አዲስ ሪፖርተር ዜና | አዲስ አበባ | ጌታቸው አሰፋ ለረዥም ዓመታት የፌደራል ፖሊስን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በኃላፊነት ሲመራ የነበረ፣ አሁን ደግሞ ከህወሓት ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጀርባ ሆኖ ሀገርን ለማፍረስ ትዕዛዝ የሚሰጥ፣ ዘመኑን ሙሉ በደም የተጨማለቀ ግለሰብ ነው። በህወሃት በህልና በፈለፈላቸው የክፋት ማስፈጸሚያ ሚዲያዎቹ አማካይነት “የግል ህይወቱን መስዋት አድርጎ በሚለው” ስላቅ ብዙ ተለፍፎለታል። ጌታቸው በስልጣን ላይ በነበረባቸው ረዥም ዓመታትም ሆነ አሁን ስሙ ሲነሳ በህዝብ ዘንዳ የሚፈጠረው ስሜት የሰላም እና የደህንነት ሳይሆን የአፈና፣ የፍርሃት፣ የጭነቀት፣ የስቃይ፣ የሞትና የመሳሰሉ ክፉ ስሜቶች ናቸው።
ምንም እንኳን በይፋ እንደ ብሔራዊ ጀግና ለመታየት ህዝቡን በመምሰል በፎቶ የተደገፈ ፕሮፖጋንዳቸውን ለማሳየት ቢሞክሩም፤ ይፋ የተደረጉ ሚስጥራዊ ሰነዶች እንደሚያስረዱት ከሆነ ግን የሰው አዕምሮ ከሚገምተው በላይ የክፋት ድርጊቶችን ያሳያሉ።
ጌታቸው መሸሸጊያው ባደረገው የትግራይ ሕዝብ ላይ ትውልድን የማምከን መረብ የዘረጋ የሞት መለአክ ነው። በዚህ ለጥቂቶች ጥቅም ሲባል በተዘረጋው የአፈና መረብ የትግራይን ሕዝብ ለግማሽ መዕተ ዓመት እንዲማቅቅ ተደርጓል። በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ግፍ የተፈጸመበት የትግራይ ሕዝብ ቀኑ ሲደርስ ለደረሰበት በደል የፍትህ ጥያቄ እንዳያነሳ፣ ጌታቸው እና እሱን መሰል አመራሮች ይባስ ብለው በግፍ ያማቀቁትን ህዝብ መልሰው እንደ መከላከያ ጋሻ በመጠቀም ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ እየተጠቀሙበት ነው።
እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ የጥፋት፣ የአፈና፣ የሞት መረባቸውን በስፋት ዘርግተዋል። በዚህ ሁሉ የአፈና መረባቸው የሚያደርሱትን የህዝቡን እንግልት (Societal Despair) እንደ መሳሪያ በመጠቀም በየደረጃው የራሳቸውን ጥቅም ማስከበሪይና የስልጣናቸው ማስጥበቂያ ያደርጉታል።
ጌታቸው አስፋ እና መሰሎቹ በይፋዊ ንግግሮቻቸው የትግራይ ወጣቶችን የክልሉ ተስፋና መከታ አድርገው ቢያወድሱም በግል የሂሳብ መዝገባቸው ግን እንደ ንብረት (Commodiy of Identity) ይቆጥሯቸዋል። የመንግስት መዋቅር በፈረሰበት (Institutional Starvation) እና መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዳልነበሩ በሆኑባቸው የትግራይ አካባቢዎች፣ የጌታቸው መረብ ወጣቶችን ለእኩይ አላማው ማስፈጸሚያነት እየተጠቀመበት ይገኛል።
