አዲስ አበባ (አዲስ ሪፖርተር) — የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ያለው አሁናዊው ወታደራዊ፣ ቴክኖሎጂያዊና የሰው ኃይል ብልጫ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት የሆነው የአስመራን መንግስት ለመንቀል ቀናት እንደሚበቁት ተመለከተ። ስለ ኤርትራ መንግስትና ቁመና በህወሃት አመራር ዘመናቸው መረጃ ለማሰባሰብ ዕድል ያገኙት አቶ ጌታችረው ረዳ እንዳሉት ህወሃት “ኢሳያስ በተፈጠሮ ሞት ይወገዳል” የሚል መርህ ሲከተለ ጊዜ መፍጀቱን አመልክተዋል።
የኤርትራ አምባገነን መንግስት ያለበትን መዋቅራዊ ድክመትና መፈራረስ በማንሳት ያነጻጸሩት አቶ ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ ጦር በስትራቴጂያዊው ማይሁጻ አቅጣጫ ወታደራዊ ምሽጉን ሰብሮ የገባ ዕለት የኤርትራን መንግሥት የማስወገድ ጉዳይ የሰዓታት ወይም የጥቂት ቀናት ብቻ እንደሚሆን አመክተዋል። አቶ ጌታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምስራቅ አፍሪቃ አማካሪ ከመሆናቸው አንጻር ንግግራቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
አቶ ጌታቸው የሁለቱን አገራት ወታደራዊ አቅም፣ የቴክኖሎጂ ደረጃ፣ የሰራዊት ብዛትና የደኅንነት ሥጋቶችን በጥልቅ በመተንተን የኢትዮጵያን ፍጹም የበላይነት በማሳየት በማይሁጻ ግንባር ላይ በማተኮር በዝርዝር የተናገሩት “በሰሜን የተጀመረው ጦርነት ቅድሚያስ ወደ ኤርትራ መሆንን እንደነበረበት ከሽንፈቱ በኋላ በቁጭት ከተናገሩት ጋር ገጥሟል።
የማይሁጻ አቅጣጫ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ፦ አቶ ጌታቸው በወታደራዊ ቋንቋ ሲያስረዱ፣ ማይሁጻ በተባለው ቦታ ላይ የመከላከያ ካምፕ ከተመሠረተና የኤርትራ መከላከያ ምሽግ በዚህ አቅጣጫ ከተሰበረ፣ ወደ መሃል አገር ለመግባት የሚኖረው ሂደት በቀጥታ የኤርትራን ኃይል የመንዳት ያህል ፈጣን እንደሚሆን ገልጸዋል። ይህ ወታደራዊ እርምጃ ከተከናወነም ወደ አስመራ ለመግባት ቀናት ሳይሆን ሰዓታት ብቻ ሊፈጅ እንደሚችል አስምረውበታል።
የቴክኖሎጂ ኋላቀርነትና ማርጀት፦ የኤርትራ መከላከያ ኃይል በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂ ብልጫ የሌለው ከመሆኑም በላይ፣ የታጠቀቻቸው የጦር መሣሪያዎች እጅግ ያረጁና ለዘመናዊ ውጊያ የማይመጥኑ እንደሆኑ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል። የቲ-54 (T-54) እና ቲ-55 (T-55) ታንኮች ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ይህ የቴክኖሎጂ ኋላቀርነት በማይሁጻ ግንባርም ሆነ በማንኛውም አቅጣጫ የኢሳያስ ጦር ፊት ለፊት የሚደረግ ዘመናዊ ጦርነትን መቋቋም እንደማይችል አስታውቀዋል።
ሊተካ የማይችል የሰው ኃይል (የዲሞግራፊ) ቀውስ፦ ኤርትራ በከፍተኛ የስደት መጠንና በሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል ምክንያት የደረሰባትን የዲሞግራፊ ቀውስ ያነሱት አቶ ጌታቸው፣ አገሪቱ በጦርነት ወቅት በማይሁጻና በሌሎች ግንባሮች የሚረግፈውን ሰራዊት መልሶ ለመተካትና አዳዲስ ኃይሎችን ለማሰለፍ የሚያስችል አቅም እንደሌላት አስረድተዋል። በተቃራኒው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በሰው ኃይል ብዛትና አቅምን በየጊዜው በማደስ ረገድ ፍጹም የበላይነት እንዳለው አመልክተዋል። በዚሁ መነሻ ወጣቶቿን በስደት ያጣችው ኤርትራ ኢትዮጵያ ለደህንነቷ ስጋት የሆነውን የሻዕቢያ ተላላኪ መንግስት መወገድ እንዳለበት በይፋ ገልጸዋል።
ይህንን በማይሁጻ አቅጣጫ ያለውን ስትራቴጂያዊና ወታደራዊ ድክመቷን ጠንቅቃ የምታውቀው አስመራ፣ የደኅንነት ሥጋቷን ለመቀነስና ውጊያውን ከራሷ ድንበር ለማራቅ የውክልና ጦርነትን እንደ ጋሻ እየተጠቀመችበት እንደሆነ አቶ ጌታቸው አክለው ገልጸዋል። በዚሁ መሰረት ፋኖ፣ል ኦነግ ሸኔን፣ ህወሃትን፣ የጉሙዝ ታጣቂዎችን ወዘተ በመጠቀም ጦርነቱ ወደ ኤርትራ ድንበር ድርሻ እንዳይል እነደሚጠቀሙባቸው ገልጸዋል።
አገሪቱ የገጠማትን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ መበስበስ በቀጥታ መከላከል ስላልቻለች፣ የኢትዮጵያን የውስጥ ታጣቂዎች በማስታጠቅና የውስጥ ትርምስን “በርካሽ ዋጋ” በማስፈጸም የራሷን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም እየጣረች መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው፣ ይህ አካሄድ ግን ኤርትራን እንደ አገር ከመፈራረስ ሊያድናት እንደማይችልና የኢትዮጵያ ጦር በጥቂት ጊዜያት ውስጥ የመንግሥቱን ሕልውና የማክተም ሙሉ አቅም እንዳለው በትንተናቸው አረጋግጠዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በዋር ኮሌጅ ካባዥነት ባቀረቡት ንግግር የሰጡት መረጃ ሻዕቢያን በጥልቅ እንደሚያውቅ፣ ከህወሃት ቁልፍ ሰዎች ጋር አብረው ሲሰሩ ከሰበሰቡት መረጃ አንጻር፣ ነዚሁ ጉዳይ ከውጭ አገራት ከፍተኛ ሰዎች፣ አገራትና ተቋማት ጋር ካላቸው ግንኙነትና አሁን ካላቸው ኃላፊነት አንጻር ያቀረቡት ትንተናና ድምዳሜ ለበርካቶች ትሩም የሰጠ ሆኗል። በተለይም ለሻዕቢያ ባለስልታን ቀታዩን የኢዮጵያን አካሄድና ስልት አመላካች ሆኖላቸዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






