አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ታሪክ ከታዩ አስከፊ የጥፋት ታሪኮች ተርታ የሚመደበው የሰሜኑ ጦርነት ለኢትዮጵያ በተለይም ለትግራይ ህዝብ ትልቅ ስነ ልቦናዊ ጠባሳ አሳርፎ አልፏል። ታድረያ በጦርነቱ ከተሳተፉት ሁለት ተዋናዮች በላይ የኤርትራ መንግስት ጉዳዩን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሚጠላው የትግራይ ህዝብ ላይ ወድመት እንደፈፀመ አቶ ጌታቸው ረዳ ከNBC ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አሳውቀዋል።
እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በጠቅላይ ሚኒስተሩ ትዐዛዝ የወቅቱ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ሬድዋን ሁሴንን በማስጠራት የትህነግ አመራሮችን አወያዩተዋል። ግጭት ውስጥ ከተገባ ተጠቃሚ የሚሆነው የኤርትራ መንግስት እንደሆነ አስጠንቅቀውም ነበር። “ነገር ግን እኛ በወቅቱ ጉዳዩን ቸላ ብለነው ነበር” በማለት የመንግስት የሰላም ጥሪ ወደ ጎን ማድረጋቸውን አቶ ጌታቸው በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ትህነግ ለትሕነግ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ ያወሱት አቶ ጌታቸው፣ “ሻዕቢያ እና ትሕነግ እኩል ቢወድቁ እና ሻዕቢያ አንድ ኢንች ከፍ ብሎ ቢወድቅ ለኤርትራ መንግስት ስኬት” ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም የኤርትራ መንግስት የሰሜኑን ጦርነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በትግራይ ክልል ሆን ብሎ ያደረሰውን ወንጀል ቤት ለቤት በተደረገ ጥናት አስደግፈው ያቀረቡ ሲሆን፣ 76% የሚሆነውን በትግራይ ክልል የተፈፀመውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት፣ ሊድን ያልቻለ የስነልቦና ድቀት ሻዕቢያ እንደፈፀመ አስታውቀዋል። ይህም ሳይበቃ ከ100,000 በላይ በሆኑ ሴቶች ላይም ፆታዊ ጥቃት እንዳደረሱ አቶ ጌታቸው ይፋ አድርገዋል።
በሰሜኑ ጦርነት በሁለቱም ወገን የደረሰው ጥፋት በፕሪቶርያው ስምምነት እንደሚታይ ያነሱት አቶ ጌታቸው “ሻዕቢያ በትግራይ ህዝብ ላይ ላደረሰው ጥፋት መክሰስ እፈልጋለሁ” ብለዋል። አክለውም ይህን ጉዳይ በተመለከተ በትህነግ አመራሮች ዘነዳ እንዲነሳ እንደማይፈልጉ አመልክተዋል።
“ሻዕቢያ በራሱ ሰራዊት ምንም ማድረግ አይችልም” ያሉት አቶ ጌታቸው “ያን ጊዜ ጦራችንን ወደ ኤርትራ አዝምተን ቢሆን ኖሮ ድል ማድረግ አያቅተንም ነበር፣ ምክኒያቱም ኢሳያስ ከራሱ ጠባቂዎች ውጪ የሚዋደቅለት እንድም ህዝብ የለውም” ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ሰለ ትሕነግ በሰጡት አስተያየት ትሕነግ የሰላም ስምምነቱን የመረጠው ሌላ ዝግጅት አድርጎ አዲስ አበባ ገባለሁ ከሚል ሃሳብ እንጂ ሰላም ያዋጣል ከሚል አስተሳሰብ እንዳልሆነ በመግለፅ ከዚህ በኋላ ከሰላም ውጪ በሆነ ትጥቅ ትግል ማንም ሰው ስልጣን ይይዛል የሚል እምነት እንደሌለው አያይዘዞ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል በአንድ ወቅት ከራሱ አልፎ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ሰው የሚበላው አጥቶ እየሞተ ያለን ህዝብ ማስያዣ አድርጎ የሚነግደው ትሕነግ ወድቀት እና ውድቀትን ብቻ ሲያስተናግድ ኖሮ አሁንም ተዋግቼ ነፃ አወጣለሁ የሚለው ውሸት እንደሆነ እና ይህ አካሄድ ክልሉን የጦርነት ቀጠና ከማድረግ ውጪ እንደማያረጋጋ በመግለፅ አሁንም ከውድቀቱ ላልተማረው ትሕነግ መልዕክት አስተላለፈዋል።
አቶ ጌታቸው ትሕነግ ራሱን እንደ ትግሬያዊነት መገለጫ አድርጎ ስለሚጠራ ትሕነግን የማይደግፍ በሙሉ ትግሬ አይደለም ተብሎ ይፈረጅ እንደነበር አመልክተዋል። “ትሕነግ ራሱን ለትግራይ ብሄርተኝነት ተቆርቋሪ አድርጎ ቢያወራም፣ ሰፈር እየጠቀሰ አንዱን የጠራ ትግሬ ሌላውን ደግሞ ሁለተኛ ትግሬ የሚል የ‘Primordial ethnic analysis’ ሀሳብ አጠንጣኝ ነው” በማለት ወቅሰዋል።
በጦርነቱ ትልቁ ጥፋት የተፈፀመው በመጀመሪያው ዙር ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በመጀመሪያው ዙር ትምህርት ቤቶችን እና የልማት ተቋማትን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እንደደረሰ አንስተው ትሕነግ ከሽሬ እስከ መቐሌ መዳረሻ ድረስ መዝረፍ የሚችለውን እየዘረፈ መውሰድ የሚችለውን ደግሞ ሆን ብሎ እንዳልነበረ አድርጎ እያወደመ ይሄድ እንደነበር አመልክተዋል።
ትሕነግ ድሮ የሃሳብ አንድነት እንደነበረው የገለፀው አቶ ጌታቸው አሁን ላይ ግን ከታች እስከ ላይ አመራር ድረስ ምንም አይነት የዕውቀት መሰረት ስለሌላቸው ከስድብ በዘለለ ተጨባጭ መፍትሄ የሚያመጣ አካል የለም ሲሉ ድምዳሜያቸውን አስታውቀዋል። እነዚህ “ቆሞ ቀር” የሚባሉት አመራሮች የፕሪቶሪያውን ስምምነት አንበበውት እንደማያውቁ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