እነዚህ የክፋት መጠንሰሻዎች በፈጠሩት መረብ አማካኝነት ማህበረሰቡን በማዋረድ የራሳቸውን የስልጣን ግብ ለማሳካት ሲሉ ለሰው ህይወት ክብር አልባ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ በዚሁ የወንጀል መተገበሪያ መረባቸው አማካይነት በሚፈጽሙት ወንጀል ሳቢያ ድፍን የትግራይ ህዝብ ሊገለጽ በማይችል የስነ-ልቦና እና የኢኮኖሚ ጠባሳ ውስጥ እንዲዘፈቅ አድርገውታል። “ጽድቁ ቀርቶብኝ፣ በቅጡ በኮነነኝ” እንዳለችው እናት፣ የትግራይ ሕዝብ ከእነዚህ አመራሮች እንኳን ሊጠቀም ተራ ዜጋ ሆኖ አፈር እየገፋ መኖር እንኳን እንዳይችል ተደርጓል።
ለጌታቸው አሰፋና ለቡድኑ ህዝቡ የሚታየው እንደ ጥቅም ማስከበሪያ ቁስ እንጂ መብት እንዳለው ሰብአዊ ፍጡር አይደለም። እጅግ አሳዛኙ ነገር ትግራዋይ በየመንደራቸው ሳይቀር የተንሰራፋውን አፈናና እና ሰቆቃ “እስከመቼ በዚህ ይዘለቃል” ብለው ጥያቄ እንዳያነሱ፣ የጌታቸው አሰፋ መረብ ያቀፋቸው የወንጀሉና የጥቅሙ ተቋዳሾች የትግራይ የጠላትነት ምስልና ትርክት ፈጥረውለት በስጋት እንዲኖር አድርገውታል። በዚሁ የፈጠራ ትርክት የእነ ጌታቸው ቡድን ለትግራይ ህዝብ የሳሉለትን የፈጠራ ጠላት የሚታደግላቸውና ለትግራይ የተላኩ መለኮታዊ ኃይል ወይም መሲህ (savior complex propaganda) ተደረግዋል። ህዝቡን ስጋትና ፍርሃት ውስጥ የሚከተው የእነ ጌታቸው የውንብድና መረብ፣ የትግራይ ህዝብ ዛሬም ከዚህ ስጋት እንዳይወጣ እየሰራ ነው። ጌታቸውም ሆነ ሌሎቹ የትውልዱ አምካኝ መረብ አባላቶችና የህውሃት አመራሮች በትግራይ ህዝብ ላይ በጅምላና በተናጠል የሚፈጽሙት ግፍ የራሳቸውን የግል ህይወት ቅንጣት ስለማይነካው ልጆቻቸው በግርድፉ የምለው ይኖራል!

የጌታቸው አሰፋ መደራደሪያ (Bargaining Chip )
የጌታቸው አሰፋ በሴራ፣ በአፈናና በግፍ የተሞሉ ተግባራቱ፣ የትግራይን ሕዝብ ለተለያዩ ቀውሶች የዳረገ፣ እንደ ክልል ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለ፣ አሁንም መቆሚያ የሌለው መከራ ውስጥ የከተተ ስለ መሆኑ ለመረዳት ጠቢብ መሆን አያስፈልግም። ግልጽና ማመን ሰው የሆነ ሁሉ የሚረዳው ሃቅ ነው። ትግራዋይ ሆነውም ይሁን በጥቅም ተገዝተው በጌታቸው የአፈና ኔትወርክ ስር የጋራ ጥቅማቸውን የሚያሳልጡ የተሰባሰቡበት ውስብስብ የመዋቅር ቡድን አለ። እነዚህ ግለሰቦች የትግራይን ህዝብ ለረጅም ጊዜ በሰቆቃ ውስጥ እንዲማቅቅ ሲፈርዱበት የራሳቸው ቤተሰቦች በውጭ ሀገራት በቅንጦት እንዲኖሩ በማመቻቸት፣ የተቀራመተውን ሀብት ወደ ውጪ በማሸሽ (Illicit Financial Flows) የሚኖሩ ናቸው።
