አዲስ ሪፖርተር – ህጋዊ መሰረት ሳይኖራቸው አሜሪካ የተቀመጡ ኢትትዮጵያዊያን በስልሳ ቀን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ፤ በጊዚያዊነት ከለላ የተሰጣቸውን የኦትዮጵያ ዜጎች “በ60 ቀናት ከሃገሬ ውጡ” ስትል አሜሪካ ያወጣቸውን ማዘዣ ተከትሎ አቶ ልደቱ አያሌው፣ ኢንጂነር ይልቃል፣ መእዛ መሐመድ፣ በቅርቡ ይግባኝ የጠየቁት ቫቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳዩ እንደሚመለከታቸው ተሰምቷል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት ማንሳቷን ተከትሎ የሚሰሙ ዜናዎች መንግስትና አሜሪካ ወዴት እያመሩ ነው? አሰኝቷል።
አሜሪካ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም” ከሚል ድምዳሜ በመነሳት እደሆነ ይፋ አድርጋለች። ይህ ውሳኔ በቅርቡ “የብልጽግና መግስት ይህን ዓመት አይጨርስም” በማለት ትነተና ሲሰጡ ለነበሩት አቶ አንዳርጋቸውና የሻዕቢያ መሪዎች አስደንጋጭ እንደሚሆንባቸው ዜናውን የሚከታተሉ አመልክተዋል። ከማስደንገጥም አልፎ እንቅልፍ የሚነሳ እንደሚሆን ነው እየተገለጸ ያለው።
አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋና በሌሎች ተመሳሳይ የሰውን ልጅ የሚፈትኑ ችግሮች ሳቢያ ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ ተሰጣለች። ወደ አሜሪካ ያመሩ ኢትዮጵያውያንም በዚሁ መብት ነበር ተጠቃሚ የነበሩት።
አሜሪካ በአዲሱ ብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂዋ ከአፍሪካ ጋር ባላት ግንኙነት ላይ ሙሉ በሙሉ ለውጥ ማሳየቷን ስትገልጽ ዋናው የግንኙነት መርኋ በጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን ይፋ ማድረጓን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
በዚሁ መነሻና ኢትዮጵያ ላይ ባላቸው ወቅታዊ ግምገማ አስጊ ሁኔታ ስለሌለ የአሜሪካ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም አገራቸው ለኢትዮጵያዊ ዜጎች ሰጥታው የነበረው ጊዜያዊ ከለላ መነሳቱን ይፋ አድርገዋል። በመሆኑም ይፋ የሆነው መመሪያው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን በ60 ቀናት ውስጥ “ምድሬን ልቀቁ” ተብለዋል።
በመመሪያው ቀድመው በፈቃዳቸው ከአሜሪካ ለሚወጡ ሙሉ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን አመልክቷል። በተጨማሪም የአንድ ሺህ ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ተመልክቷል።
ይፋ የሆነው ይህ ቀነ ገደብ ከመጪው የነጮቹ የካቲት 13 በኋላ እንደሚያበቃ አሜሪካ አምስታውቃለች። ይህን ማሳሰቢያ ተከትሎ ጊዜያዊ ከለላ ከተሰጣቸው መካከል አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ መዓዛ መሐመድ፣ ኢንጂነር ጌትነት ይልቃል የመሳሰሉትና ከሻዕብያ ጋር በይፋ እየሰሩ ያሉ አካላት ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።
አሜሪካ አሸባሪነትን ከመዋጋት አንጻር፣ በቀይ ባህር የአፍሪካ ቀጣና ላይና በሁለቱ አገሮች የጋራ ጥቅም ጉዳይ አብረው ለመስራት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረጋቸው አይዘነጋም።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






