“በሰሜን ሸዋ በስም የሚታወቁ የፋኖ አመራሮች፣ አጃቢዎችና ከ60 በላይ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ከተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች አንዱ ከሆነው የመከታው ቡድን በተገኘ መረጃ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ። በድንገት በተወሰደ እርምጃ አመራሮችን ጨምሮ ታጣቂዎች በገደላቸው ታውቋል።

ከአካባቢው የጸጥታ ኃይሎች የተገኘው መረጃ እንደሚያመልክተው ድንገተኛ እርምጃው የተወሰደው ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ኩሬ በረት ቀበሌ እቧይ ግድ የተባለ ቦታ ነው።

“ድንገተኛ” የተባለው ኦፕሬሽን የተከናወነው ከመከታው ቡድን በተገኘ መረጃ እንደሆነ ዜናውን ያሰራጩት አመልክተዋል። መከታው ማሞ በደሳለኝ ሲያስብ በሚመራውን የሸዋ ቡድን ላይ ጥቃት ፈፅሞና በርካቶችን አስሮ እንደነበር ያስታወሰው ዜናው፣ መረጃው የተገኘው ከመከታው ቡድን እንደሆነ ቢገልጽም ለተመሳሳይ ኦፕሬሽን ሲባል ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

እርምጃ የተወሰደባቸውን አመራሮች ስም፣ ማዕረግና ልዩ የስራ ድርሻ ጠቅሶ ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ይህ እስከተዘገበ ድረስ ማስተባበያ አልተሰማም።
እንደ መረጃው እርምጃ ተወሰደባቸው የተባሉት አመራሮች

1 አጌጠ የሸዋ እዝ ሎጂስቲክስ ኃላፊ
2 አብረሐም የእስረኛ አስተዳደር
3 ሀምሳ አለቃ ታዬ ብርሐኑ የአስቻለው ደሴ ክ/ጦ ዘመቻ ኃላፊ
4 ይበልጣል ማሩ የራምቦ ክ/ጦ ወታደራዊ አዛዥ
5 ተስፋዬ መካሻ የደሳለኝ ሲያስብሸዋ ምክትል አዛዥ እና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ
6 መቶ አለቃ ልመነው ዘውዴ የደሳለኝ ቡድን ም/ል አዛዥ
7 ዳዊት ቀፀላ የደሳለኝ ቡድን ፖለቲካ ዝርፍ ኃላፊ
8 አብረሐም ብርሌ የደሳለኝ ቡድን ወታደራዊ አዛዥ
9 የኮ/ል ማን ነገረው መለሰ ሶስት ታማኝ አጃቢዎችን ጨምሮ ከ60 በላይ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተመልክቷል። ተመሳሳይ ኦፕሬሽኖች በተለያዩ አካባቢዎች እንደሚደረጉም ለማወቅ ተችሏል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አንቀጽ 39 «እስከ መገንጠል» እና «ያለገደብ» የሚሉ ድንጋጌዎች እንዲሰረዙ ስምምነት ተደረሰ -ሪፖርት

"እስከመገንጠል" የሚለው እና ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና ከጅምሩ የተቃወመው...

የጋራ መድረክ በሻዕቢያ እንደሚመራ ሰብሳቢው አረጋገጡ፤ “ኢሳያስ እየረዱን ለምን ተቃውሞ ይሰነዘራል”

አዲስ ሪፖርተር - ራሱን "የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የጋራ የትግል...

በችኮላ የሚወጡ ሕጎች የሕግ አወጣጥ ሥርዓቱን እያዳከሙ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋት ላይ የተካሄደ ጥናት፣ በችኮላና...