ትህነግ በትግራይ በስልት ታቦት ሆናለች፤ ሕዝብ እንዲያመልካት ስልሳ ዓመት ተሰርቶበታል
አዲስ ሪፖርተር ህወሃት ሰሞኑን “አንድ ነን” በሚል ያወጣው መግለጫ “የሕዝቡን ሞራሉን እንጠብቅለት” በሚል እሳቤ እንጂ፣ ህወሃት መከፈሉን፣ ስብሰባውንም ሲያካሄድ ለሁለት ተቧድኖ ሲነታረክ እንደነበር ያስታወቁት አንድ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዥ ናቸው፤ እሳቸው እንዳሉት አሁን ላይ ህወሃት እያንሰራራ ያለውና ሕዝቡን እየሸነገለ ያለው ከመሃል አገር “ህወሃትን እናጠፋዋለን” የሚለውን ፉከራ ለፕርፖጋንዳነት በመጠቀም ስለሆነ ይህን ፉከራ የሚደጋግሙ አጀንዳውን ለትግራይ ሕዝብ እንዲተውለት መክረዋል።
መኮንኑ ከአዲስ ሪፖርተር የትግራይ ተባባሪ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ እንዳሉት “ህወሃትን እናተፋዋለን” የሚለው የባለስልጣናት፣ የመንግስት ደጋፊዎች፣ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ገጾች እድምተኞች የቀን ተቀን ፉከራ ለጽንፈኛውና ከኤርትራ አምባገነኖች ጋር ግንኙነት ለጀመረው አንድ ቡድን ከፍተኛ የቅሰቀሳ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን አመልክተዋል።
“ህወሃት ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንዲቆራኝ ተደርጓል። አንዳንዶች ህወሃትን ታቦት አድርገው ያዩታል። አንዳንዶች ህወሃት ከሌለ መኖር የሚችሉ እስከማይመስላቸው ድረስ ተጠምቀውበታል። ላላፉት ሃምሳ ዓመታት ሕዝቡ በህወሃት አስተምህሮት ታጥቧል። የስነ ልቦናውም ውቅር በዚሁ አግባብ የተቀኘ ነው” ያሉት መኮንኑ ይህን ስር የሰደደ እምነት “እኔ አጠፋልሃለሁ” ማለት ለጽንፈኛው ቡድን ሰርኛ ምላሹ ነው።
ፉከራውን “አላለንህም፣ ይኸው ሊያተፉህ ነው። ድርጅትህን አፍርሰው አንተን ከምድረ ገጽ ሊያስወግዱህ ነው” በሚል ቅስቀሳ ሕዝቡን በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ውስጥ በመክተት ከጎናቸው እንዲሆን እንደሚጠቀሙበት ከፍተኛ መኮንኑ አስታውቀዋል።
በፕሮፕጋንዳ የተካኑ በመሆናቸው ከመካከል ሳይታሰብበት የሚረጨውን የስሜት ንግግር በደንብ እንደሚተቀሙበት ያመለከቱት መኮንኑ፣ መንግስት ወይም የሚመለከታቸው በዚህ ጉዳይ ላይ በጥልቅ እንዲያስቡበት መክረዋል። በስሜት በደጋፊ ስም የሚሰራጩ “ህወሃትን እናጠፋለን” ፉከራ የተናበበና ስትራቴጂ ተኮር ቢሆን እንደሚበጅ ጥቆማ ሰጥተዋል።
አሁን ላይ ሕዝብ ብዙ ነገር እየገባው ስለሆነ፣ ህወሃትን እየተፈረካከሰ በመሆኑ ቢቻል ኢንተርኔት የማይተቀመውን ሕዝብ በቲቪና በሬዲዮ ለመግኘት ቢሞከር ውጤታማ ስራ ሊሰራ እንደሚችል ያመከቱት የሰራዊት አመራር፣ ኢንተርኔት የሚያገኘው አብዛኛው ወይም ከሰማኒያ በመቶ በላይ ህወሃት ላይ ፊቱን ማዞሩን አመልክተዋል። ቀሪውን ገጠር ያለውንና ኢንተርኔት የማያገኘውን ሕዝብ በሬዲዮና ሳተላይት ቲቪ ለማግኘት መሰራት እንዳለበት ደግመው አሳሰበዋል።
አሁን ላይ ትግራይ ተቀምጦ በራሱ ዩቲዩብ ትንተና እየሰጠ ያለው ዳንኤል ብርሃኔ “ህወሃት በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ታቦት ነች” በማለት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ሰፊ ማብራሪያ መስጠቱ አይዘነጋም።
“እንደ ፊውዳሉ ዘመን ትህነግ ለትግራይ ሕዝብ አዲስ ታቦት ሆናለች፤ ሌላው ህዝብ ማዳመቂያ ነው” ሲል ዳንዔል ብርሃኔ የተናገረው በርካሄ ሾው በሚባል የዩቲዩብ አውድ ላይ ነው። ዳንዔል እንዳለው “ትህነግ አዲስ የትግራይ ታቦት ሆናለች። ለዚህም ምክንያቱን ሲያስረዳ ትህነግ ላለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት የትግራይን ህዝብ ዋና እሴት በስልት ወደ እራሱ አዙሮ እምነት እንዲሆን አድርጓል” ብሏል።
ዳንዔል በንግግሩ በትግራይ አዲስ እሳቤ እየተነሳ መሆኑን አመልክቶ “ የትግራይ ሕዝብ ታቦትን ያከብራል፣ ይወዳል፣ ትህነግ ቀስ ብላ ይህን አማኝ ህዝብ “ትህነግ ከሌለ ትግራይ አትኖርም” በሚል ዕምነት እንደቀየረው አስታውቋል።
ልክ ዳንዔል እንዳለው እኚሁ ከፍተኛ የጦር መኮንንም የሚደግሙት ይህንኑ የዳንዔል እይታ ነው። ስለሆነም ትህነግን የትግራይ ሕዝብ በወጉ እያወቀውና እየተረዳው ስለሆነ፣ የደረሰበትንና እየደረሰበትን በደንብ እያስተዋለ በመሆኑ፣ የሩቁ ቢቀር ከቅርብ ጊዜዎች ጦርነቶች የደረሰበት ጉዳይ አሁን ደረስ እየፈጀው በመሆኑ፣ ትህነግን አስመልክቶ የሚነሰነዘሩ አስተያየቶች ለዚህ እየወደቀ ላለ ቆሞ ቀር ቡድን ግብአት እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ሊወሰደ እንደሚገባ፣ ይህ ሲሆን በውስጥ ለለውጥ ለተነሱ አካላትም አመቺ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ሻዕቢያ የትግራይ ሕዝብን አቋም አይቶ አካሄዱን ነገ ሊቀይር እንደሚችል መረጃ መውታቱን ተከትሎ ከጽንፈኞቹ የትህነግ ኃይሎች ጋር ቆመው የነበሩ ከፍተኛ የጦር አመራሮች እየተነጠሉ መሆኑን፣ እሳቸው አንዱ መሆናቸውን ያመለከቱት የጦር አመራር፣ ጽንፈኛው ቡድን የቃላት አምባጓሮ፣ የመግለጫ ምልልስና “ትህነኝ እንቀብረዋለ፣ ከምድር እናጠፋዋለን” የሚለውን ፉከራ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚፈልገው ገልጸዋል። የሚሰማ ካለ ቢቆም ትህነግ እርቃኑን እንዲቀር የተጀመረውን ትግል እንደሚያፋጥነው ገልጸዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
tiktalk – https://www.tiktok.com/@addisreporter3
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






