አንቀጽ 39ን ጨምሮ ኢትዮጵያን ወደ መከራ ያመሩ ጉዳዮች ለምክክሩ ይቀርባሉ፤ ኢትዮጵያ [ከልጆቿ] ቀናነትን እየተማጸነች ነው፤ “ታሪካዊ መስቀለኛ መንገድ”

Date:

በበርካቶች ዘንድ ተስፋ የተጣለበት የአገራዊ እርቅ ኮሚሽን ገና መቋቋሙ ይፋ የሆነ ዕለት “እበተናለሁ አለ” በሚል አፍራሽ መረጃ ያስረጩበት ሚዲያዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ነበሩ። እንደተባለው አራት ዓመታት ባደረገው ሰፊ ዝግጅት ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን በቀጥታ ያሳተፈ ሲሆን፣ ከሕዝብ የቀረቡለትን ወደ 2,000 የሚጠጉ የምክክር ሐሳቦችና ጉዳዮች በመለየትና በመጭመቅ 8 ዓበይት ብሔራዊ አጀንዳዎችን ይፋ ለማድረግ በቅቷል።

አውቃቂዎችንና በቃት ያላቸው ዜጎችን የሚያሸማቅቅና አፍ የሚያዘጋው የማህበራዊ ሚዲያ መረን የለቀቀ የጅምላ ውቀሳ፣ ማስፈራራትና ስም ማቆሸሽ ያላቆማቸው የኮሚሽኑ አባላት አጀንዳዎቹ ይፋ በሁኑበት ቀን፣ ዋና ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና የጋራ እጣ ፈንታን በጋራ መበየን እጅግ አስፈላጊ በሆነበት ታሪካዊ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች በማለት ከምንም በላይ ቀናነትን ከሁሉም ወገኖች ጠይቀዋል። ተማጽነዋል። ለምነዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያ እንደ አገር ወደ መላክም ጎዳና ሊያመራት የሚስችላትን በረካታ ዕዶች በራሷ ሰግብግብ ልጆች እንዳጣች የሚናገሩ ይህንን ዕድል በጨዋነት፣ በቀናነት፣ በብሄራዊ ስሜት፣ መጪውን ትውልድ በማሰብና የተማርን ነን በሚሉ ወገኖች ሴራ መከራ እየበላ ላለው ዜጋ ሲሉ ይህንን እድል እንዲጠቀሙ የሚያማጸኑ “ገና ምኑም ሳይይያዝ ለተቃውሞና ለማፍረስ ሲተጉ የነበሩ ሁሉ ከድርጊታቸው በመቆጠብ አስቀድመው ኮሚሽኑ የያዘውን ስራ ለማስጨረስ ይወስኑ” ብለዋል። ለመቃወምና ለማፍረስ የተካኑ የሞሉባት ኢትዮጵያ፣ በቀና ልጆቿ የተከመሩ ችግሮቿን እንድትፈታ ሁሉም ወገኖች ግፊት ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም (ጁን 2024 እ.ኤ.አ) ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ ዋናው አገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ የሚከተሉት አጀንዳዎችና ነጥቦች በዝርዝር ይቀርባሉ።

ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:-

አጀንዳ ቁጥር 1

1. የሀገር ግንባታ
1.1 የማንነት እና የሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች
2. ታሪክ እና ማንነት
3. የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች (እሴቶችንም የሚመለከቱ ጉዳዮች)
4. ሀገር ግንባታና ብዝሀነት አስተዳደር ጉዳዮች
5. የቋንቋ ጉዳዮች
1.6 የባህል፣ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች

አጀንዳ ቁጥር 2

2. የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ስርአት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት
2.1 የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ
2.1.1 የመንግስት አደረጃጀት፣አስተዳደር ስርአት አይነት
2.1.2 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት (በቅንፍ ውስጥ ሲቲዝንሺፕ ዜግነት) ህዝባዊ…አንድ
2.1.3 የብሄር ብሄረሰቦች ትርጓሜ (አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ህገ መንግስቱ)
2.1.4 የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት መሪዎች የስልጣን ዘመን
2.1.5 የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት። የስልጣን ክፍፍል፣የፌደራልና የክልል መንግስት። የፊሲካል ፌደራሊዝምና የሀብት ክፍፍል
2.1.6 የክልል አስተዳደር እና ወሰኖች፤ የአዳዲስ ክልሎች አመሰራረት። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች
2.1.7 የህግ አውጪው አካል ወይም ፓርላማ አወቃቀርና ሚና
2.1.8 ህገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን
2.1.9 የህገ መንግስት ማሻሻያ ስርአት (አንቀጽ 104ና 105)

2.2 የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርአት ጉዳዮች

2.2.1 የሀገሪቱ የምርጫ ስርአት
2.2.2 የመድብለ ፓርቲ ስርአት
2.2.3 የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት
2.2.4 የመንግስትና የገዢ ፓርቲ ሚና መለያየት
2.2.5 የምርጫ ክልሎች አወቃቀር
2.2.6 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት ሀብት አጠቃቀም

አጀንዳ ቁጥር 3

3. የፌደራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ)

3.1 የአዲስ አበባ ጉዳይ
3.1.1 የአዲስ አበባ ህጋዊ አቋም። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት የአዲስ አበባ ከተማ የበጀት ድርሻ ጉዳይ

3.1.2 የፌደራል ዋና ከተማ ጉዳይ
3.1.3 የአዲስ አበባ ፖሊስና ፍ/ቤት ጉዳይ
3.1.4 የአዲስ አበባ ወሰንና የቦታዎች ስያሜዎች
3.1.5 የአዲስ አበባ የስራ ቋንቋ
3.1.6 የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣አካታችነት ጉዳይ

3.2 የድሬዳዋ ጉዳይ
3.2.1 የድሬዳዋ ህጋዊ አቋም
3.2.2 የድሬዳዋ የወደፊት አስተዳደራዊ ሁኔታ፣የህዝቦቿ ውክልናና ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር ያላት ግንኙነት
3.2.3 የድሬዳዋ በፌደራል መንግስት ውክልና። ድሬዳዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ጉዳይ

አጀንዳ ቁጥር 4

4. የሃይማኖት ጉዳዮች፣ታሪካዊ ቅሬታዎች እና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች
4.1.1 በሴኪውላሪዝምና በሃይማኖት ነጻነት መካከል ጤናማ ሚዛን መጠበቅ
4.1.2 የሃይማኖት ነጻነትና ገደቦቹ
4.1.3 አናሳ የተከታይ ቁጥር ያላቸው ሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ
4.1.4 ከባህል እና ከሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ ድርጊቶች ጉዳይ
4.2 ታሪካዊ ቅሬታዎችና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች
4.2.1 ታሪካዊ መገለል እና ልዩ ተጠቃሚነት
4.2.2 የእርቅና እውቅና የመስጠት ሂደት
4.3 በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት እና አብሮ መኖርን በተመለከተ
4.3.1 በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ውጥረቶችና መፍትሄዎቻቸው
4.3.2 በሃይማኖቶች መካከል የውይይት እና ምክክር ዘዴዎችን ማጠናከር
4.4 ሃይማኖት በህዝብ ህይወት እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ያለውን መስተጋብር በተመለከተ
4.4.1 በህዝብ ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት ሚና
4.4.2 የሃይማኖት መድረኮች፣ሚዲያና ህዝባዊ ውይይቶች
4.4.3 የሃይማኖት ተቋማት የድምጽ አጠቃቀም እና የህብረተሰብ መብት

