Monday, December 1, 2025

በድሬደዋና ሶማሌ የኦነግ አመራሮችና ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፤ ከታጋቾች ላይ ብር የወሰዱ በቁጥጥር ስር ዋሉ፤ ባንካቸው ታገደ

Date:

የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ግብረ ኃይል ይፋ እንዳደርገው ከሆነ የኦነግ ታጣቂዎች በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሶማሌ ክልል የጥፋት ዕቅድ ለመፈጸም ሲነሱ መረጃ አለው። ይህ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሉ የሚጠራው ቡድን በተቀነባበረ ዘመቻ አመራሮችና ተዋጊዎቹ ተድምሠዋል። የተማረኩ ሲኖሩ “34 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል። ታጋቾችን ለማስፈታት ገንዘብ የተዘዋወረበት የባንክ ሂሳብ ታግዷል። ኦነሠ ይህን አስመልክቶ ይህ እስከታተመ ድረስ ያለው ነገር የለም።

አርባ ሶስት ታጣቂዎች መገደላቸውን እንዲሁም ሌሎች እንደተማረኩ እና እጅ እንደሰጡ ምስል አስደግፎ ያስታውቀው የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ግብረ ኃይል፣ “43 የጠላት ኃይል ተገድሏል” ብሏል። አክሎም ዋና መሪያቸው ጃል ሀረርጌ ወይም ኢቲመር እንደሚገኝበት አመልክቷል። የጃል ሐረርጌ ምክትል ጃል ቦባስ እና ጃል ራሳ እንዲሁም ጃል ቦባስ ቆስለው መያዛቸውን፣ ጃል ራሳ እንዲሁ መማረኩን የድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ አስታውቀዋል።

በዘመቻው “የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የፀጥታ ኃይል አሉ” ኮሚሽነሩ፣ ከምዕራብ ሐረርጌ በተለይም ከአንጫር ዲንዲን አካበቢ የተነሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የገቡት ከአንድ ወር በፊት መስከረም 19 ቀን እንደሆነ አመልክተዋል። ታጣቂዎችሁም ከ70 እስከ 80 እነደሚገመቱ ተናግረዋል። ታጣቂው ቡድን በኦሮሚያና ድሬደዋ አዋሳኝ ስፍራ የመመሸግ ዕቅድ ነበረው ብለዋል።

ይህ ታጣቂ ከመሸገበት ቦታ ሆኖ ስልጣና በመስጠት ቤዙን በማስፋት እንደለመደው “በማኅበረሰብ፣ በኢኮኖሚ እና በኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ የሽብር ጥቃቶችን” የመፈጸም ዕቅድ እንደነበረው በበቂ መረጃ መረጋገጡን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

“ዋና ዓላማው፤ በምሥራቅ ሐረርጌ ጋራ ሙለታ ሄዶ፣ ሌላ ቤዝ መመሥረት እና በዚያም እንደዚሁ የሥልጠና ቦታ በማመቻቸት፣ ራሱን ከግዜ ወደ ጊዜ አስፍቶ ምሥራቅ ኢትዮጵያን የግጭት፣ የሽብር ቀጣና፣ የብሔር ብሔረሰቦች ግጭት ቀጠና ለማድረግ ያለመ ነበር” በማለት ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። ዘመቻው ለምን እንደዘገየ ባያብራሩም የታጣቂው እንቅስቃሴ በቅርብ ክትትል ስር እንደነበር ገልጸዋል።

ቡድኑ ራሱን ለማደራጀት አቅዶ ከመሸገበት በመነሳት በጅቡቲ መስመር፣ በደንገጎና በሶማሌ ክልል በኩል ጥቃት በመሰንዘር ሽብር የመፍጠር ዕቅድ እንደነበረም አስረድተዋል።

የኦሮሞ ሰራዊት ታጣቂዎች ወደ ተጠቀሰው አካባቢው ከገቡ ጀመሮ ኦፕሬሹ እስከተሰራበት ቀን ድረስ ሁለት የፖሊስና ሦስትየሚሊሻ አባላት መግደሉን፣ከዚህም በተጨማሪ አንድ መምህር በተመሳሳይ መገደላቸው በመግለጫው ወቅት ተመልክቷል።

በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ላስዴሬ አካባቢ ውስጥም አራት በቻይና ካምፓኒ ተቀጥረው የሚሰሩ አራት ኢትዮጵያውያን ታግተው እንደነበር፣ ለማሰልቀቂያ “አራት ሚሊዮን ብር” መከፈሉንም ኮሚሽነሩ አስታወቀዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በድሬዳዋ ከተማ እና ሶማሌ ክልል መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር የተባለውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ክንፍ “ለማጥቃት እና ለማጥፋት” ሰባት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አካላትን በአባላትነት የያዘው “የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ግብር ኃይል” ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

የፀጥታ ኃይሎቹን ጥምረት በመወከል መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ዓለሙ እንደሚያስረዱት፤ ከግብረ ኃይሉ አባላት መካከል “የመከላከያ ሠራዊት ምስራቅ ዕዝ” እና “የምሥራቅ ኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል” ይገኙበታል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ “የወንጀል መከላከል ኃይል”፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ “ፀረ ሽምቅ እና ልዩ ኃይል” እንዲሁም የሶማሌ ክልል “ልዩ ኃይል” አባላትም ግብረ ኃይሉ ውስጥ መካተታቸውን ጠቅሰዋል። የድሬዳዋ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ አባላትም ተሳትፎ እንደነበራቸው አክለዋል።

ግብረ ኃይሉ በታጣቂ ኃይሉ ላይ ያካሄደውን ዘመቻ የጀመረው “በአንድ ወር ለመጠናቀቅ” በማቀድ እንደሆነ የሚናገሩት ኮሚሽነር ዓለሙ፤ ሦስት ዘርፎች ተከፋፍለው “መረጃ የማጠናከር”፣ “ኦፕሬሽኑን በተግባር የማካሄድ” እና “ምርመራ ማካሄድ” ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ታጣቂ ቡድኑ ዕቅዱን “ተግባራዊ ሳያደርግ፣ ፍጹም በሆነ በእነዚህ ሰባት የጸጥታ ኃይል ተከቦ ካለበት እንዲወጣ አድርጎ፣ ከተቀበረ ጉድጓድ በማውጣት ሜዳ ላይ ሲገኝ እንግዲህ እርምጃ ተወስዶበታል” ብለዋል።

ኮሚሽነር ዓለሙ፤ “በዚህ መሠረት 43 የጠላት ኃይል ተገድሏል። ከዚህ 43 ውስጥ ዋናው መሪ ጃል ሀረርጌ ወይም ኢቲመር የሚባለው እርምጃ ተወስዶበታል ሞቷል። […] የእሱ ምክትል የተባሉት ጃል ቦባስ እና ጃል ራሳ የሚባሉት ደግሞ፤ ጃል ቦባስ ተመትቶ የተያዘ ሲሆን ጃል ራሳ እንዲሁ ተማርኳል” ሲሉም አብራርተዋል።

“25” የቡድኑ አባላት “እንደተማረኩ” እና “እጅ እንደሰጡም” የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውንም ተናግረዋል። ከታጣቂ ቡድኑ ጋር “በሴል፣ በፋይናንስ፣ በመረጃ፣ ገንዘብ በማስተላለፍ፣ በተለያየ ሁኔታ ሲረዱ የነበሩ”፤ “34 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች” በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አክለዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ተፈጽሟል በተባለው እገታ ውስጥ የተሳተፉ እንደሚገኙበትም ገልጸዋል። ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተከፈለው “አራት ሚሊዮን ብር” የገባበት የባንክ አካውንት እንዲታገድ ተደርጎ፤ በሒሳብ ቁጥሩ “ሲጠቀሙ የነበሩ” የቡድኑ “ደጋፊዎች” መያዛቸውንም ገልጸዋል።

ኮሚሽነር ዓለሙ፤ “እነኚህ ለሕግ ቀርበው ወደ ዘጠኝ መዝገብ ተጣርቷል። ከዘጠኙ አራቱ መዝገብ ለዐቃቤ ሕግ ሙሉ በሙሉ ተሟልቶ ወደ ክስ መክፈት እና ለችሎት ማቅረብ የደረሰበት ሲሆን አምስት መዝገብ ደግሞ በአሁን ሰዓት በማጣራት ላይ ነው ያለነው” ብለዋል።

የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ “በተለየ ወጥቶ ለሕግ እንደሚቀርብ” አስታውቀዋል። ዘመቻው በተካሄደበት ወቅትም “የደም፣ ላብ፣ የሕይወት መስዋዕትነት” የከፈሉ የግብረ ኃይሉ አባላት መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነር ዓለሙ፤ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች የነበረው ሰርጎ ገብ ታጣቂ ቡድን ሙሉ በሙል መጽዳቱን አመልክተ

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related