አዲስ ሪፖርተር ዜና – በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ ተደራጅቶ የነበረው ግብረኃይል መበተኑ ተሰማ። ግብረኃይሉ በአገር ቤት አመጽ ለማስነሳት በህቡዕና በግልጽ አደራጅቶ የሚደግፋቸው ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሚዲያዎችና ግለሰቦች በጋራ ተናበው መስራት የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ያመለከቱ “ዓላማው እንደዚህ አልመሰለንም ነበር” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር ያስታወቁት አባላቱ ናቸው።
“እያደር ጥርጣሬያችን ቢያድግም በሻዕቢያ በኩል የሚተገበረው ይህ የግብጽ ፕሮጀክት ዓላማው በደንብ የገባን አሁን ነው” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ መረጃ የሰጡት የግብረኃይሉ አባል፣ በሳምንት ቢያንስ ሶስቴ ይደረግ የነበረው ስብሰባ ከቀረ ሁለተኛው ሳምንት አልፏል። በሚከፈላቸው በስም በሚታወቁ ሚዲያዎች በኩል ሲተላለፉ የነበሩ የሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያዎች፣ የቃለ ምልልስ ቅስቀሳ ፕሮግራም ማስታወቂያዎች እንዲወርዱ ተደርገዋል። ወይም እንዳይናገሩ ተደርጓል።
ከኢትዮጵያን አድን ማህበር የተወከሉት ዶክተር ሚኒሊክ የሚባሉት የግብረኃይሉ አባል “ይህ ስብሰብ ድርጅታዊ መልክ የለውም። ለመተማመን ያስቸግራል። የሚያያይዘው ደንብና መተዳደሪያ ደንብ የለውም። ዝም ብሎ ትርምስ ነገር ነው የሚመስለው። ሲሉ አልገባንም ነበር” ያሉት መረጃውን ለተባባሪያችን ያቀበሉት የግብረኃይሉ አባል፣ “በኤርትራ አማካይነት ከግብጽ የሚላከውን ገንዘብ ከመዝረፍ የዘለለ አገርን የሚጠቅም ስራ እንደማይሰራ የፖርት ሱዳኑ ስብሰባ ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል” ብለዋል።
በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ እንደ እሳቸው ያሉ አገራቸውን የሚወዱ “ከሻዕቢያ ጋር ያለው ግንኙነት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንዴት ይታያል? ጥንቃቄ አይስፈልገውም ወይ?” በሚል ጥያቄ ሲቀርብ አቶ ነዓምን ስብሰባውን በማቋረጥ “ስለኤርትራ እዚህ መድረክ ላይ አይነሳም” በማለት ያከላክሉ የነበርበት ምክንያት ግልጽ እያደር ግልጽ መሆኑን ያመለከቱት እኚሁ አባል “አሁን ላይ ግብረኃይሉ አለ ማለት አይቻልም። ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አይደረግም። ግንኙነትም የለም። አንዳንዴ አቶ ነዓምን የዋትስአፕ ግሩፕ ላይ የአንከር ሚዲያ ኢንተርቪው ይለጥፋሉ” በማለት አመጽ ለመቀሰቀስ የተደራጀው ቡድን መፍረሱን አመልክተዋል።
ሕዝብ በፖርት ሱዳን የተሰበሰቡትን “ባንዳዎች” በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ መሰማቱን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ የገባቸው የመድረኩ ተሳታፊዎችና አጃቢዎቻቸው፣ ይህንን የሕዝብ ስሜት የሚቀይሩ የተለያዩ መረጃዎች እየተዘጋጁ እንዲሰራጩ በጎንዮሽ ንግግር ቢደረገም ምንም ዓይነት ለውጥ ሊታይ እንዳልቻለ ከግብረኃይሉ ትዝብት ለመረዳት ትችሏል። ሰሞኑን የሚበተኑት የሃሰት መረጃዎችም የዚሁ ዕቅድ አካል እንደሆኑ ተመልክቷል።
አቶ ነዓምን አቶ ልደቱን ወደ ዋሽንግቶን እንዲዛወሩ በማድረግ አብሮነትን ከእሳቸው ማህበር ጋር ቀላቅለው ምርጫ እንዳይደርግ በሚቻለው ሁሉ ለማሰናከል የተቋቋመውን ግብርኃይል ሲመሩ መቆየታቸው፣ በዋሽንግቶንና በሎንዶን ለማድረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ሊሳካ ባለመቻሉና በአገር ቤት ለማካሄድ የታሰበው አመጽ በሚፈለገው መልኩ ባለመሄዱ የሸዋ ኦሮሞዎችን ለማነሳሳት ሌላ ዕቅድ ይዘው ኤርትራ ኤምባሲ መግባታቸውን ሰሞኑን መዘገባችን አይዘነጋም።
ተባባሪያችን እንዳለው አሁን ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አቶ ነዓምንና የሶማሌ ህዝብ ወኪል እንደሆኑ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መሐመድ በአንድ የክህደት መደብ ተመድበው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ነው። በዚህም ምክንያት ድንጋጤ መፈጠሩንና ይህንኑ ተቃውሞ ለመቀየር ሃሰተኛ መረጃዎችን በብዛትና በፍጥነት በቅብብል “ተባባሪ” በሚሏቸው ሚዲያዎች ለማሰራጨት እየሰሩ እንደሆነና ይህም ሰሞኑን እንደሚተገበር መረጃ እንዳላቸው አመልክተዋል።
ፕሮፌሰር መሐመድ የፕሬቪዳንት ኢሳያስ አፉወርቂን መጽሃፍ መግቢያና መደምደሚያ ያዘጋጁ፣ በጥቅሉ መጽሃፉን የተየቡ፣ በየጊዜው ኤርትራ የሚመላለሱ፣ በሶማሌ ክልል ተወላጆች ዘንዳ “አትወክለንም” በሚል በተደጋጋሚ የሚወቀሱና ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር የሻዕቢያን የቤት ስራ የሚያስፈጽሙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
አቶ ልደቱ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ የበተኑትን አብሮነት አስቸኳይ ስብሰባ ቢጠሩም የሚፈልጉትን ምላሽ ባለማግኘታቸው ስብሰባው ሊካሄድ እንዳልቻለ ታውቋል። አቶ ልደቱ ለአገልግሎታቸውና ለመኖሪያቸው የሚሆን ወጪ የሚሸፈንላቸው በአቶ ነዓምን እንደሆነ ለአዘቦት ባልደረባቸው አቶ ጥበቡ መናገራቸውን ለሁለቱም ቅርብ የሆኑ መናገራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን የሚታወስ ነው። እነዚህ ወገኖች እያደር በገንዘብ ክፍያና ሌሎች የጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች እየተብላላ ያለው ጉዳይ ይፋ እንደሚሆን አክለው ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አቶ ነዓምንን በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ለማነጋገር በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ቢሞከርም ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም። አቶ ልደቱ ስልካቸውን አያነሱም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