አጀንዳ ቁጥር 5

5. የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብአዊ መብቶች
5.1 የሰብአዊ መብቶች
5.1.1 ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማእቀፍ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ
5.1.2 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች መብቶች
5.1.3 አካል ጉዳት፣ተጋላጭና የተገለሉ ቡድኖች መብቶች
5.1.4 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በግጭት እና በጸጥታ ሁኔታዎች ውስጥ
5.1.5 ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማዊ ማእቀፎች የማጠናከር ጉዳይ
5.1.6 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ዳያስፖራ)። የጥምር ዜግነት መብት እውቅና እና ሌሎች ጉዳዮች
5.2 የህግ የበላይነት
5.2.1 የህግ የበላይነት (ህጋዊነት)
5.2.2 በህግ ፊት እኩልነት
5.2.3 ተጠያቂነት
5.2.4 የፍትህ ተደራሽነት
5.3 የተቋማት ግንባታ
5.3.1 የዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ነጻነትና ተደራሽነት
5.3.2 የፍትህ ተቋማት ነጻነትና ተጠያቂነት
5.3.3 የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና አደረጃጀት
5.3.4 የሶስቱ የመንግስት አካላት ሚዛን፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት
5.3.5 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማዊ ገለልተኝነት፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት
5.3.6 የሲቪል ማህበራት ነጻነት፣ ሚናና ተጠያቂነት

አጀንዳ ቁጥር 6

6. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች
6.1 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች
6.1.1 የሴቶች ጉዳይ እና ተያይዘው የቀረቡ ጥያቄዎች
6.1.2 የሀብት አስተዳደር እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል
6.1.3 የመሬት ይዞታና ባለቤትነት
6.1.4. የህዝብ ቆጠራ ውክልና እና አካታች አስተዳደር
6.1.5 ማህበራዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርትና የኑሮ ደረጃ)
6.1.6 የሰራተኛ መብቶች እና ፍትሀዊ የስራ ሁኔታ
6.1.7 ዘላቂ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ።
6.1.8 የተፈጥሮ ሀብት መብቶችና ጥቅም መጋራት
6.1.9 አካታች ኢኮኖሚ፣ኢንቨስትመንት እና ምርታማነት
6.1.10 ማህበራዊ ደህንነትና የስራ እድል
6.2. የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ
6.2.1 የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተሳትፎና እኩልነት ተጠቃሚነትን የማሳደግ ጉዳይ
6.2.2 የግብርና ግብአቶች ወቅታዊና ፍትሀዊ ተደራሽነትን በተመለከተ።
6.2.3 የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 5ና አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን ‘ዘላን’ የሚለውን ስያሜ ማስተካከል
6.2.4 ነጻ የገበያ እድልና የገበያ ትስስር መፍጠር
6.2.5 የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች የጋራ መልማትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ
6.2.6 የአርብቶ አደሮች የኑሮ ዘይቤያቸውን ያማከለ የልማት ፖሊሲ

አጀንዳ ቁጥር 7

7. ሙስና እና መልካም አስተዳደር
7.1 የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች።
7.2 የጸረ-ሙስና ስርአት ግንባታ
7.3 የመልካም አስተዳደር ስርአት ግንባታ
7.4 ፍትሀዊ ፓብሊክ ሰርቪስ
7.4.1ፍትሀዊና አካታች ፓብሊክ ሰርቪስ
7.4.2 በብቃት ላይ የተመሰረተ የሰው ሀብት አመዳደብ እና ቅጥር

አጀንዳ ቁጥር 8

8. ሰላም ግንባታ
8.1የግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች

ግጭቶችንና መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከቱ
8.3 የዘላቂ ሰላም መሰረቶች
8.4 ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች እውቅና፣ ማጠናከር እና ዘመናዊ ውህደት
8.4.1 ባህላዊ እውቅና እና ህጋዊ ማእቀፍ
8.4.2 የእርቅና ይቅርታ ጉዳይ
8.4.3 የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነቶች
8.4.4 የሽግግር ፍትህ
8.5. ሃይማኖት ተቋማት ሚና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related