ጋዜጠኛው ታፍኖ 300 ሺህ ከፍሎ ተፈታ፤ ” መታገትህ ሚዲያ ቢሰማና ጫጫታ ቢነሳ ትገደላለህ” ፋኖ

Date:

አዲስ ሪፖርተር (ጎንደር)- የጎንደር አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ጋዜጠኛ ደስታ ካሳ በፋኖ ታጣቂዎች ታፍኖ ከወር በሁዋላ ሶስት መቶ ሺህ ብር ከፍሎ መፈታቱን መዋጮ ሲያሰባስቡ የነበሩ ወገኖችን ጠቅሶ የአዲስ ሪፖርተር የጎንደር ተባባሪ አመለከተ። አጋቾቹ የጋዜጠኛው መታገት ለመከላከያ፣ ለሚዲያና ለአካባቢ የጸጥታ ኃይሎች ቢነገር በአንድ ጥይት እንደሚገድሉት በመዛት ጉዳዩ ሳይዘገብ ቆይቷል።

ደስታ የታገተው ከጎንደር ወደ ባህር ዳር ሲሄድ ማክሰኚት ላይ ነው። ማክሰኚት ከጎንደር 18 ኪሎሜትር ላይ ትገኛለች።በተደጋጋሚ ሰሊጥ የጫኑ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከሚቃጠሉበት ከዚህ ቦታ ላይ የታገተው ደስታ ሶስት መቶ ሺህ ብር እንዲከፍል፣ ካልከፈለ እንደሚገድሉት በተነገርው መሰረት ቤተሰቦችቹና ወዳጆቹ እንዲሁም ባልደረቦቹ የከተማዋ ነዋሪዎችን በማስተባበር የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍለው አንድ ወር ግድም ከተቀመጠበት ጫካ ወጥቷል።

አጋቾቹ የፋኖ ኃይሎች፣ በስልክ በተደረገ ግንኙነት አማካይነት ብሩን በሰው ወዳሉበት ግድም ተወስዶ ከተረከቡ በሁዋላ የተፈታው ደስታ ነጻ ከሆነ በሁዋላም ቢሆን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይሰጥ በመከልከሉ በስጋት ምንም ማለት እንደማይፈልግ ቅረብ የሆኑት ለጎንደር ተባባሪያችን ነግረውታል።

“ክላሽ ወድረው ካሉት ስፍራ የተላከላቸውን ገንዘብ ይዞ ከሄደ ሰው ሲቀበሉ፣ ያስቀመጠው ሰው ፊቱን አዙሮ እንዲሄድ አዘዙት። ዞሮ እንዳይመለከት አስጠነቀቁት።” በማለት ብሩን ካደረሰው ሰው የሰሙትን ያስረዱ እንዳሉት ወዲያው ደስታ ነጻ ሊሆን ችሏል። አጋቾቹ ገንዘብ ከመጠየቃቸው ሌላ እገታ የሚፈጽሙበት ፖለቲካዊ ምክንያት እንደሌላችውም ለማወቅ ተችሏል።

ደስታ በአሁኑ ሰዓት መደበኛ ስራውን እያከናወነ ሲሆን። ከምስክሮቹ እንደተሰማው ሞባይል የያዘ፣ ንጹህ ልብስ የለበሰ፣ እንዲሁም ጥቆማ የተላለፈበት ሰው እንደሚታገት ገልጸዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ ብሉይ ምሁር አመራር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው 'ምድር አንቀጥቅጥ' ሰላማዊ...