ኩምሩክና ሸረሪና እንደ ማግኔት የሚሳሳቡ ድሎች፤ የRSF/TASIS ኃይሎች ተጨማሪ ከተሞችን ተቆጣጠሩ፤ ድሉ ለ”ጽምዶ” አባል አገራትና ቡድኖች መርዶ መሆኑ ተሰማ

Date:

ኩምሩክ ከRSF/TASIS ኃይሎች ላይ ስትነጠቅ፣ ከሸረሪና የሚነሳው የህወሃት ኃይል በቀጥታ ወደ ሁመራ፣ ከጀርባ ያለው መንገድ የሚጠረግለት ታጣቂ ደግሞ ከደጀን ኃይሉ ጋር ወደ ቤኒሻንጉል የሚያኮበኮበኩብበት ቀን በጉጉት ይጠበቅ ነበር። ሸሸረሪና በአገር መከላከያ እጅ በወደቀች ቀናት ልዩነት ኩምሩክ ከጄኔራል አብደል ቡረሃን እጅ ተነጥቃ በRSF/TASIS እጅ ስትወድቅ ድሉ “እንደ ማግኔት” የሚሳሳብ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግተም። ይህ “ጽምዶ” ለተባሉት አገራት፣ ቡድኖችና ታጣቂዎች ከነደጋፊዎቻቸው መረዶ የሆነ ዜና ዙሩን እያከረረ ነው። ህውሃትም ፊቱን ወደ ራያና አፋር አቅጣጫ ….

አዲስ ሪፖርተር – የሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) በጄነራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን መሪነት ኩርሙክን በድጋሚ ተቆጣጥረው እንደነበር ይፋ የተደረገው በፈረንጆች March 2025 አጋማሽ ላይ ነበር። ዜናው ታዲያ የህወሃትን ደጋፊዎችና አመአሮች እንዲሁም በጽምዶ ውስጥ የታቀፉትን በሙሉ አስደስቶ ነበር።

በወቅቱ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በብሉ ናይል ግዛት ባደረጉት የተቀናጀ የጦርነት ዘመቻ ከተማዋን እና አካባቢዋን ከRSF/TASIS ኃይሎች አስመልሰው እንደነበር ሲዘገብ የህወሃት አርሚ 70 ኃይሎች ድሉን በጩኸትና በጭፈራ ሲያበስሩ የሚታዩ የቪዲዮ ምስሎችም በራሳቸው ላይቭ ተሰራጭተው ነበር።

ይህንኑ ድል ተከትሎ የህወሃት ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ጎን ለጎን የሚሰሙት ድምጾች “ሁመራ በቅርቡ” የሚሉ የድሉን መቃረብ የሚያመለክቱ ነበሩ። በተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚሰሙት የደጋፊዎች ድምጽ በተጨማሪ ዶክተር ደብረጽዮና እሳቸው የሚመሩት የህወሃት አንድ ስንጣቂ “በብልጽግና መቃብር ላይ እንቆማለን” በማለት በአደባባይ ስብሰባዎች ሲያስታውቁ ነበር።

ህወሃት “ትዕግስቴ አልቋል” በማለት ወደ ሙሉ ጦርነት እንደሚገባ ለደጋፊዎቹና ለዓለም እያሳሰበ ባለበት ቅጽበት ጠዋት በማለዳ ድምጸ ወያኔ “በሸረሪና የብልጽግና መንግስት ጭፍጨፋ ፈጸመበኝ” ሲል ዓለም እንዲሰማው መግለጫ አወጣ። የድል ብስራት ሲጠብቁ ለነበሩ ሁሉ አስደንጋጭ የሆነው “የአለቅን” መግለጫ በተሰማ በሰዓታት ውስጥ ከሸረሪና ግንባር “ሰበር ዜና” በሚል ሌላ ዜና ተሰማ።

ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ግድም አርሚ 70፣ አርሚ 15 እና አርሚ 13 በሚል ስያሜ የሚታወቁት የጦር አሃዶች፣ እንደ ወትሮው ሳይሆን ከጀርባቸው በቂ ደጀን ኃይል ተበጅቶላቸው፣ ሜካናይዝድ ኃይል ከፊት አሰልፈው ከሸረሪና ቤዛቸው ሙሉ ጦርነት ለመገጠምና ሁመራን በሰዓታት ጦርነት ለመቆጣጠር ሲሞክሩ ነው “ቀድሞ መረጃ ነበረው” የተባለው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትበከባድ መሳሪያ፣ ፈጣን፣ የተቀናጀ፣ ከሁሉም አቅጣጫ በሚሰነዘር፣ በአየርና በምድር የተደገፈ ጥቃት የከፈተው።

ይህን እርምጃ ተከትሎ የአገር መከላከያ ላለፉት አምስት አመታት በትህነግ እጅ የነበረውን ምሽግ፣ መሳሪያ፣ ስንቅ፣ ትጥቅ እና ሰራዊት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የሚያሳዩ መረጃዎች ይፋ ሆኑ። ምርኮኞች በስለፍ ታዩ፣ ቃላቸን ሰጡ። ውጊያውን ተረኩት። ህታናትና አዛውን ወዴት እንደሚሄዱና ለምን እንደሄዱ ባላወቁበት አግባብ ተርፈው ምስክርነት ለመስጠት በቁ። የሸረሪና ዜና በዚህ መልኩ ከተቋጨ በኋላ ከሱዳን ደጋፍ ሰጪ ኃይሎች ሌላ ዜና አስከተሉ። ኩምሩክ ተመልሳ በእጃቸው ወደቀች።

“ኦፕሬሽን ሸረሪና”፤ ከጀርባው ያዘለው ዕቅድ መዳረሻ የት ነበር? ከሸረሪናና ግዴማ ዲፖ የተገኘው መሳሪያ” በሚል ርዕስ አዲስ ሪፖርተር ባቀረበችው ልዩ ሪፖርት፣ ህወሃት ያቀደው ኦፕሬሽን፣ ይዞታን በማስፋት አንዱ ወገን ሁመራ መያዝ ከቻለ፣ ከጀርባ ደጀን ሆኖ የሚጥብቀው ኃይል ያሰፋውን አካባቢ ለሱዳንና ሻዕቢያ አስረክቦ ውስን ኃይሉን ከጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጥቂት ታጣቂዎች ጋር በማቀናጀት በጉሙዝ በኩል በመንደርደር ይዞታውን ማስፋት እንድነበር አመልክተን ነበር።

ይህ ዕቅድ የተሰራው ከህወሃት፣ ከሻዕቢያና ከግብጽ ጋር በጥምረት የሚሰራው የአልቡርሃን ኃይል፣ ኩምሩክን እንዲቆጣጠር በጣምራ ከተሰራ በኋላ ስለነበር፣ ሚስጢሩን የሚያውቁ “ደብቀነው እንጂ ሰበር ዜና አለን” በማለት እያሟሟቁ ነበር።

የታሰበው ሳይሆን የሸረሪና ኦፕሬሽን በተሰማው ዜና አግባብ በተጠናቀቀ በሳምንቱ የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ኩምሩክን ዳግም መቆጣጠራቸውን ትናንት አስታወቁ። ዛሬ ጠዋት ባወጡት መግለጫ ድላቸውን እያሰፉ የተለያዩ ከተሞችን መያዛቸውን ይፋ አደረጉ።

ኩምሩክ መሳሪያና ሽፍታ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍበት ቁልፍ ቦታ በመሆኗ የአልቡርሃን ኃይሎች ተሸንፈው ከአካባቢው መውጣታቸው ለኢትዮጵያ እፎይታ ሲሆን፣ ለህወሃት፣ ሻዕቢያና ግብጽ ግን ክፉ መርዶ ሆነባቸው። ባለሙያዎች እንደሚሉት አሁን ላይ ወደ ቤኒሻንጉል ለመግባት የሚያስብ ታጣቂ እድል የለውም። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ለምሰንዘር የታሰበውን ጦርነት ያከሽፈዋል።

እንደ እነዚሁ ባለሙያዎችና ጉዳዩን የሚከታተሉ ክፍሎች መግለጫ ህወሃት ፊቱን ወደ ራያ እና አፋር ግንባር ለማዞር እና በመረዋ በኩል ለመስረግ ወስኖ መንቀሳቀስ የሞከረው በሸረሪና በኩል አሁን ላይ የማይታሰብ በመሆኑ ነው።