በአሁን ጊዜ የጌታቸው አሰፋ እና ያዋቀረው ቡድን አካሄድ ማህበረሰቡን እንደ አንድ የንግድ ዕቃ ወይም ቁስ በመቁጠር ለግል ጥቅማቸው እንደ መደራደሪያ (Bargaining Chip) እየተጠቀሙበት ነው። በዚህም ምክንያት አብዛኛው የትግራይ ማህበረሰብ ለረጅም ዓመታት በጨለማና በስቃይ ውስጥ እንዲኖር ተገዷል።
በትግራይ የወጣቱ እውነታ VS የጌታቸው አሰፋ የፎቶ ትግል

ማመሳከሪያ የማይሻ እውነታ እነሆ ! በሰሜን የተካሄደው ጦርነት ተስፋ የነበረበውን ክልል ወደ ባዶነት ቀይሮታል። ውጤቱም የትግራይን ማህበረሰብ ክፉኛ ጎድቶቷል። የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት በሱዳን እየተካሄደ ላለው አሰቃቂ የውክልና ጦርነት በማያገባው እንዲገባ ተደርጎ ግንባር ቀደም ሰለባ ሆኗል፤ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸው ከቤታቸው በአፈሳ ሲወሰዱ የሚያዩት ስቃይና የሚያፈሱት እንባ የሚያስ\ችንቅ፣ ረፍት የሚነሳ፣ ከምንም በላይ በቀላሉ ሊረሳ የማይችል የስነልቦና ጠባሳ የሚያሳድር ነው።
ልጆቻቸውን በመከራ ውስጥ ያሳደጉ እናቶች አሁን በጨካኝ አመራሮች ምክንያት የወላድ መካን እየሆኑ ይገኛሉ። በትግራይ “ብሔራዊ ግዴታ” በሚል ሽፋን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶችን መመልመል እና ማፈስ እንደ አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ተስፋፍቷል። እነዚህ ወጣቶች በልጅነታቸው በጉልበት ከቤተሰቦቻቸው ተነጥቀው በግዳጅ የዚህ የአፈና መረብ አስፈጻሚዎች ሰለባ በመሆናቸው የሚያሳድርባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ እጅግ ከፍተኛ ነው። የትግራይ አዲሱ ትውልድ ለዓመታት የሚፈትነበት ትራውማም ጭምር ነው። እናቶች/ አባቶች ልጆቻቸው የት እንዳሉና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሳያውቁ የጭንቀት ህይወት ይገፋሉ። ደጅ ደጁን እያዩ ቀናቸውን ይቆጥራሉ። “አንድ ቀን ድንገት ልጄ በሩን ያንኳኳል ወይም ታንኳኳላች” በማለት በቁም ስቃይ ህይወትን መግፋ ምን ያህል መራር እንደሆነ የሚያውቁት የደረሰባቸው ብቻ ናቸው።
የችግሩ ግዝፈት ዘመን ተሻጋሪ፣ በቀላሉ የማይሽር መሆኑ ቢታወቅም፣ እነ ጌታቸውና ቡድኑ በህይወት የተረፈ የትግራይ ወጣትን ማየት ትግራይ ላይ ማየት ሌላ ሴራና የእልቂት እቅድ እንዲያወጡ ይገፋፋቸው ካልሆነ በቀር፣ ሃዘን የሚባል ነገር ባጠገባቸውም አያልፍም። ለምን ቢባል የጌታቸው የአፈና መረብ ህይወቱ ሁሉ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ ስለሆነ፣ ስልጣንን መልቀቅ፣ በተረጋጋ ሁኔታ መኖር ተተያቂነትን ስለሚያስነሳ በጥንቃቄ የሚሰሩት ይህ እንዳይሆን ነው። ምን ዓይነት ልክፍት ይሆን? ምን ዓይነት የስነ ልቦና መዋቅር ይሆን? እንዴትና እንደምን ….
