ግብጽ በኤርትራ በኩል በጀት ለቀቀች፤ አዲስ የትግል ስልት ተጀመረ፤ ኦሮሚያን ለማበጣበጥ ሰነድ ተዘጋጀ፤ “የትጥቅ ትግል አላዋጣም፤ ወደ ፖለቲካ ጥምረት እና ዲፕሎማሲ” ተባለ

Date:

ኦሮሚያ እስካልተረበሸ ድረስ የዲፕሎማሲ ጫና መፍጠር አንችልም። ስለዚህ ኦሮሚያ ለወደፊቱ ለሚፈጠረው አሃዳዊ አገዛዝ እንዲመች በአራት እንድትከፈል ይደረጋል። በኦሮሚያ ሸዋ፣ ጅማ፣ አርሲና ወለጋ ሌሎቹን ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች ይቀራመቷቸዋል። ፕሬዚዳንቱ ስልጣን አልባ ይደረጋል። ይህ ከሆነ በኋላ በሂደት ክልሉ ይፈርሳል። ሁለት ገጽ ላይ የሰፈረው የቅስቀሳ ሰነድ እንደሚለው ባሌ፣ ቦረና፣ ሀረርጌ፣ ኤሊባቦ0ር፣ ከምዕራብ ሸዋ በቀር ሶስቱ ሸዋዎች ከዞን በታች እንደሚሆኑ በተከታታይ ማስታወቅና፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከውስጥ አደረጃጀቱ ውስጥ ጥርጣሬ እንዲነሳ በመንግስት ምስረታው ወቅት የሚሰጡ ሹመቶችን በአካባቢ በመለየት፣ ከዕምነትና ጎሳ ጋር በማያያዝ ማቅረብ …

አዲስ ሪፖርተር – በዲያስፖራ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ የአደረጃጀቶቹ መሪዎች እና ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት በየፊናቸው ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ለመገናኘት እንደ ቀድሞው ቀላል አልሆነላቸውም። ዕድሉ አግኝተው ሲገናኙም የሚሰጣቸው ምላሽ “የተበታተናችሁ ናችሁ” የሚል እንደሆነ በተለያዩ መድረኮች ይገልጻሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነታቸው ወደ ላቀ ደረጃ ማደጉን የሚያበስሩ መረጃዎች ባለማቋረጥ እየወጡ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅና በቀይ ባሕር ካለው ወቅታዊ ሁኔታ በመነሳት አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እያሰረቻቸው ያሉት ውሎች በተቃውሞው ጎራ ያሉትን ተስፋ የሚያስቆርጥ ደረጃ ደርሰዋል።

“ምስራቅ አፍሪካን የሚያስተሳስርና ሰላምን የሚያመጣ” በማለት ኤርትራ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሳይቀር ደብዳቤ ጽፋ ይፋ ያደረገችው “ጽምዶ”፣ በጦር ሜዳና በዲፕሎማሲ የአሜሪካን አቋም ለማስቀየር እንደሚረዳ የዚሁ ጥምረት አባላትና ፈጣሪዎች መግለጫ ሲሰጡና በየስብሰባው ሲያስተባብሩ ቆይተዋል። ወደ አውሮፓም ድረስ በመዝለቅ ድጋፍ ለማግኘት ሞክረዋል። ይሁን እንጂ የታሰበው ምላሽ አልተገኘም። ይልቁኑም በደብዳቤ ለሚላክላቸው ጥሪና መግለጫ እንኳን ምላሽ መስጠት አቁመዋል።

ሰሞኑን በሸረሪና እና በራያ ግንባር ሰፊ ዝግጅት ተደርጎበት መንግሥትን ከተቻለ ለማስወገድ፣ ካልሆነም አስገድዶ ለድርድር እንዲቀመጥ ለማስቻል የተገፉት ኦፕሬሽኖች ባልተጠበቀ ሁኔታ መቀልበሳቸውና ከባድ ኪሳራ ማስከተላቸው “አዲስ አማራጭ” ወደሚለው ለመሸጋገር አስገዳጅ አድርጎታል።