በመረዋ በኩልም በተሰራ ኦፕሬሽን ህወሃት ጥቃት እንደደረሰበት ባመነው መሰረት በራያ እና አፋር በኩል ለመጀመር የታሰበው ጦርነት ምን ያህል እንደሚሳካ ህወሃት ብቻ እንደሚያውቀው የሚናገሩ ወገኖች፣ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ድንበር በማለፍ ግዛታቸውን እያሰፉ መሄዳቸው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል።

በሱዳን የፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) እና የህዝባዊ ነፃነት ግንባር-ስሜን (SPLM-N) በጥምረት ያቋቋሙት የሱዳን መስራች ጥረት (TASIS)፣ በብሉ ናይል ክልል ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውንና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለውን የኩርሙክ ከተማ በቁጥጥር ስር ማድረጉን ሲገልጽ ጥቃቱን አጠናክሮ እየገፋበት እንደሆነ አመልክቷል።

የTASIS ኃይሎች ከሱዳን የመከላከያ ኃይል (SAF) እና ከአካባቢው አጋር ታጣቂዎች ጋር ጠንካራ ውጊያ ካደረጉ በኋላ፣ ከደማዚን ከተማ በስተደቡብ 136 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኩርሙክንና ዋና ዋና የመተላለፊያ መስመሮችን በሙሉ መቆጣጠራቸውን አስታውቀው በቴሌግራም ገጻቸው ይፋ ባደረጉት ቪዲዮ ከፍተኛ የሰውና የቁሳቁስ ጉዳት ማድረሳቸውን አሳይተዋል። በርካታ የጦር ተሽከርካሪዎችን፣ መሣሪያዎችን እና ጥይቶችን ማርከዋል። ምሻግ ተቆጣጥረዋል።

የሱዳን ፈጣን ደጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) ዛሬ አርብ ባወጡት መግለጫ በሰሜን ኮርዶፋን ዋና ከተማ “ኤል ኦቤድ” አቅራቢያ የሚገኘውን “ኡም አርዳ” አካባቢ ነፃ በማውጣት አንጸባራቂ ድል ማስመዘገባቸውን አስታውቀዋል። “በሙስሊም ወንድማማቾች ጦር ላይም አሰቃቂ ሽንፈት አድርሰናል። እንዲሁም ለአሸባሪው ስብስብ መሳሪያ አከፋፋይ ኃይሎች በጀግንነትና በቁርጠኝነት ትምህርት ሰጠን” ብለዋል።

“ኃይሎቻችን ከኡም አርዳ ፈርጥጠው የሸሹትን የተሸነፉ ኃይሎች እያሳደደ ሲሆን፣ እነዚህም ኃይሎች በርካታ መጠን ያላቸውን የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጥለው ነው የፈረጠጡት። ዝርዝሩን ስናጠናቅቅ ይፋ እንዳድረጋለን” ብለዋል።

በተጨማሪም ኃይሎቻው በኮርዶፋንና በብሉ ናይል አቅጣጫዎች ግስጋሴያቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ ወደ ጠላት ጠንካራ ምሽጎች ዘልቀው በመግባት የመከላከያ አቅሙን ማዳከም እና በዋና ዋና አስፈላጊ ቦታዎች ላይ ሙሉ ቁጥጥራቸውን እይጠናከሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አንቀጽ 39 «እስከ መገንጠል» እና «ያለገደብ» የሚሉ ድንጋጌዎች እንዲሰረዙ ስምምነት ተደረሰ -ሪፖርት

"እስከመገንጠል" የሚለው እና ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና ከጅምሩ የተቃወመው...

የጋራ መድረክ በሻዕቢያ እንደሚመራ ሰብሳቢው አረጋገጡ፤ “ኢሳያስ እየረዱን ለምን ተቃውሞ ይሰነዘራል”

አዲስ ሪፖርተር - ራሱን "የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የጋራ የትግል...

በችኮላ የሚወጡ ሕጎች የሕግ አወጣጥ ሥርዓቱን እያዳከሙ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋት ላይ የተካሄደ ጥናት፣ በችኮላና...