብ እንዴት አጣመው እንዳቀረቡት ስንዘግብ ዋናውና ቁልፉ የትርክት ሽምጠጣ ምክንያት ገንዘብ ነበር። የጉዳዩ ዋና ባለቤትና “ሴራው አብይ ላይ ይለጠፍ” በማለት ከሃብታሙ አያሌው ጋር ስምምነት የደረሰው ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። ኤርሚያስና ሃብታሙ “የሞቱት ጎንደሮች ናቸው። አብዛኛው ዴያስፖራና የገቢ ምንጫችን ጎንደሮች ናቸው። ስለዚህ ጎንደሬዎችን ይዘን ለመቀጠል ሴራውን አብይ ላይ እናድርገው ብለን ተስማማን” በማለት ሃቁን እዛው ዋሽንግተን ዲሲ የተገኘው የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ አረጋግጧል። በዚሁ መነሻ ግድያው በተፈጸመ ማግስት ማታ ዐቢይ አህመድ ሰለባ ሆኑ።
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በባህር ዳርና በአዲስ አበባ በተደረገው ጥቃት የሠራዊቱ ጠቅላይ አዛዥ ጄነራል ሰአረ መኮንን፣ ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበበ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ እና የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴ ጨምሮ ሌሎች የተገደሉበትን አገባብ አስመልክቶ ለአሚኮ አስተያየት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ “በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሰኔ 15ቱ የከፍተኛ አመራሮች ግድያ አንዳች ግብ ያላሳካ መጥፎ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው” ብለውታል።
በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ የተከሰተው አሳዛኝ ድርጊት በስሑት የመረጃ ግምገማ እና በሁለት እግር ለማንከስ በተደረገ የፖለቲካ ስሌት የተከሰተ ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስታወቁት ወቅቱን እንዴት ያስታውሱታል በሚል ተጥየቀው ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሚኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በወቅቱ ያጋጠመውን ሁኔታ ሲያብራሩ ድርጊቱ ለሀገር ለውጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን እንደ ዶክተር አምባቸው እና ጄኔራል ሠዓረ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ኃይሎችን ያሳጣ፣ በፖለቲካ አመራሩ መካከል የነበረውን መተማመን ያቀዘቀዘ እና በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግን አጥፊ የፖለቲካ ባሕል ያስቀጠለ መሆኑን ክፉ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። አክለውም እንዲህ ያለው ተግባር አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እያንዣበበ ያለውን አደገኛ የትርክት ስብራት ያስከተለ እንደሆነ ተናግረዋል።
ገዳይም ሟችም በእኩል ደረጃ በጀግንነት የሚወደሱበት ሁኔታ አደገኛ የፖለቲካ ብዥታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ታሪክን እያንሻፈፉ እና እየመረጡ ማቅረብ የነገውን ትውልድ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ታሪክ እንዳለ በትክክለኛው መንገድ መቀመጥ እንዳለበት አሳስበዋል።
የሰኔ 15ቱን ክስተት አስመልክቶ በወቅቱ ስለተሰጠው መግለጫ ሲራገቡ የነበሩት የሴራ ትንተናዎችም እውነቱን ለመቅበር የሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ ድርጊቱ ከጅምሩ ምንም ግብ ያላሳካ እና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጠባሳነቱ የሚታወስ ዘግናኝ አጋጣሚ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ከቢሯቸው ሲወጡ መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸው ልህዝብ ይፋ እንዲሆን ፋና፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና አሚኮ ማታ ላይ ቢጠሩም እንዳልመጡ፣ ይሁን እንጂ አሚኮ ቢሮው አራት ኪሎ አጠገብ በመሆኑ ወዲያው በመገኘቱ ከትንሽ ጥበቃ በኋላ “አሚኮ ለሌሎችም ያጋራል” በሚል መገለጫውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሰጡ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መግለጫው የተሰጠው ከባህር ዳር እንደሆነ ተደርጎ ሲዘገብ እንደነበር አስታውሰዋል።
“ዐቢይን ተድርጊቱ ፈጸሚና አቀናባባሪ እናድርገው” ብለው የወሰኑት ሚዲያዎች በሰሩት የፈጠራ ትርክት “ካስገደላቸው በኋላ እዛው በህር ዳር ሆኖ መግለጫ ሰጠ” በማለት በተደጋጋሚ ሲናገሩ በተለያዩ የዩቲዩብ አግባብ ሲያሰራጩ እንደነበር ይታወሳል።
ወንዝን ለመሻገር አብሮ መዋኘት እንጂ ውኃውን መውቀስ አይበጅም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ለለውጥ ሂደቱ የሚያሳዩት ድጋፍ መቀያየሩ ከተሳሳተ ስሌት፣ ከግል ጥቅም እና ለጥያቄ ምላሽ ከማጣት የመነጨ ሊሆን እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ይህ የጎራ መደበላለቅ በአማራ ዳያስፖራ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አካባቢዎች ተወላጆች ዘንድ በስፋት የሚታይ ዝንባሌ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ወጥ ያልሆነ ተለዋዋጭ ድጋፍ ሦስት መሠረታዊ መነሻዎች እንዳሉት ጠቅሰው፣የመጀመሪያውና ዋነኛው የተሳሳተ ስሌት የነበራቸው ግለሰቦች የሚያሳዩት ባሕሪ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ለውጡን በግላቸው እንዳመጡት በማሰብ የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ ለማሳካት የሞከሩ አካላት፣ ለውጡ የብዙዎች ጥረት እና መስዋዕትነት ውጤት መሆኑን ሲረዱ እና ፍላጎታቸው ሳይሳካ ሲቀር ጎራቸውን እንደሚቀይሩ አብራርተዋል። ሂደቱን በግል መነጽር ብቻ በመመልከት የሕዝብን ፍላጎት ለማድመጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ ኃይሎች መኖራቸውንም አንስተዋል።
