“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቄስ እንዳልካቸው አቻምየለህ ታግቶ መቆየት አስመልክቶ አዲስ መረጃ ይፋ እንደሚያደርጉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።

እነዚህ ወገኖች እንዳሉት እገታው የተፈጸመው ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ባሉ ጥቆማ ሰጪዎች ሲሆን፣ እነዚሁ አገልጋዮች ይህ ብቻ ሳይሆን በበርካታ የወንጀል ድርጊቶች በስፍራው ካሉ የሚታወቁ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ተባባሪ ሆነዋል።

“በእነዚሁ ካህናት ተላላኪነት ከመልዐከ መንክራት ቀሲስ እንዳልካቸው ሌላ በወረታ ደብረ መንክራት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ውስጥ ከሳቸው በፊት ሁለት ቄሶችን ቄስ አግማስ ፀጋን እና ቄስ አዳነ ማይደፍሮ ተይዘው ነበር።” የሚሉት መረጃ ያላቸው ክፍሎች፣ ቄሶች በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ቄስ አግማስ የካቴድራሉ ፀሀፊ ሲሆኑ፣ ቄስ አዳነ ማንደፍሮ ደግሞ የደብሩ ሒሳብ ሹም እንደነበሩም አመልክተዋል። “እነዚህንም ካህናት ያሲያዟቸው እነዚሁ ተላላኪ ካህናት ናቸው መረጃው አለን አስፈላጊ ከሆነ እና ሚዲያው ይፋ የሚያደርገው ከሆነ ከነ ሙሉ ማስረጃው እንልካለን” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።

“የምንጠብቀው አንድ ጉዳይ ነው። ስማቸውን ዘርዝረን ይፋ እናደርጋለን” ያሉት የመረጃው ባለቤቶች በስም ይፋ ላለማድረግ እስካሁን የታገሱት ኃላፊነት ስለሚሰማቸው ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። ይህ የጥቆማ ሰጪዎቹ መልዕክት ከመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው ከፋኖ ጋር የሚሰሩ፣ መረጃ የሚያቀብሉ፣ የመከላከያ ስምሪትንና ዕቅድ የሚያፈተልኩ፣ የባንክ መረጃን አሳልፈው የሚሰጡ እገታና ዘረፋ ላይ አብረው የሚሰሩ አሉ ከሚለው ጥቆማ ጋር የሚመሳሰል ሆኗል።

“ጠብመንጃ እንደ ንግድ” በሚለው አዲሱ ስልት በየጫካው እየተደበቁ ህዝብን የሚያማርሩ ታጣቂዎችን አስመልክቶ በተለያዩ መድረኮች ሕዝብ ዝምታውን እያሰበረ መሆኑ ይታወሳል። “ራሱን ውባንተ አባተ ስም ሰይሞ አያጭበረበረ በሚኖረው ውባንተ ኮር” በማለት ስም እየጠሩ ድርጊቱን የኮነኑ ጥቂት አይደሉም።
“ህዝብን ያገለለ፣ ህዝብን የደፈረ፣ያገተና ያሰቃየ ትውልድ መድረሻው የት ይሆን” በሚል ምሬቱን የሚገልጸው የአማራ ክልል ሕዝብ “መጨረሻው ወዴት ነው? መጨረሻው ምን ይሆን?” የሚሉ በበረከቱበት በአሁኑ ሰዓት እኚህ አባት ታግተው አራት ሚሊዮን ካልተከፈለ እንደማይለቀቁ ያስታወቁት የውብ አንተ ኮር አባል ይበልጣል ጣፈጠ እንደሆነ ተመልክቷል።

“የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እንደ ድርጅት ተጠያቂዎች መሆናችሁን አምናችሁ እኒህ አባት የማስፈታት ኃላፊነት ብትዎስዱ የተሻለ ነው። አሁን ሁሉም ነገር ከሕዝብ የመቻል አቅም በላይ እየሆነ ነው። ጭራሽ በእምነቱ ተመጣበት። ሕዝብ እስከምን እየታገሰ እንደሆነ የገባችሁ አልመሰለኝ” በማለት በግል ፌስ ቡክ ገጹ እውቂያ እንዳላቸው ጠቅሶ ያስጠነቀቀም አለ።
“ድምፅ እምትሆኑት ለቤተክርስቲያን ነውና በአባታችን አለመኖር ብዙ ስለተጎዳን በህብረት እንጸልይ” የሚለው ጥሪ ህዝቡ በተፈጸመው እገታ ተስፋ መቁረጡን የሚያሳይ ሆኗል።

“በእርግጥ ይሄ ቡድን ነውር ጌጡ ነው። በሕዝብ ሚዛን የመቅለሉ ነገር አያሳስበውም። ለምን እንደሚታገልም የዓላማና የግብ ግልፅነት የለውም። አላማና ግብህ ምንድን ነው ብትለው መዝረፍና መስረቅ ሊልህ ይችላል። የዚህ አካባቢ አብዛኛው ፋኖ ነኝ ባይ እገታን የትግሉ አካል ብቻ ሳይሆን ዋና የገቢ ምንጭ ካደረገው ቆይቷል። ትግል ማስመሰያ እንጂ ዓላማው በዝርፊያ ኪስን መሙላት ነው” በማለት ምሬት የተመላበት አስተያየት ያሰራጩ አሉ።

ይህንኑ እገታ ፈጽሟል የተባለው የፋኖ ክንፍ ዳባት፣ ገደብዬ፣ አምባጊዮርጊስ አካባቢዎች ስለተፈፀሙ አገታዎች በማንሳት ቁጣቸውን የገለጹ፣ ሕፃናት መገደላቸውን፣ በእግት ከ1 ሚሊዮን እስከ 7 ሚሊዮን ብር መረከባቸውን፣ ሴት ልጇን አላስደፍርም ያለች እናት መገደሏን፣ በመዘርዘር ቁጣቸውን ገልጸዋል።
በቄስ እንዳልካቸውን አግተው አራት ሚሊዮን ብር የጠየቁት የተጠቀሱት አጋቾች መልስ እንዲሰጡ ከስፍራው በተገኘ ስልክ ቢሞከርም መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። “ተሳስተሃል። ሁለተኛ እንዳትደውል” የሚል መልስ ከተሰጠ በሁዋላ ስልኩን አጥፍተውታል። አሁንም ቢሆን ምላሽ ካላቸው ዝግጅት ክፍላችን ለማካተት ፈቃደኛ ምነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...