በራያ አላማጣ ስምንት አድባራት ለጥምቀት በዓል ታቦታቸውን ሳይወጡ ዋሉ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ታላቁ የጥምቀት በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሮ ቢውልም፣ በራያ አላማጣ ከተማ ግን በዓሉ ሳይከበር መዋሉንና አድባራት ተዘግተው መዋላቸውን አዲስ ሪፖርተር አረጋግጧል።

የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለአዲስ ሪፖርተር እንደገለጹት፣ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ሳይከበሩ መቅረታቸውን ተናግረዋል።

እንደ ከንቲባው ገለጻ፣ ለክስተቱ ዋነኛው መንስኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኘው “መንበረ ሰላማ” ሲኖዶስ መካከል ያለው የአስተዳደር ሽኩቻ ነው።

የመንበረ ሰላማ አባቶች “ራያ በእኛ ስር ነው የሚመራው” በሚል ወደ አላማጣ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ ካህናቱና ምዕመኑ “ከእናት ቤተክርስቲያን ከተለየ አካል ጋር በዓሉን ልናከብር አይገባም” በሚል በዝምታ ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ከንቲባው ገልጸዋል።

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ እንደገለጹት፣ የታቦት ማደሪያው (ጥምቀተ ባሕሩ) በታጣቂዎች ተይዞ መዋሉ ለምዕመኑ ስጋት ሆኗል። ሀገረ ስብከቱ ለኮማንድ ፖስቱ ጥያቄ ቢያቀርብም “ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ነው” የሚል ምላሽ ማግኘቱንና ግጭትን ለመከላከል ሲባል ታቦታት ሳይወጡ መቅረታቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባው አክለውም፤ ካህናትና ዲያቆናት እየታፈኑ ወደ ሞኸኒ እንደሚወሰዱና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው የገለጹ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት በርካታ አገልጋዮች ወደ ቆቦና ወልዲያ ተፈናቅለዋል ብለዋል።

የታጣቂ ኃይሎች የራያ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤትንና የወረዳ ቤተ ክህነት ቢሮዎችን በኃይል በመቆጣጠር፣ ንብረቶችና ቅርሶችን ዘርፈው ለወታደራዊ አገልግሎት እያዋሉ መሆኑ ተገልጿል።

በዘንድሮው በዓል ታቦታቸውን ሳያወጡ የቀሩት ስምንት ታዋቂ አድባራት የአላማጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ አቡነ አረጋዊ፣ ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅድስት ደብረ ምሥራቅ ኪዳነ ምህረት እና ደብረ መድኃኒት ኢየሱስ ካቴድራል መሆናቸውን ከንቲባው ተናግረዋል።

የራያ ሀገረ ስብከት መንግስት በአካባቢው ሰላም እንዲያስከብር፣ የታሰሩ ካህናት እንዲፈቱ እና የሕዝቡ የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበር ጥሪ አቅርቧል። አዲስ ሪፖርተር ጉዳዩን በሚመለከት ከሕወሓት ወገን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካም፣ ምላሽ ባገኘን ጊዜ የምናጋራ መሆኑን እንገልጻለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የክፉ ጊዜ ወዳጅነት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኤምሬትስ ጉብኝት አንድምታዎች  

      የኢትዮጵያን ቀጠናዊ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚከፈለው መስዋዕትነት ታሪካዊ ዋጋ...

ማርኮ ሮቢዮ ከአብይ ጋር መከሩ፤ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በቀይ ባህርና በአፍሪቃ ቀንድ አሰላለፋቸው ይፋ እየሆነ ነው

አዲስ ሪፖርተር - አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጠብመንጃ ግብግብ...

How Ethiopia Anchors the Horn Against Sudan’s Ongoing War

Civil wars are often explained as the inevitable eruption...

ነዳጅ ከዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፤ ከ 3 እስከ 10 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ - የገንዘብ ሚኒስቴር በመካከለኛው ምስራቅ...