በተጨማሪም ዩቲዩብን ጨምሮ ከተለያዩ የዲጂታል ትስስር ገጾች ለሚገኝ የገንዘብ ጥቅም እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት ሲሉ ብቻ ለውጡን ለማንቋሸሽ የሚሰለፉ አካላት መኖራቸውን አመልክተዋል።
እነዚህ ግለሰቦች ወደ ሀገር ቤት መጥተው ለውጡን ሲመለከቱ በመጸጸት እውነታውን ቢመሰክሩም፣ ሲመለሱ ግን ለጥቅም ሲሉ ዳግም ወደ ቀድሞ አፍራሽ አቋማቸው እንደሚመለሱ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሀቀኛ ጥያቄ ኖሯቸው በበቂ ሁኔታ ምላሽ ያላገኙ እና ስጋት የገባቸው ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ በዚህ በኩል የመንግሥትም ክፍተት ሊኖር እንደሚችል አልሸሸጉም።
ሀቀኛ ጥያቄ ያላቸው አካላት በቀጣይ መከተል ስላለባቸው አቅጣጫ ባስተላለፉት መልዕክትም፣ መፍትሔው ተቀራርቦ አብሮ በመሥራት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን አመላክተዋል።
ለውጥን ከዳር ቆሞ በመተቸት ብቻ ማሳካት እንደማይቻል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ወንዝን ለመሻገር አብሮ መዋኘት እንጂ ዝም ብሎ ውኃውን መውቀስ አይበጅም” በማለት ሁሉም አብሮ በመዋኘት ለሀገር ግንባታ የድርሻውን እንዲያበረክት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዜጎች ለወቅታዊ ፈተናዎች እጅ ሳይሰጡ ለሀገር ዘላቂ ጥቅም በጽናት ሊቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እና የዘመኑን የመረጃ ፍሰት በአግባቡ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት መረጃ በዋናነት በብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ብቻ ይገኝ የነበረ መሆኑን አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን የኢንተርኔትና የዳታ ስርጭት በመስፋፋቱ እንዲሁም በርካታ ትንታኔ ሰጪዎች በመፈጠራቸው ወቅቱን በጥንቃቄ መረዳት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
ለውጥ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ዜጎች ራሳቸውን እያስተማሩ እና ከሁኔታዎች ጋር እያስማሙ መጓዝ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክረዋል።
ጫናን መቋቋም አቅቷቸው ለጊዜያዊ ችግሮች ሸብረክ የሚሉ አካላት እንዳሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለርካሽ እና ጊዜያዊ ነገር ሲባል ከትልቅ ሀገራዊ ቁም ነገር መጉደል እንደማይገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ሁሉም አካል ታሪክ መሥራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ማተኮር እንዳለበት፣ ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቢያንስ ከታሪክ ቀኝ መቆም እንጂ በአቋም መዋዠቅ የሀገርን ጥቅም አደጋ ላይ መጣል እንደማይገባ አስገንዝበዋል።
እውነታው በሂደት እና በተጨባጭ ሥራዎች እየተገለጠ እንደሚመጣም እምነታቸውን ገልጸዋል።
የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዜጎች ለወቅታዊ ፈተናዎች እጅ ሳይሰጡ ለሀገር ዘላቂ ጥቅም በጽናት ሊቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እና የዘመኑን የመረጃ ፍሰት በአግባቡ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት መረጃ በዋናነት በብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ብቻ ይገኝ የነበረ መሆኑን አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን የኢንተርኔትና የዳታ ስርጭት በመስፋፋቱ እንዲሁም በርካታ ትንታኔ ሰጪዎች በመፈጠራቸው ወቅቱን በጥንቃቄ መረዳት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
ለውጥ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ዜጎች ራሳቸውን እያስተማሩ እና ከሁኔታዎች ጋር እያስማሙ መጓዝ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክረዋል።
ጫናን መቋቋም አቅቷቸው ለጊዜያዊ ችግሮች ሸብረክ የሚሉ አካላት እንዳሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለርካሽ እና ጊዜያዊ ነገር ሲባል ከትልቅ ሀገራዊ ቁም ነገር መጉደል እንደማይገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ሁሉም አካል ታሪክ መሥራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ማተኮር እንዳለበት፣ ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቢያንስ ከታሪክ ቀኝ መቆም እንጂ በአቋም መዋዠቅ የሀገርን ጥቅም አደጋ ላይ መጣል እንደማይገባ አስገንዝበዋል። እውነታው በሂደት እና በተጨባጭ ሥራዎች እየተገለጠ እንደሚመጣም እምነታቸውን ገልጸዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






