አዲስ ሪፖርተር – ኤርትራ ራስዋን ከኢጋድ ማግለሏን አስታወቀች። ውሳኔው የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሰራ መሆኑ ያጋለጠው አህፋህግ የሰላም ስምምነት እንዲፈርም ኢጋድ ከፍተኛ ጥረትና ተሳትፎ በማድረጉ የፈጠረው ብስጭት እንደሆነ ተመልክቷል። ውሳኔው የሚገርም እንዳልሆነ የገለጹ አሉ። ኢጋድ በበኩሉ ማዘኑን አስታውቆ ምላሽ ሰጥቷል።
ኤርትራ እ.ኤ.አ. በ1993 ኢጋድ እንደገና ሲዋቀር፣ ለቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር እንደ ዋና መሣሪያ ሆኖ የሚያገለግል ተቋምን ለመገንባት ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር በመስራት ወሳኝ ሚና መጫወቷን በዛሬው የስንብት መግለጫዋ አስታውቃለች።
ኤርትራ፣ ” ህጋዊ ማንነቱን እና ስልጣኑን በአግባቡ አልተረዳም ፤ ስትራቴጂካዊ ጥቅም ማረጋገጥ አልቻለም ፤ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን አስተዋጽኦ አላደረገም ” ስትል ኢጋድን ከሳለች።
ኢጋድ ኤርትራ ከአባልነት መውጣቷን በተመለከተ በሰጠው ቃል ፤ ” ተጨባጭ የሆኑ ተቋማዊ ወይም ፖሊሲ ለውጦች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ሳታቀርብ ለመውጣት መወሰኗ አሳዝኖኛል ” በማለት ለኤርትራ ስንብት ምላሽ ሰጥቷል።
መቀመጫውን ጅቡቲ ያደረገው ኢጋድ ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ የመሠረቱ ሲሆን ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን አርፍደው መቀላቀላቸው ይታወሳል።
በነጮቹ አቆጣጠ 2007 ኢጋድን ተሰናብታ ከአስራ ስድስት ዓመት በሁዋላ በ20223 ዳግም ኢጋድን የተቀላቀለችው ኤርትራ ድርጅቱ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የማሪታይም እቅድ ኢትዮጵያን ማካተቱ ኤርትራን ማበሳጨቱ፣ በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላትን አገር በዚህ ፕላን ማካተት አግባብ ባለመሆኑ ስሟ እንዲፋቅ ኤርትራ ስትወተውት ቆይታች።
በቅርቡ በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ የሚመራና የእሱን ዱካ ተከትሎ ወደ ሰላም እየጎረፈ ያለውን ኃይል ጭመሮ ጠብ መንጃ ያነሱ አካላትን ለማስማማት ኢጋድ ከፍተኛ ድርሻ መውሰዱ የኢሳያስ መንግስትን ቅር እንዳሰኘ ዜናው እንደተሰማ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።
በዚህ መነሻ ኤርትራ ከአስራ ስድስት ዓመት በሁዋላ ዳግም የተቀላቀለችውን ኢጋድን ለቃ ወጥታለች። ኤርትራ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳላት፣ የአልሸባብ ኃይሎችን በማስለጠን፣ በማስታጠቅና፣ በማሰማራት ማስረጃ ቀርቦባት ማዕቀብ ተጥሎባት መቆየቱም አይዘነጋም።
አህፋግ ወደ ሰላም ማምራቱን ተከትሎ የተለያዩ አመራሮቹ ከኤርትራ መንግስት ጋር በሚስጢር ሲደረጉ የነበሩትን ጉዳዮች በአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ እንዲሁም ጉዳዩን በሚከታተሉ ዲፕሎማቶች ስም ማጋለጣቸው አይዘነጋም።
ኤርትራ ምርጫ፣ ፓርላማ፣ እንደ መንግስት መርህና መሰረታዊ መብቶች የሚከርባት አገር ባለመሆኗ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ሰንብቷል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