በጦር ሜዳ በገጠመ ሽንፈት ሳቢያ በዲያስፖራ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶች ወደ ፖለቲካ ጥምረትና የዲፕሎማሲ ትግል ፊታቸውን እንዲያዞሩ መታዘዛቸው ተሰምቷል። ለዚሁ ማስፈጸሚያ የሚሆን በኤርትራ አገዛዝ በኩል የሚያልፍ በጀት መመደቡ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ላይ የማይታጠፍ የበቀል ዕቅድ ነድፈው የሚንቀሳቀሱ ሀገራት ከጀርባ ሆነው የሚመሯቸው እና በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች የትግል ስልታቸውን ወደ ፖለቲካ ውህደትና ዲፕሎማሲ እንዲቀይሩ የኤርትራ መንግሥት በጀት እንደመደበ ያመለከቱት ወገኖች፣ ይህ ውሳኔ የተወሰነው “የተበታተናችሁ ናችሁ” ለሚለው የአሜሪካ ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ገልጸዋል።

“ጽምዶ” በሚል ስያሜ የሚቋቋመው ህብረት “የብልጽግናን መንግሥት በሳምንታት ውስጥ ጠራርጎ ያስወግደዋል” በሚል ዕቅድ መነሻነት በሸረሪና እና በራያ ግንባር የተሞከረው ጥቃት ከከሸፈ በኋላ፣ የዲፕሎማሲና ፖለቲካ አግባብ ለመከተል ቀደም ሲል ከነበሩት በተጨማሪ አዳዲስ “ወስዋሾች” እንደሚቀጠሩም ታውቋል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ በዲያስፖራ ውስጥ ካሉ ዕድሮች፣ ማህበራት፣ ልዩ አደረጃጀቶች እና የታጣቂዎች ወኪሎች ጋር አብረው የሚሰሩትን ጠይቆ እንደዘገበው ከሆነ፣ የሸረሪና እና የራያ ግንባር ዝግጅቶች መክሸፋቸው በሌሎች ግንባሮች ለማካሄድ የታሰበውን ጦርነት አክሽፎታል። የፋኖ አደረጃጀትም ከህወሃት ጋር የተደረገውን ስምምነት በመቃወም መከፋፈሉና መንግሥት በወሰደው ተከታታይ እርምጃ ጉዳት ስለደረሰበት ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ የተጠበቀውን ያህል አልሆነም። በዚህም ሳቢያ በኤርትራና በግብፅ በኩል የመስፋ መቁረጥ ስሜት ተፈጥሯል።

አሁንም በጦርነት መንግሥትን ለመገልበጥ የሚደረገው ሙከራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በአብዛኛው የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ትግሉን እንዲያቀላጥፉ ተነግሯቸዋል። ይህ ውሳኔ የስብሰባ ኮረም እንኳን መሙላት ያቃተው የሕዝባዊ እምቢተኝነት አደራጅ እና የአመፅ አመቻች የጋራ መድረክ ከያዘው ዕቅድ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ተገኝቷል።

ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አዲስ አበባ ካሉ የህቡዕ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ከትጥቅ ትግል ጋር በማጣመር ሲመሩ የነበሩ ቡድኖች እና ስብስቦች ፊታቸውን ወደ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ለማዞር አዲስ ዕቅድ ሲነድፉ፣ ጎን ለጎን “አንድ የመሆን ሥራ እንዲሠሩ ታዘዋል” ብለዋል የዜናው ምንጮች። በቀጣይ ሰላማዊ ሰልፎች፣ ተከታታይ የበይነ-መረብ ዘመቻዎች፣ እንዲሁም ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካይነት በትምህርት ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች ወዘተ ትርምስ እንዲፈጠር የሚሠሩበትና ለዚሁ ሥራ የሚሆን በጀት መዘጋጀቱን አዲስ ሪፖርተር አረጋግጣለች።

አዲስ ሪፖርተር ባየችው የብጥብጥ ዕቅድ መሠረት፣ ከአዲስ ዓመት ጀምሮ ከሚተገበረው ረብሻና ሁከት ጎን ለጎን “የአንድነት ፖለቲካ” አዋጆችና መግለጫዎች የዚሁ መድረክ አባላት በሆኑ ሚዲያዎች በስፋት ይሰራጫሉ። መሀል ሀገሩን በማወክ “አማራጭ ነን፤ አንድ ሆነናል፤ ህብረት ፈጥረናል” የሚል ትርክት እንደሚሰራ ያመለከቱት ክፍሎች፣ በዕቅዱ መሠረት የሚመሠረተው ፖለቲካዊ ጥምረት ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሀገራት አጋርነታቸውን የሚያሳዩበት እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የሚሆነው ጫና መፍጠር ለሚችሉ ሀገራት “ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጠረውን ቀውስ የማረጋጋት አቅም አለን፤ ህብረታችን ቀጣናዊ ነው” በሚል ተቀባይነትን ለማግኘት ነው።