አካባቢውን ለቀው የሚወጡ ወጣቶች በተለያዩ አህጉራት ለተሰረጉ የብዝበዛ መረቦች ተዳርገዋል። እነዚህን የከፋቸው ወጣቶች የነጻነት ታጋዮች በማስመሰል ለራሳቸው ጥቅም ወደ ጨካኝ የጦርነት ካምፖች እንዲጋዙ ሆነዋል። የትግራይ እናቶች ለልጆቻቸው ያላቸው ተስፋ እየተሟጠጠ ሲሄድ፣ በየቤቱ የሚሰማው ለቅሶ እና ዋይታ ማብቂያ የሌለው ሆኗል። የጌታቸው መልእክተኞች በስጦታ እና በሐሰተኛ የተስፋ ቃላት መንደሮችን በማሸበር ህጻናትን ሲወስዱ የእናቶች ልብ እየተሰበረ ነው። በተለይም በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ቤተሰቦችንና ወላጅ አልባ ህጻናትን ላይ በማነጣጠር የሚያካሂዱት አፈና የጭካኔያቸውን ልክ የሚያሳይ ሰይጣናዊ ተግባራቸው ነው። እነዚህ ህጻናት ወደ ጦር ሜዳ ሳይሆን ለባርነት እና ለብዝበዛ መስመሮች እየተዘጋጁ መሆናቸው ለወላጅ እጅግ አሳዛኝ ነው። እናቶች ልጆቻቸውን በድጋሚ የመገናኘት ተስፋቸው በመንጠፉ ስነልቦናቸው ተናግቷል። መፈናቀል ሳያንሳቸው ልጆቻቸውን ተነጥቀው ቀርተዋል።
ከባድ የስነ–ልቦና ቀውስ

ቀጣዩ ትውልድ በመነጠቁ ምክንያት የማህበረሰቡ ማህበራዊ ፋይዳ መዛባቱና የእውቀት ሰንሰለቱ መበጠሱ የረጅም ጊዜ ጥፋት ያስከትላል። ብዙ ወጣቶች በውጭ ሀገራት ለጉልበት ስራ ወይም ለጦርነት እንዲሰለፉ በግድ ድንበር ተሻግረው ይወሰዳሉ። የቤተሰቦች ድምጽ በአሳሪ ህጎች እና በማስፈራሪያ እየተዳፈነ በመሆኑ እናቶች እንኳን ልጆቻቸውን መፈለግ ውይም “ልጄ የት ነው?” ማለት አይችሉም። የትግራይ ማህበረሰብ በህወሃት ምክንያት ለዓመታት በደረሰበት መከራ እጅግ ተዳክሟል። አሜሪካ በተለያዩ የህወሓት አመራሮች ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏ የዚህ እኩይ ተግባር ውጤት ነው። ይህ ማዕቀብ አመራሮቹን ከዓለም አቀፍ መድረክ ለመነጠልና ግፊትን ለመፍጠር ያለመ ነው። ይሁን እንጂ የህወሓት አመራሮች በአገሪቱ ውስጥ ካለው የፖለቲካ ድርድር እና የአምነስቲ አሰራር ጋር በተያያዘ አሁንም የራሳቸውን መዋቅር በመጠበቅ እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለዋል።
አለም አቀፍ ማህበረሰብ በክልል ራስን በራስ ማስተዳደርና በወጣቶች መብት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት ይገባዋል። ይህ የትውልድ መመናመን ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ አደጋ ደቅኗል። ወጣቶች የሚሸጡበት መንገድ መመርመርና በህግ የሚያስጠይቅ መሆን አለበት። ህዝቡ በአንድነት በመቆም ይህንን አፈና መመከት ይጠበቅበታል። የትግራይ ወጣቶች የመኖር መብት በሁሉም ዘንድ ሊከበር ይገባል። የትግራይ እናቶች የልጆቻቸውን ስቃይ እና መከራ እያዩ በየቀኑ በሰቀቀን ውስጥ መኖራቸው የክልሉን ማህበራዊ መሰረት የሚያናጋ ነው። ይህንን እኩይ ድርጊት በአስቸኳይ ማስቆም ለክልሉ መዳን ብቸኛው መንገድ ነው።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