ከህወሃት ጋር በጥብቅ የሚሠሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ጨምሮ በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ ኦሮሞዎች አንድ ሰሞን “ለእኔም ብሎኛል” በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ ከፍተውት እንደነበረው ተመጋጋቢ ዘመቻ፣ በኦሮሚያ ላይ ልዩ ዘመቻ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል።

ዘመቻው “ኦሮሚያ ካልተበጠበጠ ውጤት አይገኝም” በሚል አዳዲስ ትርክቶች መዘጋጀታቸውን ለአዲስ ሪፖርተር ከተላከው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

እንደ መረጃው ከሆነ ኦሮሚያ በአራት ዞኖች እንደምትከፈል፣ ይህ የሚሆነው ቀስ በቀስ ወደ አሃዳዊ አስተዳደር ሲኬድ ክልሉን ለማፍረስ እንዲያመች እንደሆነ፣ በዚሁ ስሌት ጅማ፣ ሸዋ፣ አርሲና ወለጋ አራት ቦታ ሆነው ሌሎቹን የኦሮሚያ ዞኖች እንዲጨፈልቁ እንደሚደረግ፣ እንዲሁም እንደ ባሌ፣ ኢሉባቦር፣ ቦረና፣ ሐረርጌ የመሳሰሉት የኦሮሚያ አካባቢዎች ከቀድሞ አቅማቸው ዝቅ እንደሚሉ በማስመሰል ሕዝብን ለማነሳሳት “ሰነዱ እጃችን ገባ” በማለት ተከታታይ ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨት ዕቅድ ተይዟል።

“ሸዋ” የሚለው ክፍል ሰላሌን፣ ምስራቅ ሸዋንና ሰሜን ሸዋን በአምቦ ሥር አጣብቆ ከወረዳ ያነሰ መዋቅር ሊሰጣቸው መዘጋጀቱን በማመልከት ያዘጋጁት የፈጠራ ሰነድ፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ እንዲለቀቅ ዝግጅት መደረጉን አዲስ ሪፖርተር ከተሳታፊዎቹ ለመረዳት ችላለች።

ይህንኑ አስመልክቶ ጉዳዩን በበላይነት ይመሩታል ለተባሉት ፕሮፌሰር ህዝቅኤል የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ በእጅ ስልካቸው ደውሎላቸው “ማን ነገረህ? የምንሰራውን እናንተን አማክረን አንሠራም፤ ተከፋይ ሚዲያዎች ናችሁ” በማለት ተሳድበው ስልካቸውን ዘግተዋል። በተደጋጋሚ ቢሞከርላቸውም በድጋሚ ስልካቸውን አላነሱም።

አቶ ነዓምን የሻዕቢያ ወኪል በመሆናቸው ስለ በጀቱ የሚያውቁትን እንዲያስረዱ በተከታታይ ቢደወልላቸውም፣ ስልካቸውን ለመመለስ አልወደዱም። ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ቅርበት ያላቸው “ለዚህ ዓይንቱ የፈጠራ ድረሰት ምን ይመለሳል” በማለት በሰሙት መገረማቸውን አመልክተዋል።

በኦሮሚያ ቀደም ባሉት ዓመታት ጀመሮ ለጸጥታ እና ለሰላም ሲባል ክልሉን እንደ አመቺነቱ እየከፋፈሉ ማስራት የተለመደና ውጤት የተገኘበት አሰራር እንደሆነ በተለያዩ አገባቦች ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኩምሩክና ሸረሪና እንደ ማግኔት የሚሳሳቡ ድሎች፤ የRSF/TASIS ኃይሎች ተጨማሪ ከተሞችን ተቆጣጠሩ፤

ኩምሩክ ከRSF/TASIS ኃይሎች ላይ ስትነጠቅ፣ ከሸረሪና የሚነሳው የህወሃት ኃይል...

ልዩ ሪፖርት፡ የራያ ግንባር እንደ ሸረሪና! የአራት ግንባሮች ግብአት አምካኙ [ኦፕሬሽን መረዋ] አርሚ 26 ምን ገጠመው?

አዲስ ሪፖርተር — ከሸረሪና ኦፕሬሽን በኋላ አነጋጋሪ የሆነው የደፈጣ...

አንቀጽ 39 «እስከ መገንጠል» እና «ያለገደብ» የሚሉ ድንጋጌዎች እንዲሰረዙ ስምምነት ተደረሰ -ሪፖርት

"እስከመገንጠል" የሚለው እና ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና ከጅምሩ የተቃወመው...